1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፓሪስ ‘‘ማራቶን ለሁሉም’’ በባዶ እግሩ የሮጠው ኢትዮጵያዊው ኤርሚያስ አየለ

ዓርብ፣ ነሐሴ 10 2016

በፓሪስ ኦሎምፒክ «ማራቶን ለሁሉም ፓሪስ 2024» በሚል በኦሎምፒክ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነ አማተር ሯጮች የተሳተፉበት የ42 ኪ/ሜ ሩጫ ተካሂዷል።በዚህ ውድድር ብቸኛ ተሳታፊ የነበረው ኢትዮጵያዊ ኤርሚያስ አየለ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪቃ ቀዳሚ የኦሎምፒክ አሸናፊውን አበበ ብቄላን ለመዘከር በባዶ እግሩ በመሮጥ ነበር ውድድሩን ያጠናቀቀው።

 በባዶ እግሩ ከሮጠው ኢትዮጵያዊው ኤርሚያስ አየለ
በፓሪስ ‘‘ማራቶን ለሁሉም’’ በባዶ እግሩ ከሮጠው ኢትዮጵያዊው ኤርሚያስ አየለ ምስል Haimanot Tiruneh/DW

ኢትዮጵያዊው ኤርሚያስ አየለ በባዶ እግሩ የሮጠው አበበ ብቄላን ለመዘከር ነው

This browser does not support the audio element.

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ «ማራቶን ለሁሉም ፓሪስ 2024» በሚል በኦሎምፒክ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነ አማተር ሯጮች የተሳተፉበት የ42 ኪ/ሜ ሩጫ ተካሂዷል።በዚህ ውድድር ብቸኛ ተሳታፊ  የነበረው ኢትዮጵያዊ ኤርሚያስ አየለ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪቃ ቀዳሚ የኦሎምፒክ አሸናፊውን አበበ ብቄላን ለመዘከር በባዶ እግሩ በመሮጥ ውድድሩን አጠናቋል።ኤርሚያስ አየለ ለበርካታ አመታት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን ያገለገለ ሲሆን፤ ከአወዳዳሪነት ወደ ተወዳዳሪነት ፊቱን ከመለሰ  ሁለት ዓመታት ገደማ ሆኖታል። ኤርሚያስ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች በተለዬ በባዶ እግሩ በመሮጥ ቀደም ሲል በተሳተፈባቸው  ዓለም አቀፍ የጎዳና ውድድሮች የማራቶን ጀግናውን አበበ ብቄላን ዘክሯል።

ኤርሚያስ፤ በፓሪስ ኦሎምፒክም  ከሩጫው ባሻገር ለአፍሪቃ በተዘጋጄ ልዩ ህዝባዊ መድረክ ፤የጀግናውን አትሌት አበበ ብቄላ ቁርጠኝነት እና አይበገሬነት እንዲሁም ኢትዮጵያን ለዓለም ለማስተዋወቅ መቻሉን ገልጿል።በዚህም ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል። «ህዝባዊ የጤና ሯጭ የተሳተፈው በኦሎምፒክ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።እና እዛ ላይ መሳተፍ በራሱ አንድ ትልቅ ቦታ አለው።በባዶ እግር ሆኖ ደግሞ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ መሰረት የሆነውን አበበ ብቄላን ማስታወስ እና ሌሎችንም መዘከር ትልቅ ፋይዳ አለው።»በማለት ገልጿል።

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።


ሀይማኖት ጥሩነህ
ሂሩት መለሰ
ፀሐይ ጫኔ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW