1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጥብቁ የካፋ ደን ላይ ያንዣበበው ስጋት መፍትሔ ይኖረው ይሆን?

ማክሰኞ፣ የካቲት 11 2017

ኢትዮጵያ አለኝ የምትለው እና በዓለም ላይ ከፍተኛ የብዝኃ ህይወት ክምችት ካለባቸው በደርዘን ከሚቆጠሩ ስፍራዎች አንዱ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የሚገኘው የከፋ ጥብቅ ደን አንዱ ነው። በዓለማቀፉ የሳይንስ እና የባህል ተቋም የተመዘገበው የከፋ ጥብቅ ደን በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ገፊ ምክንያቶች ፈተና ተጋርጦበታል።

የካፋ ጥብቅ ደን
ኢትዮጵያ ውስጥ ጥብቅ የተፈጥሮ ደኖች ብቻም አይደሉ ለአደጋ የተጋለጡት ። በተለያዩ ጊዜያት ሆን ተብሎም ሆነ በሌላ ምክንያት በሚነሳ የሰደድ እሳት ለውድመት የሚዳረገው ደን ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። ምስል፦ Mahlet Fasil Desalegn/DW

የከፋ ጥብቅ ደን ከአስር ዓመት የዩኔስኮ ምዝገባ በኋላ የት ነው ?

This browser does not support the audio element.

የካፋ ጥብቅ ደን ከትናንት ዛሬ

ኢትዮጵያ አለኝ የምትለው እና በዓለም ላይ ከፍተኛ የብዝኃ ህይወት ክምችት ካለባቸው በደርዘን ከሚቆጠሩ ስፍራዎች አንዱ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የሚገኘው የከፋ ጥብቅ ደን  አንዱ ነው። በዓለማቀፉ የሳይንስ እና የባህል ተቋም በእንግሊዘኛ ምህጻሩ ዩኔስኮ የተመዘገበው የከፋ ጥብቅ እና የብዝኃ ህይወት ደን በሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ገፊ ምክንያቶች ፈተና ተጋርጦበታል።

በዛሬው የጤና እና አካባቢ ዝግጅታችን በዓለማቀፉ የሳይንስ እና የባህል ተቋም የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች መዝገብ ስሙ የሰፈረው የከፋ  ጥብቅ ደን አስር ዓመት ሲደፍን በምን ፈተና ውስጥ እያለፈ ይሆን ስንል እንጠይቃለን ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካለው የቆዳ ስፋት ወደ 1.4 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆነው በደን የተሸፈነ ነው። ከዚህ ውስጥ ከአንድ ሶስተኛው በላይ የሚሆነውን የሚሸፍነው የካፋ ጥብቅ ደን ሲሆን አምስት ሺ ገደማ የዕጽዋት ዝርያዎች መገኛም ነው። ደኑ በጉያው ካቀፈው ውድ የተፈጥሮ ሀብት ውስጥ አስራ ሰባቱ ብርቅዬ እና በሌላ የዓለም ክፍል የማይገኙ የዕጽዋት ዝርያዎች መሆናቸው ተመዝግቧል። የካፋ የጫካ ቡና መገኛም በዚሁ ምድር መሆኑን ልብ ይሏል። 

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካለው የቆዳ ስፋት ወደ 1.4 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆነው በደን የተሸፈነ ነውምስል፦ Mahlet Fasil Desalegn/DW


አቶ ለማ ገብረ ሚካኤል ይባላሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የደን አካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ ምትል እና የደን ዘርፍ ኃላፊ ናቸው ። በክልሉ ከሚገኘው የደን ሽፋን ውስጥ በከፋ እና በሸካ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ እና በዓለማቀፉ የሳይንስ እና የባህል ተቋም ዩኔስኮ የተመዘገቡ ደኖች አስር ዓመት ማስቆጠራቸውን ተከትሎ በደን ይዞታ ጥበቃ እና አስተዳደራቸው ላይ የክለሳ ጥናት መደረጉን ያነሳሉ። 
ሕገወጥ የደን ወረራ በደቡብ ክልል
`` ሁለቱም ደኖች በዩኔስኮ ከተመዘገቡ ከአስር ዓመት በላይ ስለሆናቸው እንደገና የክለሳ ስራ እየሰራን ነው። ያለው ደን በምን አይነት ሁኔታ ቀነሰ ጨመረ የሚለውን ዉጤቱን ይፋ እናደርጋለን። ያው ዩኔስኮ ላይም ሲለሚቀርብ ፤ እዚያ ላይ ይቀርብ እና ደኑ ምን ያህል ኮር ፣ በፈር እና ትራንዚሽን ተብሎ የሚከፈል ነው ። ስለዚህ ምን ያህል መቀነስ ወይም መጨመር አለ የሚለው ይታያል።`` 
 ኃላፊው እንደሚሉት በጥናቱ ጎልተው ከታዩ እና ጥብቅ የተፈጥሮ ደኑን ለአደጋ ካጋለጡ ጉዳዮች የከተሞች መስፋፋት እና የህዝብ ቁጥር መጨመር ቀዳሚ ተጠቃሾች መሆናቸውን ነው።
`` የከተማ መስፋፋት አንደ ችግር የታየ ነገር ስለሆነ አሁን ከተማነትን ማስፋፋት እንደ ዕቅድ ተይዞ የሚሰራ ነገር ነው። እርሱም ቀድሞ በነበረው የደን ሃብት ላይ የሚያሳድረው ጫና አለ። ሁለተኛው የህዝብ ቁጥር እየጨመረ መምጣት ነው። የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ ወጣቱ ለእርሻም ለመኖሪያ ቤትም ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል ቦታ ይፈልጋል። ሰፋ ያለው አካባቢ የተያዘው በደን ስለሆነ ወደ ደን የመግባት አዝማሚያም ይታያል``

የከተማ መስፋፋት አንደ ችግር የታየ ነገር ስለሆነ አሁን ከተማነትን ማስፋፋት እንደ ዕቅድ ተይዞ የሚሰራ ነገር ነውምስል፦ Lema Gebre Mikael, Dr. Girma Kalboprivat


አቶ ክፍሌ መሸሻ የአካባቢው ተወላጅ ምሁር እና የቦንጋ ከተማ ነዋሪ ናቸው ። የከተሞች መስፋፋት እና ተያያዥ ችግሮች ጥብቅ የተፈጥሮ ደኑን ለአደጋ ማጋለጣቸው አሳስቧቸዋል። ችግሩ ወደ ከፋ የአየር ንብረት ለውጥ እንዳያመራም ነው ስጋታቸውን የገለጹት ።

``ትናንት እንደ ጥብቅ ደን ስናያቸው የነበሩ አካባቢዎች ወደ ከተማነት የተቀየሩበት አግባብም አለ። በዚሁ ልክ ዛሬ እንደ ጫካ የምንያቸው ወይም ተጠብቀው ያሉ አካባቢዎች አሁንም ከተማ በሰፋ ቁጥር  መመናመኑ የሚቀር አይመስልም። ዞሮ ዞሮ ዛሬ ያለውን የአየር ንብረት የምናየው ነው። ነገ ደግሞ ከዚህ የባሰ በረሃማነትም ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋትም አለ።``
በዓለማቀፉ የሳይንስ እና ባህል ተቋም ዩኔስኮ በተፈጥሯዊ ቅርስነት ከተመዘገበ አስር አመታትን ያስቆጠረው የካፋ ሸካ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን ያለበት ሁኔታ የግምገማ ጥናት መካሄዱን የክልሉ የደን አካባቢ ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ አስታውቋል። ነገር ግን በሀገሪቱ የቀጠለው የጸጥታ ችግር አሉታዊ ተጽዕኖ ካሳደረባቸው መስኮች አንዱ ጥብቅ የተፈጥሮ አካባቢዎች በህገ ወጥ ወረራ እና እንዲጋለጡ ማድረጉ ነው። በሰው ሰራሽም ሆነ በተፈጥሯዊ ምክንያቶች በጥብቅ ላይ የሚደርሰው ውድመት እና ለአደጋ መጋለጥ የተፈጥሮ አካባቢን ለአደጋ ከማጋለጥ አልፎ ከአለምአፉ የቅርስ መዝገብ ሊሰረዝ የሚችልበትን ዕድል ማስከተሉ እንደማይቀር የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ ። 

 

የሁሉንም ተሳትፎ የሚሻዉ የአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃ
ዶ/ር ግርማ ቀልቦሬ ነዋሪነታቸው እዚህ ጀርመን ቦን ከተማ ነው። በደን ላይ በሚሰራ ዓለማቀፍ ድርጅት ውስጥ ይሰራሉ። በሀገር ቤት እና ከሀገር ከወጡ በኋላ በአጠቃላይ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ በደን ሃብት ጥበቃ እና እንክብካቤ ላይ ጥናቶች ሰርተዋል።  ኢትዮጵያ ውስጥ በደን ጥበቃ እና ክብካቤ ዙርያ ከፍተኛ ትኩረት ሊያገኝ እንደሚገባ ይጠቁማሉ ። ምክንያታቸው ደግሞ በዓመታት ሂደት ከምንግዜውም ይልቅ የደን ሃብት ለችግር የተዳረገበት ጊዜ ላይ በመድረሱ መሆኑ ነው።

 ኢትዮጵያ ውስጥ በደን ጥበቃ እና ክብካቤ ዙርያ ከፍተኛ ትኩረት ሊያገኝ ይገባልምስል፦ Lema Gebre Mikael, Dr. Girma Kalboreprivat



`` በጣም አጥብቆ ማየት ያስፈልጋል ፤ ይሄ ደን በዓለም ደረጃ የታወቀ ነው። የብዝኃ ህይወት እንደገና ደግሞ 
እንደ ዶ/ር ግርማ በቅርስነት የተመዘገቡ የተፈጥሮም ይሁን ሰው ስራሽ ቅርሶች ለአደጋ በሚጋለጡበት ሂደት ከቅርስ ጥበቃ እና እንክብካቤ መዝገብ ውስጥ መሰረዝን የሚaseከትሉ ሁኔታዎች ሊፈጠሩ የሚችሉበት ዕድል መኖሩ መዘንጋት የለበትም ባይ ናቸው። 
``ዩኔስኮ የመዘገባቸውን  ባይስፈር ክልሎች በመየመሃሉ ግምገማ ያካሂዳል። ያሉበት አጠባበቅ ምን ይመስላል፤ ምን ጉድለቶች አሉ ፤ ከፍተኛ ናቸው ወይ ፤ መካከለኛ ናቸው ወይ፤ ወይስ በቀላሉ የሚፈቱበት ሁኔታ ነው ያለው የሚለው ታይቶ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን በማየት ሊስተካከል የማይችሉበት ሁኔታ ከተገኘ ሊሰረዙ የሚችሉበት ሁኔታ ስላለ አደጋ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ``
የአካባቢው ተወላጅ ምሁሩ አቶ ክፍሌ በተለይ የከፋ ጥብቅ ደን ህልውና ተጠብቆ እንዲዘልቅ የማህበረሰቡ የቆየ ደንን የመንከባከብ ባህል እንዲጠናከር ማስቻል አንደኛው መፍትሄ ነው ይላሉ ። ምንም እንኳ የከተሞችን መስፋፋት እንዲሁ በቀላሉ መግታት የማይቻል ቢሆንም ።

ለደን ጥበቃ የኅብረተሰብ ተሳትፎ
``የአየር ንብረት ለውጥ ጭምር በከተማ መስፋፋት ሊሆን ይችላል፤ ሰዎች ለእርሻ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተንቀሳቅሰው በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሊሆን ይችላል የሚመናመነው ፤ ስለዚህ መንግስት የራሱ የሆነ መዋቅር አለው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም አሉ  በዚሁ ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ ፤ የአካባቢ ጥበቃ አለ። ስለዚህ የመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ይህን የህዝብ ደንን በራሱ የመጠበቅ ባህል መልሶ እንዲያገግም እና ከዚሁ የአየር ንብረት ለውጥ ራሳችንን መታደግ ብንችል የተሻለ ነው  ``
ኢትዮጵያ ውስጥ ጥብቅ የተፈጥሮ ደኖች ብቻም አይደሉ ለአደጋ የተጋለጡት ። በተለያዩ ጊዜያት ሆን ተብሎም ሆነ በሌላ ምክንያት በሚነሳ የሰደድ እሳት ለውድመት የሚዳረገው ደን ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ለውድመት የሚዳረግ ደን ጉዳቱ ለጋራ ነው። ለዚያዉም በዓለም አቀፍ ደረጃ የከፋ የአየር, ንብረት ለውጥ እየታየm ባለበት በዚህ ጊዜ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ከጎርፍ ፣ ድርቅ እና ረሃብ ጋር ተለማምደው የቆዩ ሃገራት ያላቸውን ማስጠበቅ ባለመቻላቸው ብቻ የችግር እና የመካራ ዘመናቸውን ለማስረዘም ይገደዳሉ ።

የተዛመተው የደን ቃጠሎ በኢትዮጵያ

ጉዳዩ ዓለም አቀፍ ርዳታዎች እየተቋረጡ እና ራስን መቻል አስገዳጅ እየሆነ የመጣበት ጊዜ መሆኑ ደግሞ ትኩረቱ ከፍ ማለቱ የግድ ይሆናል። ዶ/ር ግርማ ለዚህ መፍትሄ የሚሉትን ሃሳብ ሲያጋሩ ፤ መፍትሄው በራስ እጅ ነው ያለው ፤ እርሱም ተቀናጅቶ መስራት ነው።
``አካባቢን በመጠበቅ ብቻ ሊገኝ የሚችለውን ጥቅም ራሱ እያጣን ነው ያለነው ማለት ነው። መኖሩ ራሱ ጥቅም የሆነ፤ ስለዚህ የተለያዩ የልማት እና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ አቅጣቻዎችን በማቀናጀት ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት በመስራት የተለያዩ አካላት አንድ ላይ ቢተባበሩ ለውጥ ማምጣት ይቻላል። ``ነዋሪዎችን ቅር ያሰኘው በዎላይታ ዞን ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ መክፈያ በሚል ለግለሰቦች ተሽጧል የተባለው ጥብቅ ደን ጉዳይ

እንደ ካፋ የብዝኃ ህይወት ጥብቅ ደን ያሉ ተፈጥሯዊ ሃብቶች የብዝኃ ህይወትን ከማስቀጠል ባሻገር ለካርቦን ልቀት መቀነስ የሚኖራቸው ፋይዳ መተኪያ የለውም ። የክልሉ የደን እና የተፈጥሮ ሃብት ምክትል ሃላፊ አቶ ለማ ገብረሚካኤል እንደሚሉት የአካባቢው ማህበረሰብ ደኑን ሳይጎዳ እያለማ የሚጠቀምበት ብሎም በተንከባከው ልክ የሚገባውን ካሳ የሚያገኝበት መርሃ ግብር መዘርጋት ለነገ የማይባል ነው። ማህበረሰቡን በመከልከል አልያም በማግለል ብቻም ደኑን ማስጠበቅ አይቻልምና ።
`` ህዝቡ ያንን ደን የጠበቀበትን ክፍያ እንዲከፈለው መስራት ካልተቻለ በርግጥ በክልከላ በች ወይም በመጠበቅ ብቻ ላይሆን ይችላል። ለዚህ ደግሞ ወደ ዩትላይዜሽን እናስገባለን የሚል ሃሳብ አለ። ደኑንም ወደ ሌሎች እንደስትሪዎች ውስጥ አስገብተን ወጣቱ በዚያ ውስጥ መሳተፍ የሚችል ከሆነ ነው የተወሰነ ሊራመድ የሚችለው ``
ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW