1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጋዛ ሰርጥ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የተላለፈ ጠንካራ ጥሪ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 15 2017

እንግሊዝ ፣ ፈረንሳይ እና ጃፓን የሚገኙበት 28 ሃገራት በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠበቅ ያለ ጥሪ አስተላለፉ ። ሃገራቱ በጋራ ባወጡት መግለጫቸው በሰርጡ እስራኤል ሲቪሊያውያንን ሳትለይ በምትወስደው ርምጃ በሰርጡ እጅግ የከፋ ሰብአዊ ቀውስ ማስከተሉን ተከትሎ በአፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቀዋል

Gazastreifen 2025 | Palästinenser warten auf Lebensmittel in Chan Yunis
ምስል፦ -/AFP/Getty Images

የጋዛው ቀውስ እንዲያበቃ የተላለፈው ጥሪ ጠንከር ያለ ነው

This browser does not support the audio element.

እንግሊዝ ፣ ፈረንሳይ እና ጃፓን የሚገኙበት 28 ሃገራት በጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠበቅ ያለ ጥሪ አስተላለፉ ። ሃገራቱ በጋራ ባወጡት መግለጫቸው በሰርጡ እስራኤል ሲቪሊያውያንን ሳትለይ በምትወስደው እርምጃ በሰርጡ እጅግ የከፋ ሰብአዊ ቀውስ ማስከተሉን ተከትሎ በአፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቀዋል። የሃገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ከስምምነት የደረሱበት መግለቻው እንደሚለው በጋዛ የደረሰው ጥፋት «አሰቃቂ » ነው።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሊያውያን ምግብ ፍለጋ ህይወታቸውን እያጡ ነው ያለው መግለጫው ቀውሱ እንዲያበቃ ዓለማቀፉ ማህበረሰብ የጋራ እና የተቀናጀ ጥረት ማድረግ አለበት ብሏል።

በተጨማሪም በኤኮኖሚ የበለጸጉ የቡድን ሰባት አባል ሃገራት ስለጉዳዩ ለመምከር ለዛሬ ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል። ምንም እንኳ እንደ አሜሪካ እና  ጀርመን ያሉ ሃገራት አሁንም በእስራኤል ላይ ጠበቅ ያለ ዓለማቀፍ ቻና እንዳይደርስ የሚያሳዩት መለሳለስ ተጠባቂ ቢሆንም ።

ገበያው ንጉሴ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW