1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፈረንሳይ ቀኝ ጽንፈኛው ፓርቲ የመጀመርያ ዙር የፓርላማ ምርጫን አሸነፈ

ሰኞ፣ ሰኔ 24 2016

የአዉሮጳ ህብረት ምርጫ ውጤትን ተከትሎ በፈረንሳይ ትናንት በተካሄደዉ የመጀመርያ ዙር የምክር ቤት ምርጫ ናሽናል ራሊ» የተባለዉ ቀኝ ጽንፈኛ ፓርቲ አሸነፈ። ስደተኛ ጠሉ የቀኝ አክራሪዉ ፓርቲ አንዱ አመራር “ፈረንሳይዊያን ድምጻቸውን ከሰጡን የሁሉም ፈረንሳዊ ጠ/ሚ እሆናለሁ” ብለዋል።

ስደተኛ ጠሉ በማሪን ላፔን የሚመራዉ የፈረንሳዩ ቀኝ አክራሪዉ ፓርቲ የመጀመርያዉን ዙር ድል አረጋገጠ
ስደተኛ ጠሉ በማሪን ላፔን የሚመራዉ የፈረንሳዩ ቀኝ አክራሪዉ ፓርቲ የመጀመርያዉን ዙር ድል አረጋገጠምስል Yves Herman/REUTERS

የትግራይ ጦርነት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸዉ መመለስ ጀመሩ

This browser does not support the audio element.

በፈረንሳይ ቀኝ ዘመሙ ፓርቲ የመጀመርያ ዙር የፓርላማ ምርጫን አሸነፈ 

የአዉሮጳ ህብረት ምርጫ ውጤትን ተከትሎ በፈረንሳይ ትናንት በተካሄደዉ የመጀመርያ ዙር የምክር ቤት ምርጫ ናሽናል ራሊ» የተባለዉ ቀኝ ጽንፈኛ ፓርቲ አሸነፈ። የድምፅ ቆጠራዉ ተጠናቆ አሸናፊዉ እንደታወቀ፣ የፕሬዝዳንት ማክሮን ስብሰብ “ተጥረግርጎ ወጥቷል” ሲሉ ማሪን ለ ፔን ለደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል። የላፔን ፓርቲ እስከዛሬ አግኝቶት የማያዉቀዉን 33 በመቶ ድምፅ በማግኘት ነዉ የመጀመርያዉን ዙር ምርጫ ትናንት ያሸነፈዉ። ግራ ዘመሙ ጥምር ፓርቲ 28.1 በመቶ ድምፅ ማግኘቱ ይፋ ሆንዋል።

በሦስተኝነት ዉድድሩን ያጠናቀቀዉ የፕሬዚደንት ኢማኑዌል ማክሮ ፓርቲ ደግሞ 20 በመቶ ድምጽ ብቻ ማግኘቱን የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትቴር ዛሬ ይፋ ባደረገው ውጤት ተረጋግጧል። ቀኝ ጽንፈኛው የራሊ ናሽናል ፓርቲ ሌላዉ  አመራር ጆርዳን ባርዴላ “ፈረንሳይዊያን ድምጻቸውን ከሰጡን የሁሉም ፈረንሳዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እሆናለሁ” ብለዋል። በፈረንሳይ ታሪክ በፓርላማ ምርጫ ቀኝ ጽንፈኛ ፓርቲ አብላጫ ድምጽ  አግኝቶ አያውቅም።

ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ ሽንፈት ገጥሟቸዋል ምስል Dylan Martinez/Pool via AP/picture alliance

ይህ የፈረንሳይ ምርጫ የተደረገው ከታቀደለት ጊዜ ቀድሞ ነው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኤማኑኤል ማክሮ ተቀናቃኛቸው በአውሮጳ ኅብረት አገራት የፓርላማ ምርጫ ላይ ስኬት ማግኘታቸውን ተከትሎ የፈረንሳይ ፓርላማን በትነው አስቸኳይ ምርጫ መጥራታቸው ይታወሳል። በፈረንሳይ ፖለቲካ ውስጥ የማክሮ ተቀናቃኝ የሆኑት የማሪን ለ ፔን ቀኝ ጽፈኛ ናሽል ራሊ ፓርቲ በአውሮፓ የፓርላማ ምርጫ ስኬትን አስመዝግቧል። በአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ከፈረንሳዩ በተጨማሪ የጀርመን፣ የግሪክ፣ የፖላንድ እና የስፔን ቀኝ ዘመም ፓርቲዎች ስኬታማ መሆናቸው ይታወሳል። ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት በፈረንሳይ ስለተካሄደዉ የፓርላማ ምርጫ እና ዉጤቱ ከፓሪስዋ ወኪላችን ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገናል። 
ሃይማኖት ጥሩነህ / አዜብ ታደሰ 
ዮኃንስ ገብረእግዚአብሔር
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW