1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ባይደን የአየር ንብረት ቀዉስን ለመቋቋም ቃል ገቡ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 14 2014

በአውሮጳ እና በዩናይትድ ስቴትስ የሙቀት ማዕበል መከሰቱን ተከትሎ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከአየር ንብረት ቀውስ ጋር በሚደረገው ትግል አዳዲስ እርምጃዎችን መዉሰድ ጀመሩ። ባይደን የከባቢ አየር ሙቀትን ለመቀነስ በምክር ቤት ውስጥ ብዙም ድምፅ የማያስፈልገዉ ረቂቅ አዋጅ ማቅረባቸዉ ተነግሮዋል።

USA Präsident Joe Biden
ምስል Evan Vucci/AP Photo/picture alliance

በአውሮጳ እና በዩናይትድ ስቴትስ የሙቀት ማዕበል መከሰቱን ተከትሎ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ  ባይደን  ከአየር ንብረት ቀውስ ጋር በሚደረገው ትግል አዳዲስ እርምጃዎችን መዉሰድ ጀመሩ። ባይደን የከባቢ አየር ሙቀትን ለመቀነስ  በምክር ቤት ውስጥ ብዙም ድምፅ የማያስፈልገዉ ረቂቅ አዋጅ ማቅረባቸዉ ተነግሮዋል። አዋጁ ዉስጥ ከተጠቀሱት ነጥቦች መካከል፣ ማኅበረሰቡ ከሙቀት፣ ከድርቅ ወይም ከጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ራሱን እንዲያዘጋጅ የሚያስችለዉ 2.3 ቢሊዮን ዶላር በጀት መድበዋል። ከዚህ በተጨማሪ ይበልጥ ውጤታማ የአየር ማቀዝቀዣ መሣሪያዎችን ለመጠቀም የሚያስችል ገንዘብ ማግኘት እንዲሁም በአትላንቲክ የባሕር ዳርቻና በሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ አዳዲስ የነፋስ ቱቦዎች መገንባትን ያካትታል። ይሁንና ፕሬዚዳንት ባይደን የአየር ንብረት ድንገተኛ የአደጋ ጊዜን  አላወጁም።

 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW