ብሪታኒያና አዲሱ የስደተኞች ህግ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 21 2007ማስታወቂያ
የብሪታኒያ መንግሥት በሃገሪቱ በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩና ያለ ፈቃድ የሚሰሩ የውጭ ዜጎችን ማሰርና ከብሪታኒያ እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል አዲስ ህግ ሥራ ላይ እንደሚውል ማሳወቁ እያነጋገረ ነው ። መንግሥት ህጉን የሚያወጣው ወደ ብሪታኒያ በህገ ወጥ መንገድ የሚሰደደው ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ መሆኑን ይናገራል ። የመብት ተሟጋቾች በበኩላቸው መንግሥት የሚያቀርበው ምክንያት ተቀባይነት የለውም ሲሉ ይሟገታሉ ። በእንግሊዝና በዌልስ ግዛቶች ሥራ ላይ ይውላል ተብሎ በሚጠበቀው በአዲሱ ህግ ፣ህገ-ወጥ የሚባሉ የውጭ ዜጎች ከተያዙ የ6 ወር እሥራት እንደሚጠብቃቸውና እሥራታቸውንም እንደጨረሱ ወደ መጡበት ሃገር እንደሚባረሩ ተገልጿል ። ህገ ወጥ የሚባሉትን የሚያሠሩና ቤት የሚያከራዩም ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተነግሯል ።
ድልነሳ ጌታነህ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ