1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የወደብ ሃሳብ ሰዎች ምን አሉ?

ሰኞ፣ ጥቅምት 5 2016

ኢትዮጵያ የምትገለገልበት ወደብ የማግኘት ጉዳይ መሠረታዊ መሆኑን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ ይሁንና ጉዳዩ በቀላሉ ሊሳካ የሚችል ነው ብለው አያምኑም ።ከ30 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ይህንን ወደብ የማግኘት መብቷን ማጣቷን የገለፁ አስተያየት ሰጪ ጉዳዩ አሁን መነሳቱ አሁን ወቅቱ ነው ወይ የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ እንዳደረጋቸውም ገልፀዋል።

ፎቶ ከማኅደር፤ የጅቢቲ ወደብ
ኢትዮጵያ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የጅቡቲን ወደብ በከፍተኛ ክፍያ እየተጠቀመች ትገኛለች። ፎቶ ከማኅደር፤ የጅቢቲ ወደብምስል AP

በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ «የኢትዮጵያ የወደብ ፍላጎት» የተሰጡ አስተያየቶች

This browser does not support the audio element.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀይ ባሕር እና በአካባቢው ካሉ ወደቦች የባሕር በር የማግኘት መብቷ እንዲረጋገጥ ጉዳዩ የሕዝብ መወያያ እንዲሆን ሰሞኑን ያቀረቡት ሀሳብ ብዙ እያነጋገረ ነው። "የቀይ ባሕር ጉዳይ በደንብ ንግግር ያስፈልገዋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ቀይ ባሕር እና ዓባይ ኢትዮጵያን የሚበይኑ፣ ከኢትዮጵያ የተቆራኙ፣ ለኢትዮጵያ እድገትና ጥፋት መሠረት ናቸው" ሲሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ተናግረው ነበር።አሰብ ደርሶ መልስ ይህንን ለማሳካት አካሄዱ "በተቻለ መጠን በሰላማዊ መንገድ" መሆን እንዳለበት ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፌደሬሽን፣ ኮንፌደሬሽን ወይም የመሬት ልውውጥ አማራጭ የውኃ በር ማግኛ አማራጮች መሆናቸውን ዘርዝረዋል። 
ኢትዮጵያ የምትገለገልበት ወደብ የማግኘት ጉዳይ መሠረታዊ መሆኑን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ ይሁንና ይህ ጉዳይ በቀላሉ ሊሳካ የሚችል ነው ብለው እንደማያምኑ ገልፀዋል።የኤርትራ አፋሮች ጥሪና የፖለቲካ ጥያቄ
ከ30 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ይህንን ወደብ የማግኘት መብቷን ተገቢ ባልሆነ መንገድ ማጣቷን የገለፁ አንድ አስተያየት ሰጪ ይህ ጉዳይ አሁን መነሳቱ አሁን ወቅቱ ነው ወይ የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ እንዳደረጋቸውም ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የተወሰኑ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ሀሳባቸውን ጠይቀናቸዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀይ ባሕር እና በአካባቢው ካሉ ወደቦች የባሕር በር የማግኘት መብቷ እንዲረጋገጥ ጉዳዩ የሕዝብ መወያያ እንዲሆን ሰሞኑን ያቀረቡት ሀሳብ ብዙ እያነጋገረ ነው። "የቀይ ባሕር ጉዳይ በደንብ ንግግር ያስፈልገዋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ቀይ ባሕር እና ዓባይ ኢትዮጵያን የሚበይኑ፣ ከኢትዮጵያ የተቆራኙ፣ ለኢትዮጵያ እድገትና ጥፋት መሠረት ናቸው" ሲሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ተናግረው ነበር።ምስል DW/J. Jeffrey

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW