1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጋምቤላ ክልል በጎርፍ ምክንያት ተፈናቅለው የነበሩ ወደ ቄዬአቸው መመለስ ጀመሩ

ነጋሳ ደሳለኝ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 3 2017

በጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን ጂካዎ ወረዳ በክረምት ወንዝ ሙላት እና ጎርፍ ምክንያት ተፈናቅሎ ከነበሩት ዜጎች መካከል ከ20ሺ በላይ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለሳቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል፡፡

Äthiopien | Überschwemmung in der Region Gambela
ምስል Itang woreda administration

የጋምቤላ የጎርፍ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው መመለስ ቢጀምሩም አሁንም በርካቶች መንገድ ዳር ናቸው

This browser does not support the audio element.

በጂካዎ ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎች ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ነው

በጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን ጂካዎ ወረዳ በክረምት ወንዝ ሙላት እና ጎርፍ ምክንያት ተፈናቅሎ ከነበሩት ዜጎች መካከል ከ20ሺ  በላይ  ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለሳቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል፡፡

 በወረዳው  በክረምት ወቅት በውሀ ሙላትና ጎርፍ ምክንያት ከ23 ቀበሌዎች ነበር ነዋሪዎቹ የተፈናቀሉት፡፡ በጂካዎ በጎርፍ አደጋ በዚህ ክረምት 26ሺ የሚቢልጡ ዜጎች ተፈናቅለው እንደነበር የተናገሩት አቶ አንዲሪው የተወሰኑ ዜጎች አሁንም መንገድ ዳር ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡   

ወደ መኖሪያቸው ከተመለሱት ውስጥ ያነጋገርናቸው ሁለት ነዋሪዎች እንዳሉት አብዛኞቹ  የሰብአዊ እርዳታ ለረጅም ጊዜ ሳያገኙ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡  የወረዳው አስተዳዳሪ ወደ ቤታቸው ያልተመለሱት ጥቂት ሰዎች ናቸው ቢሉም አሁንም በርካታ ሰዎች በዘመድ አዝማድ ቤቶች እንዲሁም በመንገድ ዳር በሸራ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ነዋሪቹ ተናግረዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል ጎርፍ ከ40ሺህ በላይ ሰዎችን አፈናቀለ

በጋምቤላ ክልል በዘንድሮ የክረምት ወራት የወንዞች ሙላትና ጎርፍ ባስከለለው ጉዳት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን በሰብልና ሌሎች በንብረት ላይም ጉዳት አድርሷል፡፡ በክልሉ ጂካዎ፣ዋንቱሀና ላረ በተባሉ ወረዳዎች ውስጥ በጎርፍ ምክንያት ከአርባ ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው እንደነበር የየወረዳው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በጋምቤላ ክልል በዘንድሮ የክረምት ወራት የወንዞች ሙላትና ጎርፍ ባስከለለው ጉዳት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን በሰብልና ሌሎች በንብረት ላይም ጉዳት አድርሷል፡፡ምስል Itang woreda administration

በክልሉ ኑዌር ዞን ጂካዎች ወረዳም በዚህ ባለፈው ክረምት ከተፈናቀሉት 26ሺ 836 ሰዎች መካከል አብዛኛቹ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አንዲሪው ቱት ለዲዳብሊው ተናግረዋል፡፡ ከተፈናቀሉት ሰዎች መካከል የተወሰኑት ጎርፍ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ጉዳት በማድረሱና ባለመድረቁ አለመመሳቸውን ጠቁመዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባ ወርቅ መጠን ቀነሰ

በጂካዎ ወረዳ በክረምት ወንዝ ሙላትና ጎርፍ ምክንያት ተፈናቅለው ከነበሩት መካከል አቶ ቦል እንደሚባሉ የነገሩን ነዋሪም በትምህርት ቤት፣በየእምት ቤቶችና ሌሎች ቦታዎች  ተጠልሎ ከነበሩት ሰዎች ግማሹ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን አመልክተዋል፡፡ አብዛኛው የተፈናቀሉ ሰዎች አሁንም በመንገድ ዳር ጊዜያዊ መጠለያ በመስራት እየኖሩ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡ በዚህ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ባደረሰው የጎርፍ አደጋ የተፈናቀሉ ሰዎች ለረጅም ጊዜ ሰብአዊ ድጋፍ አለማግኘታቸውን አክለዋል፡፡

በጂካዎ ወረዳ በጎርፍ አደጋ ከተፈናቀሉት መካከል አቶ ቲር እንደሚባሉ የነገሩን ሌላው ነዋሪም በአካባቢው የወንዝ መጠን በመቀነሱና የተወሰኑ ቦታዎች በመድረቃቸው በአንድ አንድ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የነበሩ የተፈናቀሉ ሰዎች መመለስ መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ብዙ ቁጥር ያላቸው የተፈናቀሉ ዜጎች አሁንም አለመመሳቸውን ነዋሪዎቸ ተናግረዋል፡፡

በጋምቤላ የተሻለ የሠላም ሁኔታ እየመጣ ነው ተባለ

በጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን ጂካዎ ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች ያቀረቡት የሰብአዊ ድጋፍ ችግርን አስመልክቶ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንድሪው ቱት በግል ድርጅቶች በኩል የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ገልጸው የዕለተ ደራሽ ሰብዊ ድጋፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች አለመድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

ጉዳዩን ለክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ማቅረባቸው ጠቁመዋል፡፡ ከጋምቤላ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር አገልግሎት  ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረኩት ጥረትም አልተሳካም፡፡ በክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በዚህ ዓመት  የባሮ እና ጊሎ ወንዞች ሙላት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማፈናቀል በንብረት ላይም ጉዳት አድርሷል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ 

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW