1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች የገንዘብ ማሰባሰቡ መርሃግብር

ሰኞ፣ መስከረም 30 2015

በሰሜን ኢትዮጵያ በሚካሄደው ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አጣዳፊ ሕይወት አድን ሕክምና ለመስጠት የሚያስችል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ካናዳ ውስጥ ተካሄደ። ኢክናስ ካናዳ እና ሰዎች ለሰዎች ማለትም ፒፕል ቱ ፒፕል የተባሉ ድርጅቶች በጋራ ባካሄዱት የበይነ መረብ ዝግጅት፣ እስካሁን 117 ሺህ ዶላር የሚደርስ ገንዘብ መሰባሰቡ ተገልጿል።

Äthiopien | Teile der Amhara-Region nun unter Kontrolle der Regierung
ምስል፦ Waghemra Communication office

በበይነ መረብ የተካሄደ የድጋፍ ማሰባሰቢያ

This browser does not support the audio element.

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ፣ ኢትዮጵያ ካናዳውያን የሕክምና ባለሙያዎች፣ የሕክምና ዕርዳታ ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በልገሳ የተገኙና በጣም አስፈላጊ የተባሉ የሕክምና ቁሳቁሶችን በጦርነቱ ለወደሙ የጤና ተቋማት አቅርበዋል። በሰሜን አሜሪካ የሚገኙና ይህንን ዓላማ ለማስፈጸም የጋራ ራዕይ ያነገቡት ባለሙያዎቹ፣ በቅርብ ጊዜም ተመሣሣይ ተልዕኮዎችን፣ በኢትዮጵያ ቀጥለዋል። በዚህ ተልዕኮም፣ በጦርነቱ ምክንያት በሕይወት የተረፉ በርካታ ሰዎች የእግርና የእጅ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የሕክምና ቡድኑ፣ በቦታው ከሚገኙ የቀዶ ጥገና ሃኪሞች ጋር ባደረገው ውይይት፣ አንድን ተጎጂ ለመጠገን 10 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ወይም 200 የአሜሪካ ዶላር ያስፈልገዋል ተብሏል። በዚህም መሠረት ሁለት ሺህ የሚሆኑ የጦርነቱ ተጎጂዎችን የቀዶ ሕክምና ለመስጠት፣ 400 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለማሰባሰብ የሚያስችል ዘመቻ ባለፈው ቅዳሜ አካሄደው፣ እስካሁን 117 ሺህ  የሚደርስ ዶላር ለማግኘት ችለዋል። በበይነ መረብ በተካሄደው መርሐ ግብር ላይ የተገኙት፣የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ በጦርነቱና በተፈጥሯዊ ሁኔታዎች ምክንያት፣ ሃገሪቱ በርካታ ተግራቶችን እያለፈች መሆኑን ተናግረዋል።

«ሀገራችን በበርካታ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እያለፈች ነው። ጎን ለጎን እንደ ሃገር ብዙ የሚበረታቱ ለውጦች ቢኖሩም፤ብዙ ደግሞ ፈታኝ የሆኑ ችግሮች ማኀበረሰባችን እየተፈተነበት በተለይም ከጦርነቱ አኳያ ሌሎችም ተፈጥሯዊ የሆኑ ችግሮች ጨምሮ ብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ እያለፍን ነው። ያንን ለማለፍ ግን ብዙ አቅም እንዳለና፣ በተለይ ያለው ቁርጠኝነት በዳስፖራ በተለያዩ ሀገር በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እያሳዩ ያለው ቁርጠኝነት እና መስዕዋት ሆኖ መሥራቱ በጣም ትልቅ አቅም ነው የሆነን።»

በጦርነቱ የወደመ ምስል፦ AFP via Getty Images

በካናዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ በበኩላቸው፣ የዕርዳታ ማሰባሰብ መርሐ ግብሩን ላካሄዱት ድርጅቶችና ግለሰቦች ምስጋና አቅርበዋል።

«ድር ቢያብር አንበሳ ያስር በሚል በሰሜን አሜሪካ ማለትም በካናዳና አሜሪካ የሚገኙ በሌሎችም አህጉሮች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለይም ደግሞ ኢክናስ የኢትዮጵያ ካናዳ ኔትዎርክ በአጭር ጊዜ ተቋቁሞ፣አንጋፋ ተቋማት የሚያከናውኑትን ሥራ እየሰራ በመሆኑ፣አመራሩ መላ ቻኘተሩና አባላትን አሜሪካም በነበርኹበት ጊዜ እንቅስቃሴያቸውን ስለማውቅ ከልብ ላመሰግን እፈልጋለሁ።» በተጨማሪም ፒፕል ቱ ፒፕል ከኤች አይ ቪ ጀምሮ ሲሰራ የነበረ እና ከሁለት አስርተ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ አንጋፋ ማኀበር መሆኑን አስታውሰዋል። በገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻው የሚገኘው ድጋፍ፣ሀገር ቤት በሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በኩል በቀጥታ ለተጎጂዎቹ እንደሚደርስና፣ በምን መልኩም እንደዋለም  ተመልሶ ዕርዳታ ለሰጠው አካል የሚገለጽበት አሰራር መዘርጋቱ ተገልጿል።

ታሪኩ ኃይሉ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋኅ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW