1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባለቅኔ እና ፀሐፌ ተዉኔት አያልነሕ ሙላቱ

እሑድ፣ ሚያዝያ 23 2008

ከተዉኔቱ፤- እሳት ሲነድ፤ ድሐ አደግ፤ ሻጥር በየፈርጁ፤ ድርብ ጭቁን፤ የገጠርዋ ፋና ይጠቀሳሉ።ከግጥሙ ደግሞ ጥገት ላም እና ማን ይሆን የበላ የግጥም መድብሎች።የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ እና ሥነ ፅሁፍ ያሉበት ደረጃ ግን አንጋፋዉን ደራሲ ብዙ ሳያሳስቡ አልቀሩም።

ምስል bilderbox

ገጣሚ ናቸዉ።ፀሐፌ ተዉነትም።ከብዙ የግጥምና የተዉኔት ድርሰቶቻቸዉ መሐል ጣልቃ የገባች አንዲት የታሪክ መፅሐፍ አለቻቸዉ።መፅሐፏ በ19ኛዉ መቶ ክፍለ-ዘመን በሥነ-ፅሑፉ መድረክ፤ ዓለም አቀፍ ክብርና ሞገሥ ያተረፈዉ የሩሲያዊዉ ባለቅኔ የአሌክሳንደር ሰርግዬቪች ፑሽኪን ታሪክን ነዉ የምትወሳዉ።

በእሳቸዉ አገላለፅ «ሕዝባዊ» የሚሉት ለገበሬዉና ለዝቅተኛዉ መደብ የመወገን ፍልስፍናን ያዳበሩት ግን ከፑሽኪን ታሪክና ስራዎች ብቻ አልነበረም።ገን በልጅነታቸዉ ከገበሬ ሳይወለዱ ግን ገበሬ ሆነዉ፤ ከገበሬ ጋር ኖረዉ እንጂ።የፊታዉራሪ ልጅ ናቸዉ።ጎጃም ጠቅላይ ግዛት አገዉ ምድር አዉራጃ ተወለዱ።እዚያዉ አደጉ።ትምሕርትም ጀመሩ።መቀጠሉ ግን አሳር ነበር።

ከተዉኔቱ፤- እሳት ሲነድ፤ ድሐ አደግ፤ ሻጥር በየፈርጁ፤ ድርብ ጭቁን፤ የገጠርዋ ፋና ይጠቀሳሉ።ከግጥሙ ደግሞ ጥገት ላም እና ማን ይሆን የበላ የግጥም መድብሎች።የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ እና ሥነ ፅሁፍ ያሉበት ደረጃ ግን አንጋፋዉን ደራሲ ብዙ ሳያሳስቡ አልቀሩም።

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW