1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ትምህርትኢትዮጵያ

የዕድሉ ተጠቃሚዎች በተሰጠው ስልጠና ምን አገኙ?

ሰለሞን ሙጬ
ቅዳሜ፣ መስከረም 24 2018

"የመርሐ ግብሩ ዋና ዓላማ ውጭ ያሉ ባለሙያዎች እንዲሁም ዓለም አቀፍ በጎ ፈቃደኞች እዚህ ሀገር ውስጥ በተለያየ ክልል ላይ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሩዎች ጋር በማገናኘት አስፈላግ ዕውቀቶችን ማስተማር እና ብቁ ዜጋን ማፍራት ነው"

"ስልጠናው የሚያጠነጥነው የተማሪዎች የመግባባት ክህሎት፣ የአመራር ክህሎት፣ በጥልቀት ማሰብ የምንላቸው እንዲሁም ችግርን የመፍታት ክህሎትን የሚያዳብር መርሐ ግብር ነው ለተማሪው ሲሰጥ የቆየው።"
"ስልጠናው የሚያጠነጥነው የተማሪዎች የመግባባት ክህሎት፣ የአመራር ክህሎት፣ በጥልቀት ማሰብ የምንላቸው እንዲሁም ችግርን የመፍታት ክህሎትን የሚያዳብር መርሐ ግብር ነው ለተማሪው ሲሰጥ የቆየው።"ምስል፦ privat

የቀጠለው የ "ብሩህ ትውልድ" ወጣቶችን የማነጽ ጥረት

This browser does not support the audio element.

 "ብሩህ ትውልድ" የተባለው ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ላለፉት 12 ሳምንታት በመላውኢትዮጵያ ከሚገኙ 23 አካባቢዎች የተውጣጡ 600 ተማሪዎችን በልዩ ልዩ ክህሎቶች አሰልጥኖ ዛሬ ማጠናቀቁን አስታወቀ።

በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችና ዓለም አቀፍ በጎ ፈቃደኞች በበይነ መረብ የተሰጠው ይህ ስልጠና ተማሪዎቹ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸውን፣ የንባብ ባህላቸውን፣ ጠለቅ አድርጎ የማሰብ ልምምዳቸውን፣ የአመራር ችሎታቸውን እና ችግር የመፍታት አቅማቸውን እንዲያዳብሩ ያገዘ ነው ተብሏል።

በዚህ ስልጠና ተጨባጭ እውቀት ማኘታቸውን የገለፁ የዕድሉ ተጠቃሚዎ ተማሪዎች መደበኛው የትምህርት ሥርዓት እውቀት ከማስጨበጥ ባሻገር ክህሎትን ማሳደግ ላይ ቢያተኩር ለትውልድ ይበጃል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
የዚህ ትምህርት ዓላማው ምንድን ነው?
አሜሪካ በሚኖሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ 2022 የተመሠረተው "ብሩህ ትውልድ" ኢትዮጵያ ውስጥ የሚማሩና በትምህርታቸው የላቀ ችሎታ የሚያስመዘግቡ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን አወዳድሮ ብልጫ ላስመዘገቡት በልዩ ልዩ ዘርፎች  የገፅ ለገፅ እና የበይነመረብ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል። የድርጅቱ የኢትዮጵያ አስተባባሪ ፋሲካ ተስፋዬ እንደነገሩን የዚህ ሥራ ዓላማው "ብቁ ዜጋን ማፍራት" ነው።

"የመርሐ ግብሩ ዋና ዓላማ ውጭ ያሉ ባለሙያዎች እንዲሁም ዓለም አቀፍ በጎ ፈቃደኞች እዚህ ሀገር ውስጥ በተለያየ ክልል ላይ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሩዎች ጋር በማገናኘት አስፈላግ ዕውቀቶችን ማስተማር እና ብቁ ዜጋን ማፍራት ነው" 
በዚህ ዓመት ለአራተኛ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ 25 ቦታዎች ላይ 600 ያህል ተማሪዎችን ለሦስት ወራት ሲያሰለጥን መቆየቱን ታውቋል።

"ስልጠናው የሚያጠነጥነው የተማሪዎች የመግባባት ክህሎት፣ የአመራር ክህሎት፣ በጥልቀት ማሰብ የምንላቸው እንዲሁም ችግርን የመፍታት ክህሎትን የሚያዳብር መርሐ ግብር ነው ለተማሪው ሲሰጥ የቆየው።"


የዕድሉ ተጠቃሚዎች በተሰጠው ስልጠና ምን አገኙ?

የእድሉ ተጠቃሚዎች በስልጠና ላይምስል፦ privat

መደበኛ የትምህርት ጊዜ ሲያበቃክረምት ተጠብቆ በሚሰጠው ስልጠና የዚህ ዓመት ተሳታፊ ከሆኑት መካከል መቐለ ውስጥ የሚገኘው የቓላሚኖ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪዋ አርሴማ ሙሉ ብርሃን አንደኛዋ ናት።

"መርሐ ግብሩ በዋናነት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች የቀጣዩ ትውልድ የኢትዮጵያን ችግር የሚፈታ እና ኢትዮጵያን ለማሻሻል የሚያስፈልጉትን ክህሎቶች እና ትምህርቶችን ነው የሚሰጠው።"

ሌላኛዋ የአፋር ሎጊያ የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሪማ አብዱልቃድር እንደሌሎቹ ቃለ መጠይቅ ተድርጎላቸው ተሽለው ከተገኙት ተማሪዎች አንዷ ስትሆን መደበኛው ትምህርትም በዚህ መልኩ ቢሰጥ ተማሪዎች ውጤታማነታቸው የጎላ ይሆናል ትላለች። "መደበኛው የትምህርት ሥርዓት ተማሪ ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት።»

ብሩህ ትውልድ ላለፉት አራት ዓመታት 4,000 ተማሪዎችን ማሰልጠኑን የገለፁት የአዲስ አበባ አስተባባሪ ተማሪዎቹ በአቅማቸው ለሚፈቱ የማህረሰብ ችግሮችም ጥናት እንዲያደርጉ ዕድል እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል።


ሰሎሞን ሙጬ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW