በ 2 ተኛው የዓለም ጦርነት የ 3 ተኛው ዓለም ሚና
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 6 2003ማስታወቂያ
ከዚህ ውስጥ በጦርነቱ የ 3 ተኛው ዓለም በተለይም የአፍሪቃውያን ሚና አንዱ ነው ። ከመስከረም አንስቶ በምዕራብ ጀርመኗ የኮሎኝ ከተማ በመታየት ያለ አንድ ዐውደ ርዕይ ይህን የተሳሳተና በርካታ አውሮፓውያን የማያውቁትን የተደበቀ ታሪክ ያሳያል ። “በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የ 3 ተኛው ዓለም ሚና“ የተሰኘው ይህ ዐውደ ርዕይ የቀረበበት ህንፃም በጦርነቱ የናዚ ጀርመን ቁምስቅል ማሳያ ስፍራ ነበር ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን እዚህ አውሮፓ ብዙም በማይታወቀው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የአፍሪቃውያን ድርሻ ላይ ያተኩራል ። አብረን እንቆይ ። ሂሩት መለሰ ተክሌ የኋላ