1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጊምቢ ወደ ቀያቸው የተመለሱ ዜጎች ቅሬታ

ነጋሣ ደሳለኝ
ዓርብ፣ ሐምሌ 10 2018

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ከዚህ በፊት ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ገምሱ ወደ ግብርና ስራ መግባታቸውን የገለጹ። ሲሆን መኖሪያ ቤታቸው የወደመደመባቸው በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ደግሞ ለስምንት ወራት ያህል ሰብአዊ ድጋፍ እንዳላገኙ ተናግረዋል። ቤታቸው የወደመባቸው ሰዎች አሁንም መጠለያ ዉስጥ ናቸዉ ሰብአዊ ድጋፍ የላቸዉም፡፡

ጊምቢ ወረዳ
ጊምቢ ወረዳ ምስል፦ Negassa Dessalegn/DW

በጊምቢ ወደ ቀያቸው የተመለሱ ዜጎች ቅሬታ

This browser does not support the audio element.

በጊምቢ ወደ ቀያቸው የተመለሱ ዜጎች ቅሬታ

በምዕራብ ወለጋዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ከዚህ በፊት ተፈናቅለው  የነበሩ ዜጎች ገምሱ ወደ ግብርና ስራ መግባታቸውን የገለጹ ሲሆን መኖሪያ ቤታቸው የወደመባቸውና በመጠለያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ደግሞ ለስምንት ወራት ያህል ሰብአዊ ድጋፍ እንዳላገኙ አመለከቱ፡፡ በወረዳው በግጭት ወቅት መኖሪያ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ የወደመባቸው ሰዎች አሁንም በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን ከህዳር ወር ወዲህ ሰብአዊ ድጋፍ እንዳለገኙ ጠቁመዋል፡፡ እነዚህ የተመለሱ ዜጎች ግጭት ሸሽተው ወደ ደብረብርሀን በ2014 ሄደው የነበሩ ዜጎች ናቸው፡፡ የወረዳው አስተዳዳር በበኩሉ የተፈናቀሌ ዜጎች ወደ መደበኛ ህይወት መመለሳቸውን እና  በአሁኑ ወቅት በማምረት ላይ እንደሚገኙ የገለጸ ሲሆን መቋቋሚያ ወስደው  ወደ ግብርና ስራ ለመግባት ፈቃደኛ ያልሆኑ ያላቸው ግለሰቦች አሉ ሲል ገልጸዋል፡፡

በመጠለያ ውስጥ ያሉ ሰዎች ለወራት ሰብአዊ ድጋፍ  እንዳላገኙ አስታወቁ

በጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በ2014 ዓ.ም ወደ ደብረብሀን እና ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው የነበሩ በርካታ ዜጎች በ2016 ዓ.ም የተወሰኑት በሁለት ዙር ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል፡፡ ወደ ቀያቸው ከተመለሱት መካከል መኖሪያ ቤታቸው ያልተጎዳባቸው እና ወደ ቤታቸው የተመለሱ ዜጎች ከባለፈው ዓመት ጀምሮ  በግብርና ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ተገልጸዋል፡፡ በወቅት በግጭት ምክንያት መኖርያ ቤታቸው የወደመባቸው ነዋሪዎች ደግሞ በአካባቢው በተዘጋጀው መጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡን አንድ የአካባቢው ነዋሪም ሰብአዊ ድጋፍ ካገኙ ስምንት ወራት እንዳለፋቸው ተናግረዋል፡፡

በወረዳው ወደ ቤታቸው ከተመለሱት እና በአሁኑ ወቅት በግብርና ስራ ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙ የተናገሩት ሌላው ነዋሪም የአካባቢው የሰላም ሁኔታ መሻሻል ማሳየቱን ያብራሩት ሲሆን ንብረታቸው የወደመባቸው አርሶ አደሮች ወደ ስራ የገቡት በክፊል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹ወደ ቤታቸው የተመለሱት ሰዎች ወደ ግብርና ስራ ገብተዋል››

በጊምቢወረዳ ቶሌ ቀበሌ ጨቆርሳ የተባለ ሰፈር ነዋሪ የሆኑት ሌላው አርሶ አደርም በቶሌ ቀበሌ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በርካታ ቁጥር ያለው ወደ ቀያአቸው የተመለሱ ነዋሪዎች ወደ ግብርና ስራ መግባታቸውን አመልክተዋል፡፡ ለሁሉም የተፈናቀሉ ዜጎች ቤት አለመሰራቱን የተናገሩት ነዋሪው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ ሰዎች መካከል አሁንም በርካቶች በመጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸው መኖሪያ ቤታቸው የወደመባቸው ለተወሰኑ ሰዎች ለቤት ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ ከዚህ ቀደም እንደተሰጣቸውም ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ቀደም  ቡሳ ጎኖፋ የተባለ ቢሮ ድጋፍን በተጨማሪ በቀይ መስቀል በኩልም ድጋፍ ይደረግ እንደነበር የገለጹት ነዋሪው አርዳታ ከተቋረጠ አሁን ረጅም ጊዜ እንደሆነው ጠቁመዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት በሁለት ዙር በርካታ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ተመልሰዋል፡፡  

ጊምቢ ወረዳ ምስል፦ Negassa Dessalegn/DW

‹‹የተፈናቃይ ቁጥርን ዜሮ ለማድረግ አርሶ አደሩ ወደ ምርት እንዲገባ ተደርገዋል››

በምዕራብ ወለጋዞን የጊምቢ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ  የተፈናቀሉ ዜጎች በኦሮሚያና ፌደራል መንግስት ቅንጅት ወደ ቤታቸው ከተመለሱ ጊዜ አንስቶ ድጋፍ ሲደረግ እንደነበር አመልክተዋል፡፡ የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ  ቡልቻ ደመራ  በቶሌ ቀበሌ አርሶ አደሩ ወደ ግብርና ስራ መግቱን ገልጸው በክልሉ ተፈናቃይን ዜሮ ለማድረግና በምርት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ በተጀመረው መርሀ ግብር መሰረት አርሶ አደሮቹን ማቋቋም ተችሏል ብሏል፡፡

‹‹ወደ ቤታቸው የተመለሱ ሰዎች ወደ ማሳቸውም ተመልሶ አርሶ ራሳቸውን ችለዋል፡፡ ተመላልሰን ሲንደግፍ ነበር፡፡ ‹‹ቡሳ ጎኖፋ›› ኦሮሚያ ለረጅ ጊዜ ሁሉም ሰብአዊ ድጋፍ ሲያደረግ ነበር፡፡ አሁንም መንግስት በያዘው አቅጣጫ መሰረት ተፈናቃይ ተቋቁመው ራሳቸውን በማስቻል፣ የተፈናቃይ ቁጥርን ዜሮ ማድረግ ነው፡፡ በዛ አካባቢም በስፋት እያረሱ ነው፡፡ አንድ አንድ ሰዎች ወደ ግብርና መመለሱ ያለመፈለግ ነገር አለ፡፡ ያለ ስጋት ሁሉም ወደ ስራው እንዲገባ አሳውቀወናል፡፡››  የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባለፈው ዓመት በጨፈ ኦሮሚያ እንዳመለከተው በዚህ ዓመት የተፈናቀሉ ዜጎች ራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ እና በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥርን ዜሮ ለማድረግ እንዲሚሰራ ገልጾ ነበር፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW