በ«ግሪን ሃውስ» እርሻ የምግብ ዋስትናን ለመጋፈጥ የተነሳችው ካሜሩን
ቅዳሜ፣ ሐምሌ 30 2014
የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ዓለማችን በከፍተና የምግብ ሸቀጦጥ እና የኃይል አቅርቦት የዋጋ ንረት እየተናጠች ትገኛለች። ችግሩ የደረሰበት ደረጃ ዓለማቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ቀደም ሲል በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ለችግር ለተዳረጉትም ሆነ በስደት ላይ ለሚገኙ ወገኖች ምግብ እና መሰረታዊ አገልግሎት ማቅረብ እስኪሳናቸው አ,ድርሷል። እንደዚያም ሆኖ ግን ሃገራት ችግሩን ቁች ብሎ ከመጋፈጥ በማለት በጋራም ሆነ በተናጥል መፍትሄ የሚሉትን እርምጃ ለመውሰድ ታች ላይ ሲሉ ይታያሉ ።
ለዛሬ ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ካሜሩን በሩስያ ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የተፈጠረባትን የምግብ ቀውስ ለመገዳደር የሚያስችላትን መርኃ ግብር ዘርግታ ተግባራዊ ማድረግ ጀምራለች። ካሜሩን ካሁን ቀደም እምብዛም የማታውቀውን የ«ግሪን ሃውስ» መርኃ ግብር ስትጀምር አሁን ለገጠማት የምግብ ዋስትና ችግር አይነተኛ መፍትሄ ይዞልኝ ይመጣል በሚል ነው።
በእርግጥ የግሪን ሃውስ እርሻ ገና ካሜሩን መድረሱ አይደለም ስፋቱን ለመግለጽ እንጂ ። ከአስር ዓመታት በፊት ይህንን የግብርና ስልት ካሜሩን ውስጥ ሰፋ ባለ መንገድ የጀመረው ሮላንድ ፎሙንዳን ይባላል። ፎሙንዳን አሁን በካሜሩን በግሪን ሃውስ የሚለሙ ከ100 በላይ እርሻዎች አሉት ።
ካሜሩናውያን የእርሱን ጅምር እንዲከተሉ የሚፈልገው ፎሙንዳ ፤ ከውጭ የሚገቡ ሰብሎች ሀገር ውስጥ ማብቀል እንደሚቻል ማሳየት ይፈልጋል።
«ማድረግ ከቻልንባቸው ነገሮች አንዱ ካሜሩንያውያን በተለምዶ ከውጭ የሚገቡትን ወይም የሚበቅሉትን ሰብሎች እዚሁ ሀገር ውስጥ ሊበቅሉ እንደሚችሉ ማሳየት ነው።»
በፎሙንዳ የግሪን ሃውስ የእርሻ ማሳዎች ሰብሎች የሚለሙት በተዘጋ አካባቢ ነው። በእርሻ ማሳው የሚለሙት «ቼሪ» የተሰኘው የቲማቲም ዝርያ እና ቤል የተሰኘውን ሚጥሚጣ በስፋት ያመርታል ። እነዚህን የግብርና ምርቶች የሚቀበሉ የገበያ ማዕከላት ደግሞ ለአቅራቢ ደንበኛቸው እርካታቸውን እየገለጹለት ይገኛል። ለወትሮ እነዚህ ምርቶች ከውጭ የሚገቡ ነበሩ።
የአንድ የምርቶቹን ተቀባይ የገበያ ማዕከል ስራ አስኪያጅ እንደሚሉት እርካታቸው ምርቱን በቅርብ ከማግኘት ይሻገራል።
« መሰል የግብርና ምርቶችን ከውች ማስገባት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከመጠየቁ ባሻገር ውድ ነው። ምርቶቹን እዚሁ በቅርብ ማግኘት ትኩስ ምርት ፣በቅርብ እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንድናገን አስችሎናል። » ይላሉ።
በካሜሩን የግብርና ቴክኖሎጂ ትኩረት ያገኘው የፎሙንዳ ሮላንድ የግሪን ሃውስ እርሻ ተፈጥሯዊ ዕድገቱን የጠበቀ ምርት ማምረት ማምረትየ ሚያስችለውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል። የዚህ የአንድ ግለሰብ ጥረት ካሜሩናውያንን ሳይቀሰቅስ አልቀረም። የሀገሪቱ የግብርና ሚኒስቴርም እንደ አንድ ተምሳሌት ወስዶ ይህንኑ ለማስፋፋት ጊዜው አሁን እንደሆነ የተረዳ ይመስላል። በእርግጥ ነው ዓለም የገጠማትን የምግብ ዋስትና ችግር ለመቅረፍበአንድ እና ሁለት ሃገራት ላይ ጥገኝነት መሆኑ ዋጋ እንዳስከፈለ ሁሉም የተረዳ ይመስላል። አካባቢያዊ የሆኑ ምርታማነትን የሚያሳድጉ የፎሙንዳን አይነት ተሞክሮዎች መጋራቱ ጊዜው የሚጠይቀው አስቸጋሪ ዘመንን መሻገሪያ ስልቶች ናቸው ።
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ