1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጋምቤላ ክልል ጎርፍ ከ40ሺህ በላይ ሰዎችን አፈናቀለ

ሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2016

በጋምቤላ ክልል የባሮ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በመፍሰሱ በክልሉ 5 ወራዳዎች ጉዳት ማድረሱን የጋምቤላ ክልል አደጋ አደጋ ስጋት አመራር አስታወቀ፣ ጎርፉ ባስከተለው ጉዳት ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንም አመልክቷል፡፡ ለዶይቼ ቨሌ አስተያየታቸውን የሰጡ ተፈናቃዮች እስካሁን የተደረገላቸው ድጋፍ የለም፡፡

Äthiopien I In der Region Gambella wurden mehr als 40.000 Menschen in 5 Wochen durch das Hochwasser vertrieben
ምስል Andrew Tut

ጎርፍ በጋምቤላ ክልል 5 ወረዳዎች ከ40ሺህ በላ ሰዎችን አፈናቀለ

This browser does not support the audio element.

በጋምቤላ ክልል በአምስት ወረዳዎች ጎርፍ ከ40ሺህ በላይ ሰዎችን አፈናቀለ

በጋምቤላ ክልል የባሮ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ በመፍሰሱ በክልሉ 5 ወራዳዎች ጉዳት ማድረሱን የጋምቤላ ክልል አደጋ አደጋ ስጋት አመራር    አስታወቀ፣ ጎርፉ ባስከተለው ጉዳት ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንም አመልክቷል፡፡ ለዶይቼ ቨሌ አስተያየታቸውን የሰጡ ተፈናቃዮች እስካሁን የተደረገላቸው ድወጋፍ የለም፡፡

አብዛኛው የጋምቤላ ክልል በተፈጥሮው ሜዳማ በመሆኑ በክረምት ወቅት ብዙ ቦታዎች ውሀ ይተኛባቸዋል፣ ሰሞኑንም በአካባቢው እየጣለ ባለው ዝናብ ምክንያትየባሮ ወንዝ ሞልቶ ወደ ውጪ በመፍሰሱ 40ሺህ የሚሆኑ የክልሉ 5 ወረዳ ነዋሪዎች በዋና ዋና መንገዶች አካባቢ መስፈራቸውን የጋምቤላ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጋድቤል ሙን ተናግረዋል፡፡

ጎርፉ በዋናነት በጅካዎ፣ በላሬ፣ በመኮይ፣ በጆርና ጎግ ወረዳዎች ጉዳት ማድረሱን የተናገሩት አቶ ጋድቤል ለጎርፉ ምክንያት የሆነውም የባሮ ወንዝ ከመጠን በላይ ሞልቶ ወደ ውጪ በመፍሰሱ ነው ብለዋል፡፡ በዚህም እስካሁን  41ሺህ 925 ነዋሪዎች ቤታቸው በጎርፍ መከበቡንና መፈናቀላቸውን አብራርተዋል፣ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም ተናግረዋል፣ የጉዳት መጠኑ እየተጠና እንደሆነም አስረድተዋል።

በጎርፍ ከተጠቁ ወረዳዎች መካከል አንዱ የጂካዎ ሲሆን  ዋና አስተዳዳሪው አቶ አንድሪው ቱት ትናንት ለዶቼ ቬሌ እንዳሉት በደረሰው ጎርፍ ምክንት 20ሺህ የወረዳው ነዋሪዎች በወረዳው ማዕከል “ኳችቲያንግ” ተፈናቅለው በመንግስት ቢሮዎች  ተጠልለው ነበር፤ ዋና አስተዳዳሪው ዛሬ እንደነገሩን ደግሞ ጎርፉ ዛሬ ወደ ቢሮዎች በመግባቱ ተፈናቃዮቹ ወደ ዋናው የመኪና መንገድ ለመውጣት ተገድደዋል ብለዋል፡፡

በወረዳው የ19 ቀበሌ ነዋሪዎች በጎርፉ ተፈናቅለው በቤተ እምነቶች፣ በመንግስት ቢሮዎችና በሌሎች ተቋማት ተጠልለው ቢሆንም ጎርፉ አሁንም እየጨመረ በመምጣቱ ተፈናቃዮች ወደ መንገዶች መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከተፈናቃዮች መካከል ወ/ሮ ቾል ሪያንግ በጎርፉ የምግብ አህል፣ ቀሚ አትክልቶችና የቤት ቁሳቁሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል የተደረገ ድጋፍም እስካሁን እንደሌለ አብራርተዋል፡፡

“... እቃችን ወድሟል፣ የቦቆሎና የሌሎች ሰብሎች ማሳዎች በውሀ ተጥለቅልቀዋል፣ የጓሮ አትክልቶች ወድመዋል፣ ሸራ ባለመኖሩም በዝናብ እተመታን ነው በጣም ተቸግረናል፡፡” ብለዋል፡፡

አቶ ተስሏች ኮር የተባሉ ሌላ ተፈናቃይ በበኩላቸው፣ ቤቶች በጎርፍ ተከብበዋል፣ እቃዎች ተበላሽተዋል የመጠለያ ቦታም ስለሌለ ህብረተሰቡ በመንገድ ዳር ለዝናብና ለብርድ ተዳርጓል ነው ያሉት፡፡

በጋምቤላ ክልል በአምስት ወረዳዎች ጎርፍ ከ40ሺህ በላይ ሰዎችን አፈናቀለምስል Andrew Tut

ጎርፉ በጣም ከባድ እንደሆነ ተናገሩት አቶ ተስሏች፣ የቤት እቃ ተበላሽቷል ተፈናቃዮ ወደ አውራ ጎዳና ደረቅ ቦታ ፍለጋ ላይ እንደሆነና ምንም ዓይነት እርዳታ እስካሁን እንዳልደረሰም አመልክተዋል፡፡

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ጋድቤል ሙን የተወሰነ የዝናብ መከላከያ ሸራ ወደ ቦታው መላኩን ጠቁመው በቀጣይም ተጨማሪ ቁሳቁሶችን ወደ ተፈናቃዮቹ ለመላክ እየተሰራ እንደሆነ ገልጠዋል፡፡

 በዚህ ዓመት እየጣለ ያለው ዝናብ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የመሬት ናዳ፣ የመሬት መንሸራተትና ለጎርፍ ምከንያት ሆኖ ሲሆን በህይወትና በንብረት ላይም ጉዳት አድርሷል፡፡

ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW