1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሪታኒያና የአውሮፓ ህበረት

ሐሙስ፣ ጥር 16 2005

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝቡ እንዲወስን የሚያደርጉት ወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው በመጪው ምርጫ ካሸነፈ ሲሆን ህዝበ ውሳኔውንም እ.ጎ.አ በ2017 መጨረሻ ለመጥራት ነው ያቀዱት ። አስቀድሞ ግን በአዲሱ ስምምነት ላይ እንደገና ለመደራደር ይፈልጋሉ ። ሆኖም ይህ የድርድር ጥሪ ከቅርብ አጋሮቿም ሆነ ከህብረቱ ባለሥልጣናት በኩል በጎ ምላሽ አላገኘም ።

EU referendum. Prime Minister David Cameron makes a speech on Europe, in central London, where he promised an in/out referendum on the UK's membership of the European Union by the end of 2017, if the Conservatives win the next general election. Picture date: Wednesday January 23, 2013. See PA story POLITICS Europe. Photo credit should read: Stefan Rousseau/PA Wire URN:15610024
ምስል picture alliance / empics

የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምረን ብሪታኒያ የአውሮፓ ህብረት አባል ሆና እንድትቀጥል ያቀረቡት የአዲስ ድርድር ጥሬ የአባል ሃገራትን ድጋፍ አላገኘም ። ካምረን በትናንቱ ንግግራቸው ሃገራቸው በህብረቱ ውስጥ እንድትቆይ ትግላቸውን ለመቀጠል ፈቃደኝነታቸውን መግለፃቸውን የአውሮፓ ህብረት ባለሥልጣናት በትህትና ቢቀበሉም የለንደን ዋነኛዎቹ ወዳጆች ሳይቀሩ አብዛናዎቹ ለጥሪያቸው ጀርባቸውን ነው የሰጧቸው።

የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቬድ ካምረን ብሪታኒያ የአውሮፓ ህብረት አባል ሆኖ እንድትቀጥል ወይም ደግሞ ህብረቱን ለቃ እንድትወጣ የመወሰን ምርጫን ለህዝባቸው ለመስጠት ቃል መግባታቸው ከአጋሮቻቸው በኩል ትችትና ወቀሳን አስከትሏል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሪታኒያ ከህብረቱ ጋር ትቀጥል ወይም ትውጣ ሲል ህዝቡ እንዲወስን የሚያደርጉት ወግ አጥባቂው ፓርቲያቸው በመጪው ምርጫ ካሸነፈ ሲሆን ህዝበ ውሳኔውንም እ.ጎ.አ በ2017 መጨረሻ ለመጥራት ነው ያቀዱት ። ከዚያ አስቀድሞ ግን በአዲሱ የህብረቱ ስምምነት ላይ እንደገና ለመደራደር ይፈልጋሉ ። ሆኖም ይህ የድርድር ጥሪ

ኬምረንና ሜርክልምስል picture-alliance/dpa

ከቅርብ አጋሮቿም ሆነ ከህብረቱ ባለሥልጣናት በኩል በጎ ምላሽ አላገኘም ። ካምረን ሃገራቸው በህብረቱ ውስጥ እንድትቆይ እፈልጋለሁ እያሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማስቀመጣቸው ብዙዎቹ አልተስማሙም ። ይህን የካምረን አቋም ከተቃወሙት አንዷ ጀርመን ናት ። የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተር ቬለ ።

« ይሄ የፈለጉትን ብቻ መምረጥ የሚቻልበት የፖለቲካ አሰራር አይሰራም አውሮፓ በአጠቃላይ በተናጠል በዚህ በአፅናፋዊው የኤኮኖሚ ትስስር ዘመን የብሔራዊ ፍላጎት ማርኪያ ሳትሆን ክፉውንም በጎውንም ለመቀበል የተዘጋጀ ማህበረሰብ ነው ። »

ኬምረንምስል Reuters

ዴቬድ ካምረን በትናንቱ ንግግራቸው የአውሮፓ ህብረት ብሪታኒያ አባል ያልሆነችበትን የዩሮ ቀውስ በመፍታት መጠመዱን አስታውሰው የዩሮ ቀውስና ሌሎችም ህብረቱ ያጋጠሙት ፈተናዎች መፍትሄ ካልተገኘላቸው የአውሮፓ ውድቀት መከተሉ የብሪታኒያ ህዝብም ህብረቱን ወደ መልቀቅ ማዘንበሉ እንደማይቀር አሳስበዋል ። ህብረቱ የተሃድሶ እርምጃ ካልወሰደም ብሪታኒያ ማፈንገጧ አይቀሬ ነው ሲሉም አስጠንቅቀዋል ።

በሂደት የሚያረካቸው ስምምነት ላይ መድረስ ከቻሉ ግን ሃገራቸው በህብረቱ አባልነት እንድትቀጥል ከልባቸው እንደሚጥሩም ተናግረዋል ። ሆኖም ካምረን ከህብረቱ ጋር አንድ አግባቢ ውል ላይ ባይደርሱ የሚወስዱት እርምጃ ምን እንደሚሆን ከመግለፅ ተቆጥበዋል ። የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ማርቲን ሹልትዝ የካምረን ንግግር ርስ በርሱ የሚቃረን ነው ያሉት

« ከንግግሩ መጥፎው ነገር እርስ በርስ የሚጋጭ መሆኑ ነው ። በአንድ በኩል የውስጥ ገበያ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ ። በሌላ በኩል ደግሞ ደንቦቹ እንዲቀነሱ ይሻሉ ። አንድ ነገር ግን ግልፅ ነው ። 80 በመቶ የአውሮፓ ህብረት ደንቦች የውስጥ ገበያ ደንቦች ናቸው ። ይህም በጉዳዩ ውስጥ ዘልቀው አለመግባታቸውን ያመለክታል ። »

ቬስተርቬለምስል picture-alliance/dpa

ፈረንሳይ በበኩሏ የብሪታንያን የድርድር ጥሬ ፣ በምግብ መረጣ ና አንድ አይነት የስፖርት ጨዋታ ጀምሮ በመካከሉ እርሱን ትተን ሌላ ጨዋታ እንቀይር አይነት ጥያቄ ነው ስትል ነው ያጣጣለችው ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሎሮን ፋብዩስ ይሄ ይስማማኛል ያንን አልፈልግም የሚል ምርጫ በጋራ ማህበር ውስጥ አያስኬድም ነው ያሉት ። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ደግሞ ለዘብ ያለ አስተያየት ነው የሰጡት ።

« የእያንዳንዱን የግል ፍላጎት ለማራመድ ከሆነ አካሄዱ ማንኛውም የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገር ይህን ፈለግ መከተል ይችላል ። ግን አውሮፓ ማለት ምን ጊዜም ገለጋይ ስምምነት ላይ የሚደረስበት መሆን አለበት ። በዚህ መሠረት የብሪታንያን ፍላጎት በተመለከተ ለመነጋገር ዝግጁ ነን ። »

ካሜሩን የብሪታኒያ ህዝብ የአውሮፓ ህብረት አባል ሆኖ መቀጠል አለመቀጠል ላይ የህዝበ ውሳኔ እድል እንደሚሰጡ መናገራቸው ከአውሮፓ ህብረት አባላት ብቻ ሳይሆን ከሃገር ውስጥም ተቃውሞ አስከትሏል ። መፍቅሬ አውሮፓዎቹ የመንግሥቱ ተጣማሪዎች ነፃ ዲሞክራቶች እንዲሁም ዋነኛው ተቃዋሚ ሌበር የካምረንን እቅድ ተቃውመዋል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW