1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጦርነት ስለተፈናቀሉ ዜጎች የፌደራል የአደጋ ስጋት የሰጠዉ ምላሽ 

ማክሰኞ፣ ጥር 24 2014

በሰሜን ኢትዮጲያ በተካሄደው ጦርነት በአማራ ክልል ተፈናቅለው ከነበሩት ነዋሪዎች መካከል አብዛኞቹን ወደቀደመ ቦታቸው የመመለስ ስራ መከናወኑን የፌደራል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ገለፁ። በጦርነቱ በአማራ ክልል ተፈናቅለው ከነበሩት 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተፈናቃዮች መካከል እስከአሁን 1 ነጥብ 2 ሚሊዮኑን ወደ ቀያቸዉ ተመልሰዋል።

Äthiopien Mituku Kassa DW-Interview
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ

This browser does not support the audio element.

በሰሜን ኢትዮጲያ በተካሄደው ጦርነት በአማራ ክልል ተፈናቅለው ከነበሩት ነዋሪዎች መካከል አብዛኞቹን ወደቀደመ ቦታቸው የመመለስ ስራ መከናወኑን የፌደራል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነሩ ገለፁ።

ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በተለይ ከዶቼ ቬለ (DW) ጋር በሀዋሳ ባደረጉት ቃለ ምልልስ በጦርነቱ በአማራ ክልል ተፈናቅለው ከነበሩት 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተፈናቃዮች መካከል እስከአሁን 1 ነጥብ 2 ሚሊዮኑን ወደ ቀደመ ቦታቸው ለመመልስ ተችሏል ብለዋል ።

ካለፈው ሳምንት አንስቶ በአፋር አንዳንድ ወረዳዎች ህወእት አየፈጸመ ይገኛል ባሉት ትንኮሳ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ለመቆም መገደዳቸውን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ የአካባቢው የሰላም ሁኔታ  ባለመሻሻሉ የተሽከርካሪዎቹ ጉዞ አሁን ድረስ ተስተጓጉሎ እንደሚገኙም ኮሚሽነር ምትኩ ተናግረዋል።

 ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW