1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባልደራስ በፓሪስ

ዓርብ፣ ነሐሴ 10 2011

የባልደራስ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ ለገሠ የተገኙበትን ስብሰባ ያዘጋጁት ፣በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኮምኒቲ) ለዝግጅቱ ሊተባበረን ፈቃደኛ አልሆነም ሲሉ ወቀሱ። የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ (ኮምዩኒቲ) በበኩሉ ስብሰባዉ እንደሚደረግም ሆነ አቶ ኤርሚያስ እንደሚመጡ አስቀድሞ እንዳልተነገረው፣ የአዘጋጆቹ ማንነት እንዳልተገለጸለትም አስታዉቋል።

Frankreich Treffen "Addis Abeba Care taker"
ምስል DW/H. Tiruneh

ባልደራስ በፓሪስ

This browser does not support the audio element.

  የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት ወይም ባልደራስ የተባለዉ ስብስብ  ፓሪስ-ፈረንሳይ ዉስጥ በጠራዉ ስብሰባ ሰበብ ፈረንሳይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እየተወዛገቡ ነዉ።የባልደራስ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ ለገሠ የተገኙበትን ትናንት የተደረገዉን ስብሰባ ያዘጋጁት  ወገኖች በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኮምኒቲ) ለዝግጅቱ ሊተባበረን ፈቃደኛ አልሆነም ሲሉ ወቀሱ። የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ (ኮምዩኒቲ) በበኩሉ ስብሰባዉ እንደሚደረግም ሆነ አቶ ኤርሚያስ እንደሚመጡ አስቀድሞ እንዳልተነገረው፣ የአዘጋጆቹ ማንነት እንዳልተገለጸለትም አስታዉቋል። በፓሪሱ የውይይት መድረክ  ላይ የተገኙት አቶ ኤርሚያስ የአዲስ አበባ ህልውና እና ባለቤት ጉዳይ አደጋ ላይ ነው ማለታቸውን የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዘግባለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW