1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባይደን አሜሪካውያን ዴሞክራሲያቸውን እንዲጠብቁ ጠየቁ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 18 2016

ፕሬዚዳንቱ ትላንት ምሽት ከነጩ ቤተመንግስት ጽሕፈት ቤታቸው ባደረጉት ንግግር፣ለዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዚዳንታዊ ዕጩነት የደገፏቸው ካማላ ሃሪስን፣" ደፋርና ራዕይ ያላት መሪ" ሲሉ አወድሰዋቸዋል። ጆሴፍ ባይደን፣ድጋሚ የመመረጥ ፉክክራቸውን የማቆም ውሳኔያቸው፣የሃገሪቱን ዴሞክራሲ ለመከላከል የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ አመልክተዋል።

Rede an die Nation | US-Präsident Joe Biden
ምስል Evan Vucci/IMAGO/UPI Photo

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን አሜሪካውያን እንዳይከፋፈሉ ያስተላለፉት መልዕክት

This browser does not support the audio element.

ባይደን አሜሪካውያን ዴሞክራሲያቸውን እንዲጠብቁ ጠየቁ

አሜሪካውያን ዴሞክራሲያቸውን ለማስጠበቅ እንዲተባበሩ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ባይደን ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዚዳንቱ ትላንት ምሽት ከነጩ ቤተመንግስት ጽሕፈት ቤታቸው ባደረጉት ንግግር፣ለዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዚዳንታዊ ዕጩነት የደገፏቸው ካማላ ሃሪስን፣" ደፋርና ራዕይ ያላት መሪ" ሲሉ አወድሰዋቸዋል። ጆሴፍ ባይደን፣ድጋሚ የመመረጥ ፉክክራቸውን የማቆም ውሳኔያቸው፣የሃገሪቱን ዴሞክራሲ ለመከላከል የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ አመልክተዋል።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ

ሃገሬን የበለጠ እወዳታለሁ

"ይህን ቢሮ አከብራለሁ። ነገር ግን አገሬን የበለጠ እወዳታለሁ።"ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣የዲሞክራሲ ጥበቃ ከማንኛውም መጠሪያ ስያሜ በላይ አስፈላጊ ነው ብለዋል።  ከፕሬዚደንታዊ ዕጩነት እንዲገለሉ ከገዛ ፓርቲያቸው ከፍተኛ ጫና ገጥሟቸው የነበሩት ባይደን፣ውሳኔው ለሃገር ጥቅም የተደረገ በመሆኑ አሜሪካውያንም ዴሞክራሲያቸውን ለማስጠበቅ እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።

ይደን ለአሜሪካውያን ባደረጉት ንግግር፣በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ለሃገራቸውና ለሕዝባቸው ያስቀመጡትን የታሪክ ቅርስ በተመለከትም ሲናገሩ እንዲህ ብለው ነበር።ምስል Evan Vucci/IMAGO/UPI Photo

 

ፕሬዚዳንት ባይደን፣ ምክትላቸው ካማላ ሃሪስን፣"ልምድ ያላት፣  ደፋርና ራዕይ ያላት ሲሉ አወድሰዋቸዋል። ትራምፕን በቀጥታ ሳይጠቅሱም በቀጣዩ ምርጫ፣አሜሪካውያን ወደፊት ወይም ወደ ኋላ ከመሄድ፣ ከተስፋ እና ከጥላቻ፣ ከአንድነት እና ከመከፋፈል መኻከል መምረጥ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል። ትላንት ምሽት በሰሜን ካሮላይና የምርጫ ቅስቀሳ ያካሄዱት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ፣ ከቀናት በፊት በሃገራችን እጅግ አስከፊውን ፕሬዝደንት ጆሴፍ ባይደን በይፋ አሸንፈናል ሲሉ ተደምጠዋል።

ካማላ ሐሪስ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው ቢመረጡ ምን አይነት ኤኮኖሚያዊ እንድምታ ይኖረዋል?

የፕሬዚዳንት ባይደን አሻራ

ባይደን ለአሜሪካውያን ባደረጉት ንግግር፣በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ለሃገራቸውና ለሕዝባቸው ያስቀመጡትን የታሪክ ቅርስ በተመለከትም ሲናገሩ እንዲህ ብለው ነበር። "በፕሬዚዳንትነት ያለኝ አፈጻጸም፣ በዓለም ላይ ያለኝ አመራር፣ ስለ አሜሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ያለኝ ዕይታ፣ ሁሉም ለሁለተኛ ጊዜ የተገባ ነበር ብዬ አምናለሁ።ነገር ግን ዲሞክራሲያችንን ለማዳን ምንም ነገር ሊመጣ አይችልም፣ ይህ የግል ምኞትን ይጨምራል። በመሆኑም የተሻለው መንገድ ችቦውን ለአዲሱ ትውልድ ማስተላለፍ ነው።"

ፕሬዚዳንት ባይደን ለአሜሪካውያን ያደረጉት ንግግርና የትራምፕ መልዕክት

የፕሬዚዳንት ባይደንንን ውርስና አሻራ አስመልክቶ ያነጋግርናቸው የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያው አቶ መኮንን ከተማ፣ብዙ በጎ ነገሮችና ትሩፋቶችን ማከናወናቸውን ያስረዳሉ።

"በምርጫ ተመርጠው፣አይ የለም አላሸነፉም ተብለው፣ፕሬዚዳንት ትራምፕን የሚከተሉት ኮንግረስ ድረስ ገብተው ብዙ ችግሮች አምጥተው ነበር።ሃገሪቱ ተከፋፍላ ነበር።ሃገሪቱን አረጋግተው ለመምራት በቅተዋል። ይሄ ከባድ ነገር ነው። ቀላል ነገር አይደለም። ይህ ወደፊት በታሪክ እንደሚጻፍላቸው አውቃለሁ፤ አንዱ እሱ ነው። ሌላው እሳቸው የተረከቡት ኢኮኖሚ በኮቪድ በሽታ የተጎዳ ነበር። አሁን ኢኮኖሚስቶች የሚሉት፣ ከሌሎች አገሮች የበለጠ በፍጥነት እንዲያድግ አድርገዋል ይላሉ።እዚህ ሃገር በብድር ነው ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚማረው እሳቸው ምን አድርገዋል? ጥሩ ሁኔታ አበጃጅተው፣ያ ብድር እንዲሰረዝ ሁኔታ ስላበጁ፣ያን ዕድል ተጠቅመው ብዙ ተማሪዎች እንዲሰረዝላቸው ተደርጓል ብድራቸው።ይህ ትልቅ ሌጋሲ ነው በዝቅተኛ ቤተሰብ ላሉ።

ትራምፕን በቀጥታ ሳይጠቅሱም በቀጣዩ ምርጫ፣አሜሪካውያን ወደፊት ወይም ወደ ኋላ ከመሄድ፣ ከተስፋ እና ከጥላቻ፣ ከአንድነት እና ከመከፋፈል መኻከል መምረጥ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።ምስል Evan Vucci/IMAGO/UPI Photo

 

ደካማ ጎናቸው ምንድን ነው?

በታሪክ መነጽር ሊታዩ የሚችሉበት፣የባይደን ደካማ የሚባሉ የስራ አፈፃፀሞችን በተመለከተ የፖለቲካ ሳይንስ ተንታኙ ሲናገሩ፣ " አሁን እዚህ አገር፣ በዩክሬንና በሩሲያ ጉዳይ ብዙ ሰው ተከፋፍሏል።በእስራኤልም ጉዳይ ላይ ተከፋፍሏል ሰዉ።የእስራኤል ጉዳይ ግን ሪፐብሊካንም ሆነ ዴሞክራት አንድ ዐይነት ዕይታ ነው የሚኖረው፣እሱ የታወቀ ነው። በዩክሬንና በራሻ ላይ ብዙ ገንዘብ ወጣ ስለሚባል ያንን እንድ ድክመት ዐየሁ ይሆናል።"

ከአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደን ሲሰናበቱ ዶናልድ ትራምፕ ተፎካካሪያቸውን እየጠበቁ ነው

የመሰናበቻ ንግግር

ከተከታታይ የስንብት መልዕክቶቻቸው ውስጥ የመጀመሪያው በተባለው የትናንት ንግግራቸው፣ባይደን በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ፣ የፕሬዚዳንት ስራቸውን በመስራት ላይ እንደሚያተኩሩ ጠቁመዋል። በዚህም በትጋት የሚሰሩ ቤተሰቦችን ወጪ ማቅለልና  ኢኮኖሚውን ማሳደግ እቀጥላለሁ ብለዋል። በስልጣን ዘመናቸው መዝጊያ ቀናት ውስጥ የተለመደው የመሰናበቻ  ንግግር ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፤ረዳቶቻቸውም በትሩን ለተመራጯ ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ  ለማስተላለፍ በዝግጅት ላይ የሚሆኑበት እንደሚሆን ተስፋ ያደርጋሉ።

ታሪኩ ኃይሉ 

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW