1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቢምቢ ወይም ትንኝ የሚያመጣቸው በሽታዎች ስጋት በድሬደዋ

ዓርብ፣ መስከረም 8 2013

በድሬደዋ አስተዳደር በችኩንጉንያ ፣ ደንጊና ወባ በሽታ የሚያዙ ነዋሪዎች በመታየት ላይ ናቸው። ለተጠቀሱት በሽታዎች መንስኤ የሚሆኑት ቢምቢዎች ወይም ትንኞች መሆናቸው ተገልጿል። የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ በተደረጉ ምርመራዎች በሽታዎቹ መኖራቸውን ማረጋገጡንና የመከላከል ሥራ እየሠራሁ ነው ይላል።

Stechmücke auf Hautoberfläche
ምስል picture-alliance/dpa/Center for Disease Control/J. Gathany

«በሽታዎቹ በትንኝ አማካኝነት የሚመጡ ናቸው»

This browser does not support the audio element.

ወቅትን ተከትሎ በድሬደዋ እየተቀሰቀሰ ባለው የቺኩንጉንያ ፣ ደንጊ እና ወባ በሽታዎች የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን መመልከታቸውን ከቀናት በፊት በደንጊ በሽታ እንደተያዙ ለዶይቸ ቨሌ አስተያየት የሰጡ የከተማ ነዋሪ ተናግረዋል።  የበሽታው ስሜት በሆኑ ብርድ ብርድ ፣ ትኩሳት እና በከፍተኛ አቅም በማጣት መቸገራቸውን የተናገሩት አስተያየት ሰጪው በተለይ ከአንድ አመት በፊት በከፍተኛ ደረጃ ህብረተሰቡን ያጠቃው የቺኩንጉንያ እና ደንጊ በሽታ በስፋት እንዳይቀሰቀስ  ኅብረተሰቡ እና መንግሥት ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡ የህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶ/ር ፈቲ በበኩላቸው በእነዚህ የትኩሳት በሽታዎች ሳቢያ ኮሮና ይበልጥ ሊስፋፋ እንደሚችል ስጋታቸውን በመግለፅ በጋራ መረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡ የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በሽታዎቹ መከሰታቸው በላብራቶሪ ምርመራ ውጤት መረጋገጡን ጠቁመው መንግስት ችግሩን ለመፍታት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ከአንድ አመት በፊት በመስተዳድሩ ተከስተው በነበሩት የችኩንጉንያ እና ደንጊ በሽታዎች ሳቢያ ከሃምሳ ሺህ በላይ ሰዎች ለበሽታው መጋለጣቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። መሳይ ተክሉ ከድሬደዋ ዝርዝሩን ልኮልናል።

መሳይ ተክሉ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW