1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኪነ ጥበብ

ባለ ልዩ ተሰጥኦዋ ወጣት ሰአሊ በነዚያ የጦርነት ዓመታት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 8 2016

ባለተሰጥኦዋ ወጣት ሰአሊ ልእልት ሃደራ፥ የተለያዩ ስእሎችን በከሰል፣ አፈር፣ ቅጠል፣ አበባዎች እንዲሁም ሌሎች አገልግለው የተጣሉ ቁሶችን በመጠቀም ትስላለች። ይህች በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የምትኖረው የ22 ዓመት ወጣት ባለተሰጥኦ፥ በተለይም በጦርነቱ ወቀት የተለያዩ ሐሳቦችዋን የሚገልፁ የስእል ሥራዎች በቤትዋ አዘጋጅታለች።

ወጣቷ ባለተሰጥዖ ሰአሊ ከትግራይ ክልል፤ ኢትዮጵያ
ጦርነቱ በፈጠረው ችግር ስእሎች የምትስልበት ወረቀት ይሁን ሌላ ግብአት ስለሌላት ግን በነፃ የሚገኙ እንደ ክሰል ፤ አመድ የመሳሰሉ ግብአቶችን መጠቀም መጀመርዋን ትናገራለች ምስል፦ Million Hailesilassie/DW

አፈር፤ አመድ፤ ክሰልና የመሳሰሉትን ተጠቅማ የሳለችው በርካቶችን አስደምሟል

This browser does not support the audio element.

ባለተሰጥኦዋ ወጣት ሰአሊ ልእልት ሃደራ፥ የተለያዩ ስእሎችን በከሰል፣ አፈር፣ ቅጠል፣ አበባዎች እንዲሁም ሌሎች አገልግለው የተጣሉ ቁሶችን በመጠቀም ትስላለች። ይህች በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የምትኖረው የ22 ዓመት ወጣት ባለተሰጥኦ፥ በተለይም በጦርነቱ ወቀትየተለያዩ ሐሳቦችዋን የሚገልፁ የስእል ሥራዎች በቤትዋ አዘጋጅታለች። ጦርነቱ በፈጠረው ችግር ስእሎች የምትስልበት ወረቀት ይሁን ሌላ ግብአት ስለሌላት ግን በነፃ የሚገኙ እንደ ክሰል ፤ አመድ የመሳሰሉ ግብአቶችን መጠቀም መጀመርዋን ትናገራለች ። ወጣቷ ሰአሊ፥ ከሰልና፣ አፈር፣ ዕፅዋቶች ተጠቅማ በተጣሉ ወረቀቶች የሰራቻቸው የስእል ስራዎች በበርካቶች ዘንድ አድናቆት አትርፈዋል።

ይህች ወጣት ሰአሊ ስእሎችዋን የምትሰራበት ስቱድዮ አልያም የጥበብ ሥራዎችዋን የምታቀርብበት መድረክ በትግራይ ክልል አልነበረም ። ጦርነት፣ ሞት፣ ችግር በነገሰባቸው በእነዛ ሁለት ዓመታት፥ ወጣትዋ ሰአሊ ከሰው መራቅ፣ ቤት መዋል፣ በጥበብ መራቀቅን መረጠች። የዛኔ ፥ ባለተሰጥኦዋ እንስት ልእልት ሃደራ፥ የተለያዩ ስእሎችን በከሰል፣ አፈር፣ ቅጠል፣ አበባዎች እንዲሁም ሌሎች አገልግለው ከተጣሉ ቁሶች መሳል ጀመረች።

በአሁኑ ወቅት ነዋሪነትዋ በመቐለ ከተማ የሆነው የ22 ዓመት ወጣት ባለተሰጥኦ፥ በተለይም በጦርነቱ ወቀት የተለያዩ ሐሳቦችዋ የሚገልፁ የስእል ስራዎች በቤትዋ አዘጋጅታለች።

ባለተሰጥኦዋ ወጣት ሰአሊ ልእልት ሃደራ፦ የጥበብ ሥራዎችዋ ለዕይታ ማቅረብ፣ ዕውቀትዋን ማበልጸግ፣ የትምህርት ዕድል ማግኘት እና ችሎታዋን ማዳበር በቀጣይ ማሳካት ትሻለችምስል፦ Million Hailesilassie/DW

ጦርነቱ በፈጠረው ችግር ስእሎች የምትስልበት ወረቀት ይሁን እርሳስ፣ ቀለም ይሁን ሸራ አልያም ሌላ ግብአት ስለሌላት በነፃ የሚገኙ አልያም ያገለገሉ ግብአቶች መጠቀም መጀመርዋ የምትናገር ሲሆን፥ ከሰልና፣ አፈር፣ ዕፅዋቶች፣ ስባሪ ጠርሙስ፣ የወጥ መሣርያ እርድ እና ሌሎች ተጠቅማ በተጣሉ ብጣሽ ወረቀቶች ላይ ያሳረፈቻቸው የስእል ስራዎች በርካቶችን አጀብ አሰኝተዋል። በዚህች ወጣት ሰአሊ የጥበብ ስራዎች ሴትነት፣ ተፈጥሮ፣ ውበት፣ ኑሮ፣ የሕይወት ውጣውረድ እና ተስፋ ይንፀባረቃሉ።

በጦርነቱ ምክንያት ለረዥም ግዜ የተለያት ታላቅ ወንድሟ ሃብታሙ ሃደራ፥ የልእልት የጥበብ ሥራዎች በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በኩል ሲያቀርብ ፥ እንደዋዛ የተሳሉት፣ ማስቀመጫ ደህና ቦታ እንኳን የሌላቸው ስእሎች የብዙዎች አድናቆት አተረፉ። ወንድሟ ሃብታሙ እንዳለን በጦርነቱ ወቅት የተሳሉት እነዚህ ስራዎች መድረክ እንዲያገኙ ጥረት እያደረጉ ነው። የጥበብ ስራዎችዋን ለእይታ ማቅረብ፣ ዕውቀትዋን ማበልጸግ፣ የትምህርት ዕድል ማግኘት እና ችሎታዋን ማዳበር ልእልት በቀጣይ ማሳካት ትሻለች።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW