1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፈረንሳይ የስደተኞች የምግብ ዝግጅት ፌስቲቫል

ሐሙስ፣ ሰኔ 13 2011

የዓለም የስደተኞች ቀን በሚከበርበት በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ የስደተኞች የምግብ ዝግጅት ፌስቲቫል እየተካሄደ ይገኛል። ፓሪስን ጨምሮ በፈረንሳይ የተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ባለው ይሄው ዝግጅት ስለ ስደተኞች ያለውን የተሳሳተ አመላከት ለማስቀረት እና ምግብን እንደመግባቢያ ቋንቋ የመጠቀም ዓላማ አለው።

Deutschland Eid al-Fitr Fest Zuckerfest Mahnzeit
ምስል picture-alliance/dpa

በፈረንሳይ የስደተኞች የምግብ ዝግጅት ፌስቲቫል

This browser does not support the audio element.

"ፉድ ስዊት ፉድ" የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነው ድርጅት የስደተኞችን የምግብ ዝግጅት ፌስቲቫል በፈረንሳይ የጀመረው በጎርጎሮሳውያኑ 2016 ዓ ም ነበር። ዓላማው ደግሞ ምግብን እንደ ማህበራዊ እና ሙያዊ ውህደት ማስገኚያ መንገድ አድርጎ መጠቀም ነበር።

ፌስቲቫሉ የሚካሄደው በጎ ፍቃደኛ በሆኑ ምግብ ቤቶች የምግብ ማብሰያ ክፍል ውስጥ ስደተኛ የምግብ አብሳይ ባለሙያዎችን ከፈረንሳይ አቻዎቻቸው ጋራ ምግብ እንዲሰሩ በማድረግ ነው። ይህም ሙያዊ ውህደት እንዲፈጠር ባሻገር የሀገሩ ዜጎች በስደተኞች ላይ ባላቸው ግንዛቤ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲመጣ እገዛ ለማድረግ በማሰብ እንደሆነ ፌስቲቫሉ አዘጋጆች ይናገራሉ።

ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በፈረንሳይ የተካሄደው የስደተኞች የምግብ ፌስቲቫል ዝግጅት ፓሪስን ጨምሮ በቦርዶ እና በሊል በመሳሰሉ የፈረንሳይ ከተሞች ተከናውኗል። በፌስቲቫሉ ከተሳተፉ ስደተኛ የምግብ አብሳዮች ውስጥ የኢትዮጵያ፣ ሶሪያ፣ ኢራቅ እና አርሜንያ ባለሙያዎች ይገኙበታል። 

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  

ሃይማኖት ጥሩነህ 

ተስፋለም ወልደየስ 

እሸቴ በቀለ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW