1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጦርነቱ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው የሚደገፉበት ስምምነት

ሐሙስ፣ ሰኔ 15 2015

በኢትዮጵያ ባለፉት 3 አመታት በነበረው ጦርነት ምክንያት የፆታ ጥቃት ለተፈፅመባቸው አካባቢዎች እርዳታ የሚውል ከዓለም ባንክ በተገኘ ግ የ300 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ተጎጂዎችን የሚያግዝ የትብብር ስምምነት ተፈረመ ።

Äthiopien Addis Abeba PK UNICEF Programm Konfliktregionen
ምስል Hanna Demssie/DW

 የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር ያደረገው ስምምነት

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያ ባለፉት 3 አመታት በነበረው ጦርነት ምክንያት የፆታ ጥቃት ለተፈፅመባቸው አካባቢዎች  እርዳታ የሚውል ከዓለም ባንክ በተገኘ ግ የ300 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ተጎጂዎችን የሚያግዝ የትብብር ስምምነት ተፈረመ ። በስምምነቱ   የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ፣ ዓለማቀፉ የሕጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ እና  ጂፒጎ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በጋራ በመሆን የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎችን የሚያግዙ የልማት ስራዎች በጋራ መስራት ያስችላቸዋል ተብሏል። በጦርነቱ ብርቱ ጉዳት ባስተናገደው  የትግራይ ክልል የጉዳቱን ሰለባዎች የሚያግዙ ስራዎች በይፋ መጀመራቸው በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል

  
የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ መንግስት የሰጠው  የገንዘብ እርዳታ  በአጠቃልይ 300 ሚልየን የአሜሪካን  ዶላር ስምምነት ሲሆን  እርዳታው  በኢትዮጵያ በግጭት መክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን 5 አካባቢዎች መልሶ ለማልማት እና  የ መሰረተ ልማት ውድመት የደረሰባቸው ክልሎች   መልሶ ለማቋቋም   የሚውል ነው።  ፕሮጀክቱ ለ 5 አመት የሚቆይ ነው ተብሏል ፣
ለዚህ ፕሮጀክት ለ 5 ቱ ክልልሎች የፆታ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እና ህፃናት ለመርዳት በአጠቃላይ የተመደበው 70 ሚልየን የአሜሪካን ዶላር ሲሆን በግጭቱ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል የተባለው የትግራይ ክልል አብላጫው ድርሻ ተመድቦለት ስራው  ተጀምሮዋል  ሲሉ ለDW የተናገሩት  አቶ ወንድሙ ዱታሞ በሴቶች እና ማህበራዊ ሚንስቴር የፕሮጀክቱ አስተባባሪ  ናቸው።
በጦርነቱ ምክንያት ከፍተኛ የሰው እና የንብረት ውድመት የደረሰባቸው የትግራይ፣  አማራ ፣አፋር ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች  የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ፤ ከየክልሎቹ በተመረጡ 70 ወረዳዎች ቅድሚያተሰጥቶ የሚሰራ እንደሆነ ተናግረዋል ።  የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር  ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ   ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የጾታ ጥቃት የደረሰባቸውን የህብረተሰቡን ክፍሎች፣ ሴቶች እና ህፃናትን ለመርዳት የአጭር እና የመካከለኛ ግዜ እቅድ በማውጣት እየተሰራ ነው ሲሉ በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት ተናግረዋል።
ዶ/ር ኤርጎጌ  አክለው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቦታው ላይ ገብቶ መስራት የሚያስችለው ሁኔታ እስከሚመቻች ድረስ  ከክልሉ ግዜያዊ መስተደድር ጋር በመሆን እስካሁን የተሰሩትን ስራዎች የሚገመግም ይሆናል  ብለዋል።
ዛሬ በኢትዮጵያ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሰቴር   ከዩኒሴፍ ምክትል ዳይሬክተር ሚስተር ዳውዳ ጉኒዶ  ጉዳቱ በደረሰባቸው አካባቢዎች ያለውን የዳሰሳ ጥናት ከሚያካሂደው የጂፒጎ  የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር በመሆን የተፈራረሙት የእርዳታ ስምምነት በጦርነት ወቅት ጾታዊ ጥቃት ስለተፈፀመባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የሚደርገውን  ድጋፍ በቀጥታ  የሚያጠነክር እና   የአንድ  ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ያለውን ጥረት የሚያግዝ ይሆናል ተብሏል ።

ሃና ደምሴ

ታምራት ዲንሳ 

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW