1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሳ ሽማግሌዎች ስለ አፋሩ ጥቃት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 18 2013

የኢሳ ብሄረሰብ ሽማግሌዎችን በመወከል አቶ መሀመድ ሙሴ በሁለቱ ክልል አጎራባች አካባቢ በአፋር ልዩ ኃይል ተፈፀመ ባሉት ጥቃት አስራ ሰባት ያህል ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡አስተያየት ሰጭው በትናንትናው ዕለት  በጥቃቱ የሞቱ ሰዎችን ለመቅበር እየተካሄደ ከነበረው ስነ ስርዓት ወቅት ማንነታቸው ያልታወቁ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ጠቁመዋል፡፡

Karte Äthiopien Afar-Region

«በጥቃቱ ከ17 በላይ ሰዎች ተገድለዋል»የኢሳ ሽማግሌዎች 

This browser does not support the audio element.


በአፋር እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት ከአስራ ሰባት በላይ ሰዎች መሞታቸውን የሶማሌ ክልል ኢሳ ማህበረሰብ ሽማግሌዎች ገለፁ፡፡ የአፋር ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በበኩሉ ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ በንፁሀን ላይ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ስምንት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ብሏል። የኢሳ ብሄረሰብ ሽማግሌዎችን በመወከል ለDW አስተያየት የሰጡት አቶ መሀመድ ሙሴ በሁለቱ ክልል አጎራባች አካባቢ በአፋር ልዩ ኃይል ተፈፀመ ባሉት ጥቃት አስራ ሰባት ያህል ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡አስተያየት ሰጭው በትናንትናው ዕለት  በጥቃቱ የሞቱ ሰዎችን ለመቅበር እየተካሄደ ከነበረው ስነ ስርዓት ወቅት ማንነታቸው ያልታወቁ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን ጠቁመዋል፡፡የአፋር ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ካሎይታ በበኩላቸው ለDW በስልክ በሰጡት መረጃ መሠረት ሽብርተኛ ያሏቸው አካላት በፈፀሙት ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ስምንት ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል፡፡በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት ገዳማይቱ በሚባለው ከተማ ከትምህርት ሚንስቴር የተላኩ ባለሞያዎች መገደላቸውን የተናገሩት አቶ አህመድ ተደጋጋሚ ጥፋት በአካባቢው እየተከሰተ መሆኑን ጠቅሰው ጥፋት ሰርተው የሚሸሸጉ አካላትን ህብረተሰቡ ማጋለጥ ይገባል ብለዋል፡፡በሁለቱ ክልል አዋሳኝ ቀበሌዎች በየጊዜው የሚቀሰቀስ ግጭት ለበርካታ ሰዎች ኅልፈት ምክንያት መሆን ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ የፌደራልም ሆነ የክልላቱ መንግስታት ችግሩን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል መፍትሄ አለማድረጋቸው ለችግሩ መቀጠል ምክንያት ነው የሚሉ አስተያየቶች ይሰነዘራሉ፡፡
አሁን ደረሰ የተባለውን ድርጊት አንዱ ባንዱ ከማሳበብ ባለፈ ፈፃሚዎችን በሚመለከት በቁጥጥር ስር የዋለ አካል የለም የአፋር ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን መሰል ጥፋቶች የሽብር ጥቃት በመሆናቸው በመከላከሉ ላይ የመሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

መሳይ ተክሉ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW