1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፍልስጤም ታጣቂዎች የተገደሉት እስራኤላዉያን 50ኛ ዓመት መታሰብያ

ሰኞ፣ ነሐሴ 30 2014

እስራኤልን እና ጀርመን ከ 50 ዓመታት በፊት ጀርመን ሙኒክ ላይ በስምንት ፍልስጤማዉያን የተገደሉትን ዘጠኝ የእስራኤል የኦሎምፒክ ስፖርት አባላትን አስበዉ ዋሉ። የጀርመኑ ርዕሰ ብሔር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በፍልስጤማዉያን ስለተገደሉት ለተገደሉት የእስራኤል ኦሎምፒክ ቡድን አባላት ቤተሰቦቻቸዉን ይቅርታ ተማፅነዋል።

Gedenkveranstaltung zum 50. Jahrestag des Olympiaattentats
ምስል Sven Hoppe/dpa/picture alliance

እስራኤልን እና ጀርመን ከ 50 ዓመታት በፊት ጀርመን ሙኒክ ላይ በስምንት ፍልስጤማዉያን የተገደሉትን ዘጠኝ የእስራኤል የኦሎምፒክ ስፖርት አባላትን አስበዉ ዋሉ።  
የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ኢዝቻክ ኸርዞግ ለዚሁ ጉዳይ ለሦስት ቀናት ጉብኝት ዛሬ ነዉ ጀርመን የገቡት። ፕሬዝዳንት ኢዝቻክ በርሊን በሚገኘዉ የርዕሰ ብሔር መቀመጫ ሽሎዝ ቤሌቩ በጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ኸርዞግ ወደ ጀርመን ለማምራት ሲነሱ ሃገራቸዉ ላይ በሰጡት መግለጫ የጀርመን የሦስት ቀናት ጉብኝታቸው አንዱና ዋንኛዉ ምክንያት የሙኒኩን ኦሎምፒክ ጥቃት 50ኛ ዓመት መታሰቢያ ለመዘከር ነዉ። የሁለቱ ሃገራት ርዕሳነ ብሔራት ዛሬ በርሊን ሽሎዝ ቤልቩ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የሃገራቱ ግንኙነት ለየት ያለ እና ጥሩ መሆኑን ገልፀዋል። ይሁንና የዛሬ 50 ዓመት በሙኒኩ ኦሎምፒክ መንደር በእስራኤል ስፖርተኞች ላይ የተፈፀመዉ ጥቃት በሃገራቱ ጥሩ ግንኙነት ላይ ጥላ አጥልቶ ነበር ሲሉ አስታዉሰዋል። የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ጀርመን ሙኒክ ላይ በጎርጎረሳዉያኑ 1972 ዓ.ም  ታርደዉ ስለተገደሉት የእስራኤል ኦሎምፒክ ቡድን አባላት ቤተሰቦች ይቅርታን ተማፅነዋል። 
በጎርጎረሳዉያኑ 1972 ስምንት የፍልስጤም ወታደሮች በሙኒክ ኦሎምፒክ መንደር በሚገኘው የእስራኤል ኦሎምፖክ ቡድን አባላት ላይ ጥቃት እና እገታ ፈፅመዉ ዘጠኝ  የእስራኤል ኦሎምፒክ ቡድን አባላትን በሙሉ መግደላቸዉ ይታወቃል። 

 

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW