1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፓሪስ መድረክ ላይ በአማርኛ ቋንቋ የቀረበዉ ትያትር

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 20 2014

ኪነ-ጥበብ የሰዉ ልጆችን አኗኗር ባህል እና ታሪክ ቋንቋን አመለካከትን እና ማኅበራዊ መስተጋብርን ፍቅር እና ጥላቻዉን በማንሳት የገሃዱ ዓለም ነፀብራቅ በመሆን ሰዉን ለማዝናናት ለማስተማር ለማሳወቅ ለማመስገን እና ለመተቸት የጥበብ መንገድ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

"Les Sœurs de Chocolat" Belen Getachew Äthiopien"Les Sœurs de Chocolat" Belen Getachew Äthiopien"Les Sœurs de Chocolat" Belen Getachew Äthiopien
ምስል Haimanot Tiruneh/DW

የፈረንሳይ እና የኢትዮጵያ ትዉልድ ባላት የትያትር ደራሲና ተዋናይት ተዘጋጅቶ የቀረበ

This browser does not support the audio element.

ኪነ-ጥበብ የሰዉ ልጆችን አኗኗር ባህል እና ታሪክ ቋንቋን አመለካከትን እና ማኅበራዊ መስተጋብርን ፍቅር እና ጥላቻዉን በማንሳት የገሃዱ ዓለም ነፀብራቅ በመሆን ሰዉን ለማዝናናት ለማስተማር ለማሳወቅ ለማመስገን እና ለመተቸት የጥበብ መንገድ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። የኪነ-ጥበብ ስራዎች ከሚገለፁባቸዉ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች መካከልም ትያትር አንዱ ነዉ። ይህ ጥንታዊ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ በቀጥታ በመድረክ ትወና  ወይም ቃለ ተዉኔት የሚቀርብ አልያም በግጥም፤ በሙዚቃ ፤ በመነባንብ  መልክ በአስቂኝ እና አሳዛኝ መልኩ ታሪኮችን በእንቅስቃሴ አጅቦ ለተመልካቾች የሚቀርብበት የጥበብ ዘርፍ ነዉ። ይህ ዝግጅታችን ከትያትር ጋር በተያያዘ አብዛኞች አድናቂዎችዋ «ዘላይት ኦፍ ሲቲ» ወይም የብርሃን ከተማ ተብላ በምትታወቀዉ የዓለማችን የተደነቁ የኪነ-ጥበብ ስራዎች መገኛ  ወደ ሆነችዉ ወደ ፈረንሳይዋ ዋና መዲና ፓሪስ ይወስደናል። በርካታ ዝነኛ ትያትር ቤቶች እና የኪነ-ጥበብ ሰዎች መገኛ የሆነችዉ ፓሪስ ከተማ ሰሞኑን ባልተለመደ መልኩ ለትያትር አፍቃርያን በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀዉን የመድረክ ትያትር ስታስኮሞኩ ነዉ የሰነበተችዉ። ኢትዮጵያዉያን አርቲስቶች ከፈረንሳዉያን የኪነ-ጥበብ ሰዎች ጋር ያገናኘኘዉ ሦስቱ የቸኮሌት እህትማማቾች፤ በሚል የቀረበዉ ትያትር የፈረንሳይ እና የኢትዮጵያ ትዉልድ ባላት የትያትር ደራሲና ተዋናይት ተዘጋጅቶ የቀረበ የመድረክ ሥራ ነዉ። ኑሮዋን በፈረንሳይ ያደረገችዉ እና የአንጋፋዉ የአገር ፍቅር ትያትር ባልደረባ የነበረችዉ አርቲስት ብሌን ጌታቸዉም በመድረኩ ላይ ተካፋይ ነች።  ይህ ዝግጅታችን በተመልካቾች ዘንድ አድናቆትን ስላተረፈዉ ትያትር እና የትያትሩን አርቲስቶች እንግዳዉ አድርጎአል።

"Les Sœurs de Chocolat" Belen Getachew Äthiopien"Les Sœurs de Chocolat" Belen Getachew Äthiopien
ምስል Haimanot Tiruneh/DW

ሃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW