1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በግዕዝ ቋንቋ የሚያዜመው ብቸኛው አርቲስት

እሑድ፣ የካቲት 1 2012

በግዕዝ የተሰሩ ግጥሞች ተጠቅሞ ሙዚቃ መስራት መጀመሩ የሚገልፀው ድምፃዊ ፀሃዬ የሙዚቃ ስራዎቹ በሂደት እየተለመዱና ተወዳጅ እየሆኑ መምጣታቸው ይናገራል፡፡ ድምፃዊው እስካሁን 9 ዘፈኖች በግዕዝ የሙዚቃ ግጥም ለህዝብ ያቀረበ ሲሆን በቅርቡም ሌላ ስራ ይዞ ለመቅረብ ዝግጅት ላይ ነው፡፡ 

Äthiopien Tsehaye Kinfe
ምስል፦ DW/M. Hailesilassie

መዝናኛ

This browser does not support the audio element.

አርቲስት ፀሃዬ ክንፈ ይባላል፡፡ ድምፃዊና የሙዚቃ መሳርያ ተጫዎቹ ፀሃዬ ዘፈኖች ሙሉ በሙሉ በጥንታዊ የኢትዮጵያ ቋንቋ ግዕዝ የሚያቀርብ ብቸኛ አርቲስት ነው፡፡
ፀሃዬ በግእዝ ቋንቋ የተሰሩ ዘፈኖች የያዘ የሙዚቃ አልበም ለአድማጮቹ አቅርቦ ተወዳጅነት አግኝቷል፡፡ በተለያየ ወቅትም ነጠላ የግዕዝ ዘፈኖች ሰርቶ ለአድማጮች አቅርቧል፡፡

ጥንታዊው ቋንቋ ግዕዝ በቤተክርስቲያን ብቻ ተወስኖ መቅረቱና ከሌላ ዓለማዊ አገልግሎት መጥፋቱ አሳስቦት በግዕዝ የተሰሩ ግጥሞች ተጠቅሞ ሙዚቃ መስራት መጀመሩ የሚገልፀው ድምፃዊ ፀሃዬ የሙዚቃ ስራዎቹ በሂደት እየተለመዱና ተወዳጅ እየሆኑ መምጣታቸው ይናገራል፡፡ ድምፃዊው እስካሁን 9 ዘፈኖች በግዕዝ የሙዚቃ ግጥም ለህዝብ ያቀረበ ሲሆን በቅርቡም ሌላ ስራ ይዞ ለመቅረብ ዝግጅት ላይ ነው፡፡ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW