1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

​​​​​​​ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ባህር ዳር ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ናቸው ተባለ

ረቡዕ፣ ግንቦት 10 2014

ባለቤታቸው ወይዘሮ መነን ኃይሌ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት እንደሚበሳጩባቸው መረጃ ሲነግሯቸው በሀቅ ከማገልገላቸው በቀር የሚሰጧቸው መግለጫዎች ለእሥርም ሆነ ከሌሎች ጋር ለግጭት እንደማይዳርጋቸው ይገልፁ እንደነበር ተናግረዋል።

Äthiopien Addis Abeba |  Tefera Mamo
ምስል Solomon Muchie/DW

የብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ መሰወር

This browser does not support the audio element.

የአማራ ክልል የልዩ ኃይል የቀድሞው ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ባህር ዳር ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኙ መልእክት እንደደረሳቸው ባለቤታቸው ወይዘሮ መነን ኃይሌ ማምሻውን ለዶቼቬለ ተናገሩ። ወደ ባህር ዳር መቼ እንደተወሰዱ ያውቁ እንደሆን የተጠየቁት ወይዘሮ መነን " የተወሰዱት ዛሬ ይሁን የታገቱ እለት አላወቅንም" ብለዋል። መረጃውን ከማን እንደሰሙትና ምን ያህል እውነተኛ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄም " ባህርዳር ለሚገኝ ሰው እዚያ [ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ] መሆናቸውን መልእክት ልከውልኝ ነው ያወቅሁት " ብለዋል።

ባለቤታቸው ወይዘሮ መነን ኃይሌ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት እንደሚበሳጩባቸው መረጃ ሲነግሯቸው በሀቅ ከማገልገላቸው በቀር የሚሰጧቸው መግለጫዎች ለእሥርም ሆነ ከሌሎች ጋር ለግጭት እንደማይዳርጋቸው ይገልፁ እንደነበር ተናግረዋል።

ትናንት በሄዱበት የፍትሕ ተቋም ሁሉ ባለቤታቸው የት እንደሚገኝ የሚነግራቸው አለማግኘታቸውን የገለፁት ወይዘሮ መነን ዛሬ  ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ሄደው መጠየቃቸውንና ጉዳዩን እንዲያስመዘግቡ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም "አንድን ሰው ከሕግ ውጪ ማሰር፣ ያለበትን መደበቅና መሰወር የፍትሕ ተቋማትን ትርጉም አልባ ያደርጋቸዋል፣ በተጨማሪም ሰዎች በመንግሥት እና በሕግ የበላይነት ላይ ያላቸው እምነት እንዲሸረሸር በማድረግ ሕገወጥነትንም ያስፋፋል" ብለዋል።

ሰሎሞን ሙጬ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ኂሩት መለሰ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW