1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

በፈጠራ ሥራው ዓለም አቀፍ ስኬት ያገኘው ወጣት

ዓርብ፣ ነሐሴ 2 2017

ዘንድሮ፣በቶሮንቶ ካናዳ ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ተማሪ የሆነው ናሆም፣የአፕል ኩባንያ ለተማሪዎች ያዘጋጀውን ውድድር በማሸነፍ አለም ዓቀፍ ዕዉቅና አግኝቷል ።አሸናፊ የሆነበትን አዲስ መተግበሪያ ይዞ፣ ካሊፎርኒያ ውስጥ በተካሄደው የኩባንያው ኮንፈረንስ ላይ በመገኘት፣ከኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ጋርም ተወያይቷል።

Kanada | Nahom Bekalu Worku als junger Innovator
ምስል፦ Nahom Bekalu Worku

በፈጠራ ሥራው ዓለም አቀፍ ስኬት ያገኘው ወጣት

This browser does not support the audio element.

ወላጅ አባቱም ስለቤተሰባዊ መስተጋብራቸው የሚያጫውቱን አለ።እንግዳችን፣ናሆም በቃሉ ወርቁ ይባላል።ውልደቱ ኢትዮጵያ ሲሆን፣ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ካናዳ የመጣው፣የስምንተኛ ክፍል ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ነበር።ዘንድሮ፣በቶሮንቶ ካናዳ ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ተማሪ የሆነው ናሆም፣የአፕል ኩባንያ ለተማሪዎች ያዘጋጀውን ውድድር በማሸነፍ አለም ዓቀፍ ዕዉቅና አግኝቷል ።አሸናፊ የሆነበትን አዲስ መተግበሪያ ይዞ፣ ካሊፎርኒያ ውስጥ በተካሄደው የኩባንያው ኮንፈረንስ ላይ በመገኘት፣ከኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ጋርም ተወያይቷል።

አክሰስ ኢዲ ሦስት ዋና ዋና ገጽታዎች አሉት።  የመጀመሪያው የተማሪዎችን ባክራውንድ የሚፈልጉትን ዐይነት ኮርሶችን በመጠይቅ ሪኮሜንድ ማድረግ ይችላል። ማሽን ለርኒንግ በመጠቀም። ሁለተኛው ተማሪዎች ኖታቸውን ወደ ፋይል በማስገባት ያንን ጽሁፍ በማውጣት ጥያቄዎችና መልሶችን ማዘጋጀት ይችላል፤ፍላሽ ካርድ ይባላል።  ተማሪዎች በተሻለ ሁኔታ እንዲጠኑ ያለምንም ኢንተርኔት ካለ ግንኙነት መስራት እንዲችሉ የሚያደርግ ነው። ሌላኛው ደግሞ ያለ ኢንተርኔት የሚሠራ የቀን መቁጠሪያ የተማሪዎች ጊዜ አጠቃቀም ለማዳበር፣የጊዜ ገደቦች እንዳያልፍባቸው የሚያደርግ ነው፤የሰራሁት መተግበሪያ እነዚህን ሁሉ ስራዎች የሚሰራ ነው። ‘’

አሸናፊ የሆነበትን አዲስ መተግበሪያ

ናሆም፣አሸናፊ የሆነበትን አዲስ መተግበሪያ ይዞ ካሊፎርኒያ ውስጥ በተካሄደው የኩባንያው ኮንፈረንስ ላይ በመገኘት፣ከኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ጋርም ተወያይቷል።«የሚገርምና ያልተጠበቀ አጋጣሚ አጋጣሚ ነበር። እዚያ  ሄጄ የነበረው ጁን ሰባት ቅዳሜ ነበር። እና ሰኔ ስምንት ኩባንያው ውስጥ ለምትገኝ ምክትል ፕሬዝዳንት ነበር ስራችንን እንድናቀርብ  የተነገረን። ያው እሁድ ጠዋት ሄደን እዚያ  11 ብቻ ነበር የተመረጥነው ከሃምሣ ሰዎች ።እዚያ ሄደን ለእርሷ ማሳየት ጀመርን እና መሃል ላይ አዲስ እንግዳ አለ ብለው ነው ዋና ሥራ አስፈፃሚው የመጣው ባልተጠበቀ ሁኔታ በጣም የሚገርም አጋጣሚ ነው  የነበረው። እኔ ወደ መጨረሻ አካባቢ ነበር ሳቀርብ የነበረው ለእርሱ የተሰጠኝም ደቂቃ ትንሽ ነበር ወደ ሶስት ደቂቃ ነበር። እና መተግበሪያውን አሳየሁትና አንዳንድ አስተያየት ሰጠኝ።  አተኩሮ እያየኝ ነበር፤በጣም የሚገርም ያልተጠበቀ አጋጣሚ ነበር። ‘» ሲል ገልጿል።

ናሆም የሰራው ''አክሰስ ኢዲ''የተሰኘ መተግበሪያ፣ኢትዮጵያን  ጨምሮ የኢንተርኔት ተደራሽነት ውሱንነት ባለባችው አገሮች ለሚገኙ ተማሪዎች አዳዲስ ዕድሎች እንደሚከፍት ተስፋ ያደርጋል። እርሱም ኢትዮጵያ ማደጉ በብዙ እንደጠቀመው አጫውቶናል። 'የአስተዳደጌ ሁኔታ ጠቅሞኛል። ያስተማሪዎቹ ነገር የቤት ሥራ በጊዜ እንድንሰራ ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ይገፋፋሉ። እሱም አንድ ጠቅሞኛል። በስነ ምግባር እንደታነጽ ረድተውኛል። እንዲሁም ቤተሰቦቼ የቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር እርዳታም ሆኖ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሼያለሁ። ''

ናሆም፣አሸናፊ የሆነበትን አዲስ መተግበሪያ ይዞ ካሊፎርኒያ ውስጥ በተካሄደው የኩባንያው ኮንፈረንስ ላይ በመገኘት፣ከኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ጋርም ተወያይቷልምስል፦ Nahom Bekalu Worku

 አውሮፕላን አብራሪ የመሆን ህልም ነበረው

የዛሬው እንግዳችን በሁለት የስራ አቅጣጫዎች ማለትም የአጎቱን ፈለግ በመከተል አውሮፕላን አብራሪ መሆን ፣ ወይም እንደ አባቱ በምህንድስና ሙያ መሰማራት የልጅነት ምኞቱ ነበር። ይሁንና በአውሮፕላን የመብራር ፍራቻው፣የፓይለትነት ፍላጎቱን አስተወውና የአባቱን ሙያ ተከትለ። ስለ ናሆም የልጅነት አስተዳደግ የጠየቅናቸው ወላጅ አባቱ፣በቃሉ ወርቁ የሚከተውን ምላሽ ሰጥተውናል። «ናሆም፣አስተዳደጉ ፈጣን ልጅ  ነው፤በልጅነቱ ነገሮችን ቶሎ የመረዳት አቅም አለው። እኔም እንግዲህ  ያው  ወደ ቤት ስራዎችን ይዤ እገባለሁና የምሰራውን ያያል። አንዳንድ ነገሮችን ይጠይቃል። አንዳንዴ ትንንሽ ነገሮችን እሰጠዋለሁ። እንዲረዳኝም እንዲሰራም ወደፊት እንዲጠቅመው፣ሰፋ ያለ አስተሳሰብ እንዲኖረው እያልኹ። እንደእዛ እናደርግ ነበር። ከሥራም መልስ እነርሱን የቤት ስራ ማስራት ላይ ነው የምጠመደው። ያም ጠቅሟቸዋል ብዬ አስባለሁ። የሚያየው ነገር እንግዲህ እናቱም ታነባለች እኔም አነባለሁ፣እና አጥኑ ስንላቸው፣እኛም የሆነ ነገር እየሰራን ነው እና አስተዋጽኦ አድርጎላቸዋል ብዬ አስባለሁ። ሌላው የጠቀመው ብዬ የማስበው፣እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ኢትዮጵያ ነው የተማረው። ኢትዮጵያ ያለው  የትምህርት ሥርዓት ጠንከር ያለ ነው።  በተለይ ሂሳብ እና ሳይንስ ላይ ጠንካር  ያለ ነው። መሠረት ካልያዙ ያስቸገራል፣ናሆም ኢትዮጵያ መማሩ፣ ሂሳቡንም ሳይንሱንም ተምሮ መምጣቱ፣ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሲገባ አልቸግረውምና በእዛው በጥሩ ውጤት እየገፋ እንዲሄድ አድርጎታል። እና ትልቅ አስተጽኦ አለው ብዬ አስባለሁ። ያው ከሚያየውበተጨማሪ ማለት ነው።» በማለት ገልፀዋል።

«እንደ ኢትዮጵያዊ ትልቅ ደስታ ነው»

 አሁን ልጃቸው አለም አቀፍ ተሸላሚ ሆኖ ሲያገኙት ምን ስሜት እንደፈጠረባቸው ሲያስረዱ፣»ሥራውን ሲጀምረው ጊዜም ስለነበረው በዛም ስላለ ቢያንስ መሳተፉ እንኳ ጥሩ ነው ብዬ ዐስብ ነበር። ብዙ እያመሸ ስለሚሰራ እኔ ብዙ አታምሽ እለዋለሁ። ምክንያቱም ጠዋት ኢንተርንሽፕ ሰለሚሰራ ሥራ  ይሆናል ። ይህን ሁሉ ካደረገ በኋላ አስረከበ። ከዛም ውጠቱ የሚገለጽበትን ቀን ነግሮኝ ነበርና አሸነፍኹ ሲለኝ ትልቁን ምስጋና የሚወስደው እግዚአብሔር ነው ። ግን እንደወላጅ ደግሞ ስላልጠበቅሁት ይመስለኛል በጣም ነው ደስ ያለኝ፣እናቱም በጣም ነው ደስ ያላት። እንደ ኢትዮጵያዊም ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ።»ብለዋል። 

 

ታሪኩ ኃይሉ

ፀሐይ ጫኔ 

 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW