1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

ተደራራቢ የአካል ጉዳተኝነት ከመድረሻዋ ያላቆማት ወጣት

ዓርብ፣ ሐምሌ 5 2016

አካል ጉዳተኞች እንደ አካል ጉዳታቸው ክብደት እና ተፈጥሮ የተለያዩ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ፈተናዎች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ። እንደዚያም ሆኖ ግን በገጠማቸው የአካል ጉዳት ማህበረሰቡም ሆነ ከተፈጥሯዊ ሁኔታዎች ታግለው አሸንፈው ለአካል ጉዳተኞች ብቻም ሳይሆን ለሌሎቹም ጭምር አርአያ የሆኑ ተጠቃሽ ሰዎች ጥቂት አይደሉም ።

Äthiopien | Universität Addis Abeba | Junge Behinderte Absolventen
ምስል Addis Ababa University/Ethiopia

«እንደኔ ላሉ የአካል ጉዳተኞች መድረስ ነው ቀጣዩ ግቤ » አንጓች መረጭ (ተመራቂ ተማሪ )

This browser does not support the audio element.

አካል ጉዳተኝነት የአንድን ሰው አካላዊ፣ አእምሯዊ ወይም የስሜት ችሎታዎች የሚገድብ ነገር ግን በማንኛውም ሰው በየትኛውም ጊዜ ሊከሰት የሚችል ነው። አካል ጉዳተኝነት ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ በአደጋ ወይም በህመም በሚከሰት ወይም ደግሞ  በጊዜ ሂደት እየጎለበተ የሚሄድ ሊሆንም ይችላል።  አካል ጉዳተኞች እንደ አካል ጉዳታቸው ክብደት እና ተፈጥሮ የተለያዩ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ፈተናዎች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ። እንደዚያም ሆኖ ግን በገጠማቸው የአካል ጉዳት ማህበረሰቡም ሆነ ከተፈጥሯዊ ሁኔታዎች ታግለው አሸንፈው ለአካል ጉዳተኞች ብቻም ሳይሆን ለሌሎቹም ጭምር አርአያ የሆኑ ተጠቃሽ ሰዎች ጥቂት አይደሉም ። 

የአንዲት አካል ጉዳተኛ ሠዓሊና ደራሲ ጥረት
አንጓች መረጭ ትባላለች ፤ ትውልዷ ሰሜን ወሎ ላሊበላ አካባቢ ሲሆን ዕደገቷ ደግሞ መዲናዪቱ አዲስ አበባ ነው ። የተደራራቢ አካል ጉዳተኛ ናት ። በተፈጥሮ የእግር አካል ጉዳተኛ ሆና የተወለደችው አንጓች የሁለት አመት ልጅ ከሆነች በኋላ በደረሰባት በእሳት የመቃጠል አደጋ ሰለባ ሆናለች። አንጓች ለወላጆቿ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኗ መጠን አካል ጉዳተኝነቷ በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮባቸዋል። እንደዚያም ሆኖ ግን ከአካባቢው ህክምና ተስፋ የቆረጡት ቆራጦቹ ወላጆች ለአንጓች የተሻለ ህክምና ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ ተሰደዱ ። የአንጓች ከባከባድ አካል ጉዳተኛ ልጅን የምትንከባከበዋ ወጣትድ አካል ጉዳተኛ ልጅን የምትንከባከበዋ ወጣትየከባድ አካል ጉዳተኛ ልጅን የምትንከባከበዋ ወጣትአዲስ ህይወት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያም ከዚህ ይነሳል። 

አንጓች ለወላጆቿ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኗ መጠን አካል ጉዳተኝነቷ በማህበራዊ ህይወታቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮባቸዋል። እንደዚያም ሆኖ ግን ከአካባቢው ህክምና ተስፋ የቆረጡት ቆራጦቹ ወላጆች ለአንጓች የተሻለ ህክምና ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ ተሰደዱ ።ምስል Addis Ababa University/Ethiopia

ከባድ አካል ጉዳተኛ ልጅን የምትንከባከበዋ ወጣት
« ስወለድ ጀምሮ እንደ ፓራላይዝድ አይነት ነበርኩ፤ ሁለት ሶስት ዓመት እስኪሞላኝ ድረስ ድረስ ምንም አይነt እንቅስቃሴ የማላደርግ አይነት ነበርኩ ።  ከዚያም ደግሞ ሁለት ዓመቴ ላይ ሌላ አደጋ ተጨመረብኝ ማለት ነው፤ ስለዚህ ድርብርብነቱ ጨመረ ማለት ነው  »
አካል ጉዳተኞች ባለባቸው የአካል ጉዳት ዓይነት በሚደርስባቸው የአካል ጉዳት መጠን በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ በሚኖራቸው የእለት ተዕለት መስተጋብር ወቅት የተለያዩ ተግዳሮቶች ይገጥሟቸዋል፡፡ አካላዊ ብቃትን በሚጠይቁ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ በማህበረሰቡ ውስጥ በሚታዩ የአመለካከት ችግር የስነ ልቦና ጉዳት የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ሊፈጠሩም ይችላሉ። አንጓች ትምህርት ቤት ያሳለፈችው ጊዜ ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው። 

በጥርሶቹ ብሩሽ ነክሶ በመሳል ተክኗል

« አመለካከቱ ትንሽ ከበድ ይላል ። የልጆቹ አመለካከት አብሮ መቀመጥ የማይፈልጉ ነበሩ ፤ መምህራኖቹም ቢሆኑ እንዴት መንከባከብ እንዳለባቸው በትክክል የተረዱ አይመስሉም ነበር፤ ይከብድ ነበር»
አካል ጉዳተኞች በሚኖሩባቸውም ሆነ ቀናቸውን በሚያሳልፉባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎ ለአካል ጉዳተኞቹ መበርታት አልያም ዝሎ መውደቅ የሚኖራቸው አስተዋጽዖ ቀላል አይደለም። አንጓች ጠንክራ ወደ ተሻለ ደረጃ እንድትድረስ ወላጆቿ እና የተማረችበት ትምህርት ቤት የበኩሉን አስተዋጽዖ አድርጎላታል። 
«ዋናው ቤተሰብ ነው። በጣም ትልቅ ድጋፍ አለው ። ትምህርት ቤት ስገባ ነገ ተምራ ብሎ ባያስበውም ያኔ ግን ደግሞ ትምህርት ቤት መዋሌ ትልቅ ጥቅም ነበር ለእነርሱ ከልጆች ጋር ዉዬ እንድመጣ ነበር መጀመሪያ፤ ወደ ዚህ ስመጣ ደግሞ መደነጋገሮች ነበሩት  » 

አካል ጉዳተኞች በሚኖሩባቸውም ሆነ ቀናቸውን በሚያሳልፉባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎ ለአካል ጉዳተኞቹ መበርታት አልያም ዝሎ መውደቅ የሚኖራቸው አስተዋጽዖ ቀላል አይደለም። አንጓች ጠንክራ ወደ ተሻለ ደረጃ እንድትድረስ ወላጆቿ እና የተማረችበት ትምህርት ቤት የበኩሉን አስተዋጽዖ አድርጎላታል። ምስል Addis Ababa University/Ethiopia

አካል ጉዳተኛው የቴኳውንዶ አሰልጣኝ


ወ/ሮ ገነት አሰፋ አንጓችን ከልጅነቷ ጀምሮ ጠንቅቀው ያውቋታል። አቅመ ደካማ ቤተሰቦቿ እርሷን ሰው ለማድረግ የከፈሉትን ዋጋ በማንሳት አንጓች በራሷ ራሷን ለማሸነፍ የሄደችበትን ርቀት እንዲህ ይገልጻሉ ።
« እኔ በጣም ትልቅ ደስታ ነው ምን አይነት ስሜት እንደሚሰማ ለሁላችንም ግልጽ ነው ። አንደኛ ቤተሰቧ እና እርሷ የነበሩበት ህይወት ጀምሮ ነው እኔ የማውቃቸው ማለት ነው ። እና በጣም ከፍተና ችግር ውስጥ ነው የነበሩት። በችግር ውስጥ ሆነው ግን በጽናት ልጅቷ እዚህ እንድትደርስ አባትየው ሽኮኮ እያደረገ ወደ ትምህርት ቤት ሲወስዳት ነው የማውቃት። እንደገና ደግሞ ልጅቷ በጣም ጠንካራ ልጅ ናት። »
አንጓች ከትውልድ እስከ ዕድገቷ ያለፈችባቸውን ውጣ ውረዶች እንድታሸንፉ ሁሌም ከጎኗ የነበሩት ወላጅ አባቷ ናቸው። ለእርሷ ሲሉ ሀገር « እስከ ስድስተኛ ክፍል እስከ 12 ወይም 13 ዓመቴ ድረስ አባቴ ነበር ሽኮኮ እያለ ያስተማረኝ»
መምህር ወንድሙ ሰለሞን የአንጓች መረጭ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህሯ ናቸው ። በትምህርት ቤቱ የነበራትን ቆይታ በአድናቆት የሚናገሩት መምህሩ የደረሰባት ተደራራቢ የአካል ጉት ካሰበችበት እንዳትደርስ አላገዳትም ይላሉ ።

የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ቅሬታ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ


« አንጓችን ለአራት ዓመት ሃይ ስኩል አስተምሬአታለሁ ፤ እጅግ በጣም መንፈሰ ጠንካራ ልጅ ናት ። ለሁኔታዎች የማትበገር እና እጅ የማትሰጥ ናት።»
በጥረቷ እና በዙሪያዋ በነበሩ ሰዎች ጥረት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የገባችው አንጓች ዘንድሮ በመጀመሪያ ዲግሪ ከተመረቁት ውስጥ አንዷ ናት። ተማሪዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በትምህርት የሚያሳልፉት ጊዜ እንኳንስ ለአካል ጉዳተኛ ለሌላውም ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆን አይጠረጠርም። አንጓች በዩኒቨርሲቲው የነበራትን ቆይታ ታስታውሳለች።
« አካል ጉዳተኝነት የሴትነት ያህል ተግዳሮት እንዳለው የገባኝ ዩኒቨርሲቲ ስገባ ነው። ዩኒቨርሲቲ ትንሿ ኢትዮጵያ ናት ነው የሚባለው ፣ ሁሉም ሲመጣ ባህሉ እና ማንነቱን ይዞ ነው የሚመጣው ፤ እና ልክ ዩኒቨርሲቲ ስገባ ፊታቸውን ታነበዋለህ ፤ ስላንተ ሲያወሩ ምናምን ታያቸዋለህ»

«ኤች አይ ቪ» እና የአካል ጉዳተኛ ሴቶች ችግር


አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ሰው በህይወታቸው የልብ መሻታቸውጋ ለመድረስ በራሳቸው ከሚያደርጉት ጥረት እና ትጋት ባሻገር የማህበሰቡ ዕገዛ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል  ።
«እንዲህ አይነት ጠንካራ ብናበረታታ ፣ አካል ጉዳተኞችን ማህበረሰቡ ባይነቅፍ፣ ነገ ተምረው የት ይደርሳሉ በቃ ስፍራቸው ይሄ ዝቅተኛ ቦታ ነው ብሎ  ባይል ፤ ከኋላ ሆነው ቢያበረታቷቸው »
መምህር ወንድሙ ሰለሞንም ይህንኑ ሃሳብ ያጠናክራሉ።

    የትነበርሽ ተሸለመች


« እናት እና አባቷ ያው ድህነት ቢኖርም ከጎኗ ባይሆኑ አይዞሽ ባይሏት እዚህ አትደርስም ነበር ። ግን አንጓች ዕድለኛ ሆና የነበረችበት አካባቢ ያሉ ሰዎች ይደግፏት ነበር ።  »
አንጓች አሁን ከልባ መሻትጋ ለመድረ,ስ እና ህይወቷን በአዲስ መንገድ ለመምራት የቤት ስራዋን በአግባቡ ሰርታለች። አሁን መሻቷ እንደ እርሷ ሁሉ የአካል ጉዳተኛ የህብረተሰብ ክፍልን መድረስ ነው። 
« ትምህርቱ ለእኔ ትልቅ አስተዋጽዖ አለው። ለጉዳት በተጋለጡ የህብrt,ሰብ ክፍሎች ላይ ነው የሚያጠናው እና የማማከር ስራ መስራት እፈልጋለሁ።  »
ህይወት በምዕራፍ የተከፋፈለች ናት ። የአንጓችም ህይወት ይኽኛውን የህይወት ምዕራፍ በድል አጠናቃ ለቀጣዩ ራሷን እያዘጋጀች ነው ። መንገዱ ረጅም ፣ ውጣ ውረድ የበዛበት ነገር ግን ለአንጓች የተቻለ ነበር ። 

ታምራት ዲንሳ

ፀሐይ ጫኔ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW