1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጦርነት የታጀበዉ የሩስያ የድልቀን አከባበር

ማክሰኞ፣ ግንቦት 1 2015

ሩሲያ የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት በሁለተኛው ዓለም ጦርነት በናዚ ጀርመን ላይ ድል የተቀዳጀችበትን «የድል ቀን» ዛሬ አክብራለች። የዘንድሮው በዓል ሩስያ ከዩክሬን ጋር በገባችበት ጦርነትና በዚህም ምክንያት ከምራባውያን ጋር በተፈጠረው ከፍተኛ አለመግባብት፤ በአሉ በሩስያ በተለየ ሁኒታ እንድተከበረ ነው የሚነገረው።

Russland | Victory Day Parade
ምስል Gavriil Grigorov/Sputnik/Kremlin Pool Photo/AP

«ዩክሬን፤የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ አምባገነኖች የተወገዱበትን የድል በዓለ በተናትናው እለት አክብረዋል»

This browser does not support the audio element.

ሩሲያ የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት በሁለተኛው ዓለም ጦርነት በናዚ ጀርመን ላይ ድል የተቀዳጀችበትን «የድል ቀን» ዛሬ አክብራለች። ዛሬ ግንቦት አንድ በምዕራባውያን «ሜይ ዘጠኝ» የሩሲያና የአንዳንዶች የቀድሞ የሶቭየት ህብረት አካል የነበሩ አገሮች ጭምር ትልቁ ብሔራዊ የድል ቀን ነው። ናዚ ጀርመን አብዛኛውን አውሮፓን ተቆጣጥሮ በሩሲያ ላይ የከፍታውን መጠነ ሰፊ ጥቃት መክቶ ድል በማድረግ በኩል የያኔው የሶቭየት ህብረት ቀዩ ሰራዊት በሰፊው ይጠቀስል። ሶቭየቶች 27 ሚሊዮን ህዝብ መስዋዕት አድርገው የሁለተኛውን ዓለም ጦርነት ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በድል የቋጩበት ዕለት ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን፤  የያኔዋ ሶቭየት ህብረት ወራሽ  እንደሆነች የምትጠቀሰው ሩሲያ ዕለቱን በደማቅ ወታደራዊ ትርኢትና ብሔራዊ ስሜት በማክበር ትታወቃለች።

ይሁን እንጂ የዘንድሮው በዓል በተለይ ከዩክሬን ጋር በተገባበት ጦርነትና በዚህም ምክንያት ከምራባውያን ጋር በተፈጠረው ከፍተኛ አለመግባብት፤ በአሉ በተለየ ሁኒታ እንድተከበረ ነው የሚነገረው። ፕሪዝዳንት ፑቲንም በንግግራቸው፤ ከዩክሬን ጋር እየተደረገ ያለውን ጦርነትና በተለይም ምራባውያን ከ78 ዓመት በፊት በናዚ ጀርመን ላይ ድል ባስመዘገበችው ሩሲያ ላይ ጦርነት ያወጁ መሆኑን  በመግለጽ፤ ሶቭየቶች በሁለተኛ ዓለም ጦርነት ያስመዘገቡትን ወሳኝ ድል ምራባውያን ረስተውታል ሲሉም ተስምተዋል። ፑቲን በንግግራቸው በአሁኑ ወቅት በዩክሬን የሚካሄደውን ጦርነት ያኔ የናዚ ጀርመን ጦር ሶቭየት ህብረትን ከቦ ከነበረበትት ሁኒታ ጋር በማመሳሰል፤ ሩሲያ እንደተከበበችና የምታካሄድው ጦርነትም የመከላከል ጦርነት እንደሆነ፤ ለበአሉ ታዳሚዎችና ለዓለማቀፉ ህብረተስብ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል የአውሮፓ ኮሚሺን ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ቮን ደርላይን በዛሬው ዕለት በኪየቭ በመገኘት የአውሮፓን ቀን ከፕሬዝዳንት ዜለንስኪ ጋር አስበው ማዋላቸው ተገልጿል። የአውሮፓ ህብረት ቀን በየዓመቱ ሜይ ስምንት በተለይ በብራስልስ የሚከበር ሲሆን፤ ይህንን በአል ነው ዛሬ ፎንዴልር ላይን በኪየቭ ከዩኪሬኖች ጋር አስበው ውለዋል የተባለው። ዩክሬን የቀድሞ የሶቭየት ህብረት አካል ስለነበርች፤ ሶቭየቶች ያገኙትን ድል ከሌሎች የቀድሞ የሶቭየት ግዛቶች ጋር በየዓመቱ በሜይ 9 ስታከብር የነበር ቢሆንም፤ ከእንግዲህ ግን የድል ቀናቸውን ከአውሮፓውያን ጋር እንደሚያከብሩ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ተናግረዋል።

የአውሮፓ ኮሚሺን ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ቮን ደርላይን ከፕሬዝዳንት ዜለንስኪ ጋር በኪይቭምስል Valentyn Ogirenko/Reuters

ወይዘሮ ቮንደርላይን በዛሬው እለት ከኪየቭ ሰጡት በተባለው አስተይየትም፤  ዩክሬን፤ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ አምባገነኖች የተወገዱበትን የድል በዓለ በተናትናው እለት ሲያከብሩ፤ ሩሲያ ግን በሜይ ዘጠኝ በዩክሬን ከተሞችና ሲቭሎች ላይ ሚሳይሎችን በማዝነብ አክብረዋለች ማለታቸው ተዘግቧል። ሌሎች የህብረቱ አገሮች መሪዎችና ባለስልጣኖችም በሩሲያው የድል በአል አከባበርና የፕሬዝዳንቱ ንግግር ላይ የተለያዩ አስተያይቶችን ስተዋል። ከነዚህ ውስጥ የብርታኒያው የመከላከያ ሚኒስተር ቤን ዋላስ በዩክሬን ላይ ጦርነት አውጆ የድል ቀን የሚባል የለም በማለት ፕሬዝድንት ፑቲን ከገቡበት ጦርነት ሊወጡ የሚችሉበትን እንዲያስቡ ማሰሰባቸው ተሰምቷል።

የዘንድሮው የሩሲያ የድል በአል ከቀድሞውቹ በምንና እንዴት እንደሚለይ የኖርዌይ ደቡባዊ ምስራቅ ዩንቨርስቲ ፕሮፈሰር   የሆኑት ሚስተር ግሌን ዴሰን ሲገልጹ፤ “ ዋናው ከሌሎቹ የሚለይበት በአሁኑ ወቅት ሩሲያ ከዩክሬን ጋር በጦቶርነት ውስጥ መሆኗ ነው በማለት በዚህም ምክኒያት ብዙ ወታደራዊ ትርኢቶችና መሳሪያዎችም ሳያታዩ የቀሩ ይመስለኛል” ብለዋል፤ የጸጥታው ጥበቃም ከፍተኛ የነበር መሆኑን በመግለጽ ጭምር።

የበአሉ አከባበርና የተደረጉት ንግግሮች ከዩክሬን ጋር እየተካሄደ ባለው ጦርነት የሚፈጥረው አዲስ ነገር የሚኖር ስለመሆኑ ተጠይቀው ሲመልሱም፤ “ የድሉ ቀን በአልና አከባበሩ  የሚፈጥረው አዲስ ነገር አይኖሮም በማለት  ጦርነቱ ግን እንደሚቀጥልና ምናልባትም ዩክሬን ከባኽሙት ልትወጣና ሩሲያም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ጥቃት ልትጀምር ትችላለች ሲሉ አስተያየታቸውን ሰተዋል።

 

ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW