ተጨማሪው በጀት፤ የኮሬ መምህራን መፈታት፤ የእሥራኤል ሂዝቦላ ስምምነት
ሐሙስ፣ ኅዳር 19 2017ለ2017 በጀት ዓመት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀት ጸደቀ
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለ2017 በጀት ዓመት የቀረበለትን ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀት በአብላጫ ድምፅ አጽድቆታል። በ3 ተቃውሞ እና በ5 ድምፅ ተዐቅቦ የጸደቀው ተጨማሪው በጀት የኢትዮጵያን አጠቃላይ የ2017 ዓም በጀት ወደ 1.55 ትሪሊዮን ብር ከፍ አድርጎታል።
በ2017 ተጨማሪ በጀት ላይ በዶቼቬለ ፌስቡክ አስተያየት ከሰጡት አንዱ አሥራት አዴቶ አንዱ ናቸው ። « ክፍተቶችን እየፈተሹ ችግር ፈቺ መፍትሔ ማስቀመጥ ጥሩ ነው።» ሲሉ የበኩላቸው ሀሳብ ሰንዝረዋል። ሙሉሰው አዲስ፣ « ለምን ይውል ይሆን ? ገና ግማሽ ዓመት ሳይሞላ ተጨማሪ በጀት ማጽደቅ ያስፈለገው? የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። «ባለፈው የተበጀተው በጀት ለምክር ቤት ሲቀርብ በቂ ካልሆነ ታዲያ ለምን አፀደቀው? ግን ተወካዮቻችን ዝም ብሎ እጅ ማውጣት ብቻ ነው ስራቸው? ምንም ልማት እና የደሞዝ ጭማሪ ባላየንቦት ሁኔታ ሌላ በጀት ? ይህ ደግሞ የአዊ ሞገስ ጥያቄ ነው።
የእስራኤልና የሒዝቡላሕ ተኩስ አቁም፣ ለሠላም ወይስ ጊዜ መግዢያ
«እድገት ወይስ ውድቀት? ሲሉ ጥያቄ ያስቀደሙት ካህሳይ ታደሰ ደግሞ «ለማንኛውም እድገታችንንም ሆነ ውድቀታችንን ያሳምርልን ።»ብለዋል።
ምክር በጀቱን ከማጽደቁ በፊት በተካሄደው ውይይት ላይ ተጨማሪ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ በጀት በሀገሪቱ ዋጋ ንረትን እንዳያባብስ እና ኢኮኖሚውን እንዳያናጋ ሥጋት መኖሩ ተደጋግሞ ተጠይቋል። በውይይቱ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ "ተጨማሪ በጀት የሚቀርበው ተጨማሪ ገቢ መኖሩ ሲታመንበት" ተናግረው፣ መንግሥት ይህንን እንደሚያሳካውና "እንደምናገኘው እርግጠኛ ሆነን ያመንበትን ገቢ ነው ይዘን የቀረብነው" ብለዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ የሰጡት መልስ ያልተመቻቸው ፋሲካ ወሰኑ «ህዝብን ለድህነት አጋልጦ እና ያለ የሌለ ግብር ጭኖ በማማረር እንደምናሳካው አርግጠኛ ነን ብሎ በኩራት ከመናገር ይሉና ከዚያ ይልቅ «ማፈርን መምረጥ ይሻላል።» ብለዋል።
ሙስጠፋ ሁሴን ተጨማሪውን በጀት መነሻ አድርገው ለኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስር ዐብይ አህመድ ጥያቄም መልዕክትም አላቸው፤ « እርስዎ ሀገር አደገች እያሉ ነው። ትናንት ያወሩት ነገር ዛሬ ተተግብሮ አላየነውም። የመንግስት ሰራተኛው ኑሮ እርር አርጎታል። ያሀገሪቷን በጀትም ብሆን ከሀገሪቷ ነበራዊ ሁኔታ በመነሳት በጥናት ተደግፎ አንዴ ይበጀታል። ነገር ግን አሁን ተጫማሪ ተብሎ መበጀትስ ምንን የሰያል እንበል? ምን እያተደረገ ነው? በማለት ሌላም ጥያቄ ካከሉ በኋላ ።በርግጥ ሁሉንም ህዝብ ማርካት አይቻልም። እስኪ እንደኔ ቆም ብለው ቢያስቡበት እላለው። ሲሉ ሀሳባቸውን ደምድመዋል።
ታስረው የተፈቱት የኮሬ ዞን መምህራን
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ታስረው የነበሩ 66 መምህራን መፈታታቸውን የክልሉ መምህራን ማህበር በዚህ ሳምንት አስታውቋል። መምህራኑ የታሰሩት “ አለአግባብ የተቆረጠብን ደሞዝ ይመለስልን “ የሚል ጥያቄ ካነሱ በኋላ ነበር ፡፡ "ማንም ደሞዝ ሊቆርጥ አይገባም ፤ መብትም የለውም “ያሉት የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ መምህራኑ ከእሥር ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውን ለዶቼቬለ አረጋግጠዋል ፡፡መምህራኑ የተቆረጣባቸው ደሞዝ በአስቸኳይ እንዲመለስ ማህበሩ ከኮሬ ዞን እና ከክልሉ መስተዳድር ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር ላይ እንደሆነና በመምህራኑ ላይ ድብደባ ፣ እሥርና እንግልት የፈጸሙ የፀጥታ አባላትን በሕግ ለማስጠየቅ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውንም ገልጸዋል ፕሬዝዳንቱ ። በመምህራኑ መታሰር ላይ ከተሰጡት አስተያየቶች ውስጥ «ጌታ ያሻግራል ያኖራል» በሚል የፌስቡክ ስም የሰፈረው አንዱ ነው። «ሕጉ የሠራተኛ ደመወዝ መቁረጥ የሚቻለው 1.በሠራተኛው ፍቃድ 2 .በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብቻ መቆረጥ እንደሚቻል ይደነግጋል ነገር ግን አሁን የምናየው ሌላ ነዉ»ይላል።
ከሊባኖስ የውጭ ሰራተኞችን ለማስወጣት የሚደረገው ጥረት
አበራ ሳም ማም «ፍርዱን ከላይ ከእውነተኛው ፈራጅ ዳኛ በትዕግስት እንጠብቃለን። ሲሉ
«መብት መጠየቅ ወንጀል አይደለም። እውነት ፍትህ ካለ እንደውም እነርሱን ያሰሩ ባለስልጣናት በሕግ መጠየቅ አለባቸው የሚለው ደግሞ ጊዜ ደጉ በሚል የፌስቡክ ስም የቀረበ አስተያየት ነው።
አብቧል ያምራል ደግሞ ዶቼ ቬለ የአማርኛው ክፍል «ያለአግባብ የተቆረጠው ደመወዝ እንዲመለስ ለሚመለከታቸው አካላት ቃለ መጠየቅ በማድረግ የበኩላችሁን ብትወጡ? በማለት አሳስበዋል። አብቧል ለማሳሰቢያዎ እናመሰግናለን። ይህ የኛም እቅድ ነው።
የእስራኤልና የሂዝቦላ የተኩስ አቁም ስምምነት
ታሪኩ ናዝሬት «ህዝብ ያላወቀውን ደግሞ አስቡት»ሲሉ ሌሎችም ያልተሰሙ ተመሳሳይ እርምጃዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። በዚህ ሳምንት የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎችን ትኩረት ከሳቡት መካከል የእሥራኤልና ሒዝቦላህ የተኩስ አቁም ስምምነት አንዱ ነው። በእስራኤልና የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ መካከል የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ከሆነ ከትናንት አንስቶ በሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ወደ ሊባኖስ እየተመለሱ ነው። በዶቼቬለ ፌስቡክ ላይ ከተሰጡት አስተያየቶች «እግዝአብሔር ይመሰገን ሰላም ለሶው ዘረ በሙሉ።» የሚለው ዊዝ ጂ ሮስ በሚል የፌስቡክ ስም የተጻፈው ይገኝበታል። «አላህ፡ተኩስ፡አቁሙን፡የእውነት፡ያድርገው።በአለም፡በአራቱም፡አቅጣጫዎች፡ሠለም፡ይውረድ።» የሚለው ደግሞ የሁሴን ከተሞ ሙንድኖ አስተያየት ነው። ራብያት ሀሰን፣ ሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ በመድረሳቸው አልሃምዱሊላህ ሲሉ እግዚአብሔርን አመስግነዋል። ሰላምን የሚያክል ምንም የለም ያሉት ራብያት አስገራሚው ነገር በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ና ከፍተኛሁኔታ ከእስራኤል ጎን ሆነው ጦርነቱን ሲያግዙ የነበሩት ፈረንሳይ ና አሜሪካ አደራዳሪ መሆናቸው ነው።
መንግሥት 125 ኢትዮጵያውያንን ከሊባኖስ መለሰ
በተደጋጋሚ ወደ እስራኤል የሚተኮሱ ሚሳኤሎችን በማምከን እስራኤልን በማስታጠቅ ና ከምንም በላይ ጠቃሚ መረጃዎችን በስለላ ተቋሞቻቸው ና ቴክኖሎጂዎቻቸው ለእስራኤል በመስጠት ሲያግዙ እንዳልነበር ። ካሉ በኋላ ለማንኛውም ሂዝቦላ በድርድሩ መስማማቱ ጥሩ እርምጃ ነው በማለት አወድሰዋል። እየሩስ ጂሪም እንደ ራብያት «ተመስገን የድንግል ማርያምልጅ ኢየሰስክርቶስ ክብር ይግባህ ለዓለም ሁሉ ስላም አደራህን ፈጣሪዬ እንዲዘልቅ አድርገው። ሲሉ ለአምላካቸው ምስጋናም ተማጽኖም አቅርበዋል ።
ሞአሳኑኒ ደግሞ «ይሄን ዜና ኢትዮጵያ ላይ አላህ ያሰማን» የሚል ምኞታቸውን አስተላልፈዋል። የያሬድ ማኅበረሰብ ድምጽ በሚል የፌስቡክ የቀረበ አስተያየት «እስራኤል የተኩስ አቅሙን ስትፈርም ጦርነቱን በማንኛውም ጊዜ ልትጀምር እንደምትችል ባለስልጣናቱ ሲናገሩ ተደምጠዋል ። ታዲያ ይህ የተኩስ አቁም ሳይሆን ጊዜ መግዣ ከመሆን አያልፍም ፤ ዘላቂ አይመስልም። ለነገሩ ማምሻም እድሜ ነው ! በሰላም ያለምንም ስጋት ተኝቶ ማደር ቀላል አይደለም። የተኩስ አቁም ስምምነቱ ይደገፋል። የእስራኤልና የሂዝቦላ ስምምነት ተግባራዊ መሆኑ ትናንት ይፋ ከተደረገ በኋላ እሥራኤል ሊባኖስ ውስጥ የሂዝቦላ ይዞታዎችና አባላት በምትላቸው ላይ ድብደባ ማካሄዷን ቀጥላለች። ይህም የስምምነቱ ፈራሚ የሆኑትን ሁለቱን ወገኖች ማወዛገብ ጀምሯል።
ኂሩት መለሰ
ጸሐይ ጫኔ