1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

የተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 21 2017

በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ በተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮ እና በትኩረት መስክ እንዲደራጁ መደረጉን ተከትሎ 15 ያህል ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ቅርፅ ይዟል በተባለው አፕላይድ ሳይንስ ማለትም ተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ መስክ ተመድበዋል። 15 የሚሆኑ የእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት መመስረቱ ተነግሯል።

የዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት
የተግባራዊ ሳይንስ ላይ የሚያተኩሩ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት ምስረታ በድሬደዋ ተካሂዷል። ምስል Mesay Teklu/DW

የተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት  

This browser does not support the audio element.

ትናንት የትምህርት ሚንስቴር እና ድሬደው ዩኒቨርሲቲ በጋር በመሆን በድሬደዋ ባዘጋጁት መድረክ አስራ አምስቱ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ተገናኝተው በቀጣይ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ያግዛል ያሉትን ኮንሰርቲየም መስርተዋል። የተመሰረተው ኮንሰርቲየም ዩኒቨርሲቲዎቹ ሲሰሩ ከቆዩበት ከአጠቃላይ ትምህርትወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርጉትን ሽግግር ያቀላጥፋል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። የኢትዮጵያ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲሰዎችን እስከ አሁን ድረስ በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር ዱጉማ አዱኛ ዩኒቨርሲቲዎቹ ተልእኳቸውን እንዲያሳኩ ለማድረግ አንዱ አካሄድ በመሆኑ ኮንሰርቲየሙ መመስረቱን ገልፀዋል።

ዶ/ር ዱጉማ አዱኛ በኢትዮጵያ የተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት ፕሬዝደንት ምስል Mesay Teklu/DW

ዶ/ር ዱጉማ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች ቀጣይ ሥራ ተግባር ተኮር የሚንበት መሆኑን ጠቁመዋል። ከ15ቱ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የሆነው የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዲ/ር ዑባህ አደም ልየታው በቀጣይ ተቋማቱ ችግር ፈቺ ውጤታማ ዜጋን የሚያፈሩ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ብለዋል። በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ መስክ የጀርመን ዩኒቨርሲቲዎችን በተመክሮነት ማየታቸውን ዶ/ር ዑባህ ጠቅሰዋል። በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የጥምረት ምስረታ መድረክ የዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዝዳንቶች ተገኝተዋል።

መሳይ ተክሉ 

ሸዋዬ ለገሠ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW