ቢቢሲ ባንድ ኤይድን ይቅርታ መጠየቁ25 ጥቅምት 2003ሐሙስ፣ ጥቅምት 25 2003ባንድ ኤይድ የተባለው የዕርዳታ ድርጅት ለ 1977 ቱ የኢትዮጵያ ረሀብ መርጃ ያሰባሰበው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ለጦር መሣሪያ መግዣ ውሏል ሲል የብሪታኒያ ዜና መሰራጫ ኮርፖሬሽን ቢቢሲ ባለፈው ዓመት ላሰራጨው ዘገባ ዛሬ ይቅርታ ጠየቀ ።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግቦብ ጌልዶፍምስል APማስታወቂያቢቢሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በዘገባው ምክንያት ስለ ድርጅቱ የተሳሳተ ግንዛቤ በመፈጠሩ ጥፋተኛ መሆኑን አስታውቋል ። የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የቀድሞው ከፍተኛ የአመራር አባልና በወቅቱ የድርጅቱ ወታደራዊ ክፍል ሀላፊ የነበሩት ዶክተር አረጋዊ በርሄ የቢቢሲ ይቅርታ አስገራሚ ነው ይላሉ ። ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሐመድ