1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብይን በባህር ላይ ዘራፊዎች

ሐሙስ፣ ሰኔ 10 2002

አምስቱ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ5 ዓመት እንዲቀጡ ተፈረደባቸው።

የባህር ላይ ዘራፊዎችምስል AP

በኔዘርላንድ ሮተርዳም ዛሬ የተሰየመው ችሎት በእርግጥ የሶማሊያን የባህር ላይ ዘራፊዎችን ጉዳይ በመመልከት የመጀመሪያው አውሮዻዊ ችሎት ይሆናል። 5ቱ የባህር ላይ ዝርፊያ ለማድረግ በመሞከር የተከሰሱት ሶማሊያውያን እኛ አሳ አስጋሪዎች እንጂ ወንበዴዎች አይደለንም ቢሉም ሊሳካላቸው አልቻለም። እ ኤ አ በ2009 የተያዙት እነዚህ ሶማሊያውያን አንዲትን የኔዘርላንድ ዕቃ ጫኝ መርከብ ለማገት ሲሞክሩ እንደተያዙ የቀረበባቸው ክስ ያመለክታል። የዓለም ዓቀፉ የባህር ድርጅት ዳይሬክተር ፖቲንጋል ሙኩንዳ ይህ የፍርድ ሂደት ጠቃሚ ቢሆንም ዋንኞቹ ዘራፊዎቹን የሚያሰማሩትና በገንዘብ የሚደግፉት ሰዎች ካልt።ያዙ ለውጡ እጅግም ነው ይላሉ። የሮተርዳሙ ፍርድ ቤት ዛሬ ባዋለው ችሎት በ5ቱ ሶማሊያውያን ላይ የ5ዓመት ብይን አስተላልፏል።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW