1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተፈናቃዮች ርዳታ

ሰኞ፣ መጋቢት 16 2011

ባሳለፍነው ቅዳሜ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ማሕበር ፓሪስ ላይ ተፈናቅለው ለረሃብ እና ችግር ለተጋለጡ የጌዲዮ ተወላጆች የርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄደ።  የጌዲዮ ሕዝብ መፈናቀል ብሎም በጊዜው በቂ ትኩረት እና ርዳታ አለማግኘቱን ተከትሎ ለከፋ ረሃብ እና እንግልት መዳረጉ የሰሞኑ መነጋገሪያ ጉዳይ ሆኖ ሰንብቷል።

Äthiopien Gedeb Binnenflüchtlinge aus West-Guji
ምስል picture-alliance/dpa/World Vision/Fitalew Bahiru

«የርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በፓሪስ»

This browser does not support the audio element.

እነዚህ ወገኖች ያሉበት ወቅታዊ ሁኔታ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ይፋ ከሆነ ወዲህም በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ወገኖች የርዳታ ማሰባሰብ ምላሽ እየሰጡ ነው። በፓሪሱ ልዩ የርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ በቅርቡ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሕይወታቸውን ያጡ የበረራ ሠራተኞች እና መንገደኞች በሻማ ማብራት ሥርዓት ታስበዋል። ሃይማኖት ጥሩነት ከፓሪስ ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች። 

ሃይማኖት ጥሩነት

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW