1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቢቢሲ የሚታመስበት የቅሌት ተግባር

ሰኞ፣ ኅዳር 3 2005

የብሪታንያው የራዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት-ቢቢሲ- ባለፉት ወራት ፣ ህጻናት ለአያሌ ዓመታት ፣ የወሲባዊ ጥቃት ዒላማዎች ሆነው ፤ ዜናው ተደብቋል በሚል ወቀሳና ክስ ሲታመስ ቆይቷል።

LONDON, ENGLAND - OCTOBER 24: Employees arrive early for work at BBC Broadcasting House on October 24, 2012 in London, England.A BBC1 'Panorama' documentary has new allegations about the handling by BBC2 programme 'Newsnight' over claims of sexual abuse allegedly carried out by fomer BBC television presenter, Jimmy Savile, the transmission of which was subsequently dropped. Police have confirmed that Sir Jimmy Savile, the BBC presenter and DJ who died in October 2011 aged 84, may have sexually abused young girls on BBC premises. (Photo by Peter Macdiarmid/Getty Images)
ምስል Getty Images

የብሪታንያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ቢቢሲ አንድ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ወግ አጥባቂ እንደራሴ አንድ ግለሰብን በወሲብ ደፍረዋል ሲል ከአሥር ቀን በፊት ባስተላለፈው የተሳሳተ ዜና ሰበብ በገጠመው ቅሌት የተነሳ የቢቢሲ ዋና ኃላፊ ጆርጅ ኤንትዊስል ከሁለት ወራት በፊት የያዙትን ስልጣናቸውን መልቀቃቸው የሚታወስ ነው።
« ባለፉት ጥቂት ሣምንታት የተከሰተው ሁኔታ ቢቢሲ አዲስ መሪ መሰየም አለበት የሚለው ውሳኔ ላይ እንድደርስ ገፋፍቶኛል። » ቲም ዴቪስ አሁን ቢቢሲን በተጠባባቂ ዋና ኃላፊነት እንዲያስተዳድሩ ተሰይመዋል።
በሀሰት የተወነጀሉት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እንደራሴ ወቀሳውን ሀሰት ሲሉ ካስተባበሉ በኋላ ወቀሳውን የሰነዘረው ግለሰብም እንደራሴውን በስህተት መወንጀሉን አምኖዋል። የታወቀው ሟቹ የቢቢሲ የቴሌቪዝን አስተዋዋቂ ጂሚ ሳቪል ለብዙ ዓመታት በመቶ የሚቆጠሩ ሕፃናትን በወሲብ ደፍሮዋል በሚል ከተወነጀለ ወዲህ ብዙ ወቀሳ ሲፈራረቅባቸው የቆዩትና ስልጣናቸውን የለቀቁት ኤንትዊስል አሁን 563,000 ዩሮ ማካካሻ ይከፈላቸው መባሉን ወግ አጥባቂ የምክር ቤት እንደራሴዎች ተገቢ ያልሆነ ውሳኔ ነቅፈዋል። ኤንትዊስል ስራቸውን ከለቀቁ በኋላ የዜና ክፍል ኃላፊ ሄለን ቦደን እና ምክትላቸው ስቲቭ ሚቼል ትናንት ከስራ ቦታቸው ለጊዜው መታገዳቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። ሁለቱ ግለሰቦች ሳቪል ሕፃናትን መድፈሩን የሚያመላክቱ ጥቆማዎች ባለፈው ዓመ በተደጋጋሚ ቢደርሱዋቸውም ዘገባዎቹን ለማቅረብ ያልፈለጉበት ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ ከስራ ቦታቸው እንዲርቁ ታዘዋል።
ይህን ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ የለንደንዋነ ዘጋቢአችን ሐና ደምሴን በስልክ አነጋግሬአታለሁ።

ከስልጣናቸው የታገዱት የዜና ክፍል ኃላፊ ሄለን ቦደንምስል Reuters
ስልጣናቸውን የለቀቁት የቢቢሲ ዋና ኃላፊ ጆርጅ ኤንትዊስልምስል Getty Images

ሐና ደምሴ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW