1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጎዳና ላይ ውለው የሚያድሩ ሰዎችን ወደ ማቆያ ቦታ የመውሰድ ድርጊት ቀጥላል - ኢሰመኮ

ቅዳሜ፣ ጥር 3 2017

ብሔራዊው የመብቶች ድርጅት - ኢሰመኮ ታኅሣሥ 2017 ዓ.ም. አደረኳቸው ባላቸው ክትትሎች በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ በሚገኝ "ሰፊ መጋዝን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን" መገንዘቡን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

Äthiopien | Logo Ethiopian Human Right commission
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽን መግለጫ

This browser does not support the audio element.

በጎዳና ላይ ውለው የሚያድሩ ሰዎችን ወደ ማቆያ ቦታ የመውሰድ ድርጊት ቀጥላል - ኢሰመኮ

አዲስ አበባ ውስጥ ጎዳና ላይ ውለው የሚያድሩ ሰዎችን በግዳጅ "የመያዝና ወደ ማቆያ ማእከላት የማስገባት ድርጊት አሁንም ቀጥሏል" ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ።

ብሔራዊው የመብቶች ድርጅት - ኢሰመኮ ታኅሣሥ 2017 ዓ.ም. አደረኳቸው ባላቸው ክትትሎች በአዲስ አበባ ቃሊቲ አካባቢ በሚገኝ "ሰፊ መጋዝን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን" መገንዘቡን ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።ኮሚሽኑ እንዳለው ወደ ማቆያው ከገቡት ሰዎች መካከል ምርጫ ተሰጥቷቸው "በተለያዩ አካባቢዎች ወደሚገኙ እርሻ ጣቢያዎች ተወስደው  እንዲሠሩ እንደሚደረግ" በክትትሉ መረዳቱን አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዲስ አበባ ውስጥ የሚከናወኑ ትልልቅ ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላትን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን ጠብቆ በጎዳና ውለው የሚያድሩ ሰዎችን በግዳጅ የማፈስ እና ወደ ማቆያ ቦታ የመውሰድ ድርጊት እንዲቆም ጠይቋል። ኢሰመኮ ይህ ድርጊት እንዲቆም ከዚህ በፊት ቢጠይቅም ባለፈው ወር ባደረገው ክትትል ድርጊቱ አሁንም መቀጠሉን መገንዘቡን ትናንት ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

በተቋሙ የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር የሆኑት ርግበ ገብረሐዋሪያ በዚሁ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ይህ ድርጊት ከዚህ ቀደምም ተስተውሏል ብለዋል።


«ከሕግ አሰራር ውጪ ለወታደራዊ ምልመላ ተይዘው ገንዘብ ተጠየቁ» ኢሰመኮኢሰመኮ "ወደ ማቆያው ከገቡት ሰዎች መካከል በማእከሉ ከመቆየት እና የእርሻ ሥራ ከመሥራት እንዲመርጡ በማድረግ፤ የእርሻ ሥራ ለመሥራት የመረጡ ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች ወደሚገኙ እርሻ ጣቢያዎች ተወስደው  እንዲሠሩ እንደሚደረግ መገንዘቡንም ገልጿል። ኢሰመኮ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ከሚያደርገው ውትወታ ጎን ለጎን ውይይቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በማድረግ ጉዳዩን በመከታተል ላይ መሆኑንም አሳውቋል።


ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ወደሚገኙ የግል የእርሻ ጣቢያዎች የተወሰዱ ሰዎች ክፍያ እየተከፈላቸው እንደሚሰሩ ከመግለጽ በቀር የእርሻ ማዕከላቱን ሥም ይፋ ከማድረግ ተቆጥቧል።

በመንግስት የጸጥታ ሐይሎች የሚካሄድ እገታ ማቆሚያው የት ነው?የኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ "በቀጣይ ከሚዘጋጁ የአደባባይ በዓላት እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ ስብሰባዎች ጋር በተያያዘ ጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ በመሆኑ፣ ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎችን በግዳጅ ወደ ማቆያ ማእከል ወይም ቦታ አስገብቶ መያዝ ወይም ያለፈቃዳቸው ወደተለያዩ አካባቢዎች መውሰድ ወይም እንዲሄዱ ማስገደድ የነጻነት መብት እና ከቦታ ቦታ በነጻነት የመንቀሳቀስን ጨምሮ ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ስለሚያስከትል በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል" ማለታቸው በመግለጫው ተካቷል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW