በፕሬዚዳንት አሳድ ላይ ጫና በርክቷል2 ነሐሴ 2003ሰኞ፣ ነሐሴ 2 2003የሶሪያ መንግሥት ጦር የአገሪቱን ሕዝባዊ ተቃውሞ በሃይል ለማቆም በያዘው አስከፊ ዘመቻ ቀጥሎ ሰንብቷል።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግሀማ ከተማ የቆሙ ታንኮችምስል APTN/AP/dapdማስታወቂያየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን-ኪ-ሙን እና የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ የሶሪያ መንግሥት በገዛ ሕዝቡ ላይ የሚወስደውን የጭካኔ ዕርምጃ እንዲያቆም ጠይቀዋል። ፕሬዚደንት ባሸር-አል-አሣድ ግን የሀይል እርምጃውን አጠናክረዋል። ባለፉት 2 ቀናት ብቻ በመንግስታዊው እርምጃ የ90 ሰዎች ህይወት አልፏል። የንስ ቪኒንግ ልደት አበበ ሸዋዬ ለገሠ