በግብፅ ከተሞች የቀጠለው የሕዝብ ዓመጽ12 ኅዳር 2004ማክሰኞ፣ ኅዳር 12 2004ግብጽ ውስጥ የሀገሪቱን አመራር የያዘው የጦር ኃይሉ ስልጣኑን ባፋጣኝ ለሲቭሉ አስተዳደር ለማስረከብ የገባውን ቃል ባለመጠበቁና ሀገሪቱ ወደ ዴሞክራሲያዊው ስርዓት የጀመረችው ሽግግር አዝጋሚ በመሆኑ በመዲናይቱ ካይሮ በታህሪር አደባባይና በሌሎች ከተሞች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ ተቃውሞአቸውን ቀጥለዋል።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግምስል dapdማስታወቂያ በዚሁ ጊዜ ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋ በተፈጠረ ግጭት ከሰላሳ የሚበልጡ ሰልፈኞች ተገድለዋል፣ ብዙዎችም ቆስለዋል። ስለግብጽ ጊዚያዊ ሁኔታ ቀደም ሲል የጄዳ ወኪላችንን ነቢዩ ሲራክን አነጋግሬው ነበር። ነቢዩ ሲራክ አርያም ተክሌ ሂሩት መለሰ