ባለፉት 30 ዓመታት የቀጠለዉ ምክንያት የለሹ ግጭት በአፋርና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎች
ዓርብ፣ መጋቢት 26 2017
ባለፉት 30 ዓመታት በአፋር እና አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታወች ሲፈጠሩ የነበሩ ግጭቶችን ለማስቆም ማህበራዊ ሚድያን ለበጎ አላማ የተጠቀሙ ወጣቶች ደም የማድረቅ ተግባር እየከወኑ መሆኑ ተገለፀ። ምክንያት በሌለዉ ፀብ ለበርካታ አመታት በተለያዮ አዋሳኝ ቦታወች በሚነሱ ግጭቶች በየእለቱም ሰዎች ሲሞቱ የነበረ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የንብረት ዘረፋም ነበረ። አሁን ላይም መገዳደል ይብቃ ያሉ በሁለቱም ብሄሮች በኩል ያሉ ወጣቶች ሰላም የማምጣቱን ተግባር እየከወኑ ነዉ ።
ባለፉት 30 አመታት የቀጠለዉ ምክንያት የለሹ ግጭት በአፋርና አማራ አዋሳኝ አካባቢዎችየአማራ እና አፋር ክልሎች ከስምምነቱ በኋላ
ምክንያት የለሹ ፀብ ባለፉት30 አመታት በአማራና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በሚፈጠር ግጭት ብዙዎች ሲሞቱ የንብረት ዝርፊያና መሳሪያ ገፈፋዉ በሁለቱም ብሄሮች በኩል ሲከሰት ቆይተል በእዋ፣ድሬሮቃ፣ሶዶማ፣ዳፋራ፣ ጉራ ወርቄና ሌሎች ድንበርተኛ አካባቢዎች ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች በየእለቱ ምክንያት በሌለዉ ቁርሾ ሰዎች ይሞታሉ ይሉናል በአፋር ክልል እዋ ወረዳ የሸሪአ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት የሆኑት ሀጂ አረቡ ወልኢኖ መገዳደል ተጀምሮ ነበር። ያጉዳይ እየተባባሰ ሄደ ከዚያ እኛ መታረቅ አለብን ብለን እንቅስቃሴ ጀምረን ነበር መቀጠል ግን አልቻልንም መገዳደል ተጀመረ ከዚያ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በየቀኑ ሰዉ የማይሞትበት የማይገዳደሉበት ቀን የለም።
ከጥንት አባቶቻችን ተመሳሳይ ችግሮች ሲፈጠሩየተበደለን ክሶ መታረቅ በደስታና በሀዘን መገናኘት ለአፋርም ሆነ አማራ ማህበረሰብ ተወላጆች የቆየ ልማድ የነበረ ቢሆንም ባለፉት 30 አመታት ግን እርቁ እንዳይሰምር የሚያደርጉ አሉ የሚሉት በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ድሬ ሮቃ ኖሪ የሆኑት የሀገር ሽማግሌ አቶ መሀመድ ኑር መሀመድ ናቸዉ።በአፋር የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው ስጋት እና የክልሉ መንግስት የሰጠው ምላሽ
የብሄር ክልል ከመጣ በኆላ አማራ አማራ ነዉ አፋር አፋር ነዉ የሚል ነገር ተነሳ ከዚያ በኃላ አፋር ከገደለ አማራ ከሞተ በሙሉ የኛ አፋር እገድላለሁ ይላል እዚያዉ ይበቃቀላል እንደገና ንብረቱን ይሰራረቃል እንደምታየዉ ለ30 ዓመት ያህል በዚሁ እየዘለቀ ነዉ በዚሁ መካከል ላይ ብዙ እርቆችን ፈፅመናል እርቁ እንዳይሰምር ግን የሚሆን ነገር አለ ብየ ነዉ የምገምተዉ።
ማህበራዊ ሚድያን ለበጎ ተግባር ያዋሉ ወጣቶች
ከልጂነት እድሜዉ ጀምሮ የአካባቢዉ ማህበረሰብ መገዳደል ዝርፊያና ሌሎች ተግባሮች ጥያቄ የሆነበት መሀመድ ሙሴ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ማህበራዊ ሚድያን ተጠቅመዉ በሁለቱም ብሄሮች ዉስጥ ያሉ ወጣቶችን በማሳተፍ ዛር ሰላም መፍጠር እንደቻሉ ይናገራል። ስንጀምር የተወሰንን ልጆች ነን ከወደ ሀሮ ይማም የሚባል አንድ ወንድማችን አለ ሀሳቡን አመጣ በዚያ ሀሳብ ከወደ እኛም አንድ ሦስት ሰዉ ተቀላቅለን ሀሳቡን ወደ መሬት ለማዉረድ ሞከርን እናም አሁን ያለዉ ነገር በጣም ጥሩ ነዉ። ወጣቶቹ በሁለቱምበኩል ያሉ ችግሮችን በመለየትና የሀገር ሽማግሌዎችን በማስተባበር የችግሩ ዋንኛ ተሳታፊዎች ወጣቶች በመሆናቸዉ መገዳደልና ዝርፊያን ለማስቀረት ፊት ለፊት ተገናኝተዉ መምከር ችለዋል።
«ከነርሱ ጋር ተገናኝተን ተወያይተን ከአሁን በኃላ መገዳደል አይጠቅመንም ምን ጥቅም አመጣ እስካሁን አንዱ ይገድላል ይሄኛዉም ደግሞ ይገድላል ይሄም ይገድላል ደም ለመመላለስ የሚደረግ ነዉና ምንም መነሻዉ የማይታወቅበት ዉጊያ ነዉ አሁን ያለበት ያዉ ሰላሙን ለማምጣት ደግሞ ወጣቱ ቆርጦ ተነስቱል አሁን።»በአፋር ክልል በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ስምንት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
ከዚህ ቀደም ግጭቱን ለማስቆም የተወሰደዉ መፍትሄ ዉጤታሜ አልነበረም
ይህንን በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶችን ለማስቀረት የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸዉም ያለን አህመድ ሰይድ ዛሬ ላይ ግን ወጣቶቹ በመግባባታቸዉ ተዘርፎ የሄደን ንብረት ማስመለስ ተችሎል ይላል። «ግመሎች የሚሰረቁ ካሉ ወዲያዉ እለት በእለት እንዲመለስ የሚገድል ካለ እንድናሳስር ብለን ተወያይተንወደ ስራ ገባን አሁን 20 ግመል ተመልሶል።»
አካባቢዉ ከሌላዉ ጊዜ የተሻለ ሰላም ማግኘቱ
አሁን ላይ በአካባቢዉ ለበርካታ አመታት ያልታየ ሰላም እየመጣ ነዉ የሚሉት ሀጂ አረቡ ወልኢኖ ለዚህ ሰላም መገኘት የወጣቶች ሚና የጎላ ነዉ ብሉዋል። «ለኛም የጥንካሬ ስራ የሰሩት ወጣቶቹ ናቸዉ ወጣቶቹ ካወቁልን የኛ ድጋፍ የነርሱ ድጋፍ ነዉ ወጣቱ ከወደዚያም ከወደ እዚህም እየተጠናከረ ነዉና አሁን ባለዉ ጊዜ ለብዙ አመታት ተገኝቶ የማያዉቅ ለዉጥ እያየን ነዉ» እነኝህ ለዘመናት የቆየን ደም ለማድረቅ ማህበራዊ ሚድያን ለበጎ አላማ ያዋሉ ወጣቶች በአካባቢዉ ያሉ የሁለቱ ብሄሮችን በሌሎች የልማት ስራ የማስተሳሰር ፍላጎት እንዳላቸዉ ይገልፃሉ።
ኢሳያስ ገላዉ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ