1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ተጽዕኖው በግልጽ መታየት የጀመረው የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ድጋፍ መቋረጥ

ረቡዕ፣ ጥር 28 2017

የዩናይትድ ስቴትስ የልማት አጋር ድርጅት የሆነው ዩ. ሴስ. ኤይድ ለልማት ሥራዎች የሚያደርገውን ድጋፍ እና እርዳታ ማቋረጡን ተከትሎ ጫናው በኢትዮጵያ ላይ መታየት ጀምሯል። እርምጃው በተለይ በዴሞክራሲ፣ በሰላም፣ በሰብአዊ መብት፣ በማህበራዊ ዘርፍ፣ በግብርና እና ሌሎችም መስኮች ላይ በሚንቀሳቀሱ ተቋማት ላይ ቀጥተኛ ጫና ማሳደር መጀመሩ ተነግሯል።

USA Virginia 2023 | Logo der US-Behörde für Internationale Entwicklung
ምስል፦ Celal Gunes/AA/picture alliance

የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ርዳታ መቋረጥ እና አንድምታው

This browser does not support the audio element.

ተጽዕኖው በግልጽ መታየት የጀመረው የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ድጋፍ መቋረጥ
የዩናይትድ ስቴትስ የልማት አጋር ድርጅት የሆነው ዩ. ሴስ. ኤይድ ለልማት ሥራዎች የሚያደርገውን ድጋፍ እና እርዳታ ማቋረጡን ተከትሎ ጫናው በኢትዮጵያ ላይ መታየት ጀምሯል።
እርምጃው በተለይ በዴሞክራሲ፣ በሰላም፣ በሰብአዊ መብት፣ በማህበራዊ ዘርፍ፣ በግብርና እና ሌሎችም መስኮች ላይ  ከዚህ ድርጅት ድጋፍ እያገኙ የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ ቀጥተኛ ጫና ይፈጥርባቸዋል ሲሉ አንድ የዘርፉ ባለሙያ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

"እያንዳንዱ ሆስፒታል ላይ የምንጠቀምባቸው ዕቃዎች አብዛኞቹ በእርዳታ የምናገኛቸው ናቸው" ያሉን አንድ የጤና ባለሙያ ደግሞ፣ በጤና ዘርፍ ላይ የሚያሳርፈው ጫና "በቀላሉ ይህ ነው ተብሎ የሚገለጽ አይደለም።" ብለዋል።

የትራምፕ አስተዳደር የኤኮኖሚ ጦርነት
በጤና ዘርፍ ላይ መስተዋል የጀመረው ተጨባጭ ተጽዕኖ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚመሩት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ግዙፉ የዓለማችን የተራድዖ ድርጅት በሆነው ዩ.ኤስ.ኤይድ በኩል ለልዩ ልዩ ዘርፎች ይሰጥ የነበረን እርዳታ ማስቆማቸው ድንጋጤ ፈጥሯል። የድርጅቱ የዋሽንግተን ዲሲ ዋና መሥሪያ ቤት ሠራተኞችም ሥራ እንዳይገቡ ስለመታዘዙ ታውቋል።

የዚህ ውሳኔ ተጽዕኖ ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ስለመሆኑ የጤና ሚኒስቴር ለሁሉም የክልል ጤና ቢሮዎች እንደፃፈው በተገለፀ እና በማህበራዊ መገናኛ አውታሮች በተሰራጨው ደብዳቤ ክልሎች ፣ ሚኒስቴሩ ከአሜሪካ የበሽታዎች መከላከል ማዕከል እና ከUSAID ጋር ባደርገው ውል መሰረት የተቀጠሩ ሰራተኞች ውል እንዲቋረጥ ማሳሰቡ ተጠቃሽ ነው።

የዚህ ውሳኔ ተጽዕኖ ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ስለመሆኑ የጤና ሚኒስቴር ለሁሉም የክልል ጤና ቢሮዎች እንደፃፈው በተገለፀ እና በማህበራዊ መገናኛ አውታሮች በተሰራጨው ደብዳቤ ክልሎች ፣ ሚኒስቴሩ ከአሜሪካ የበሽታዎች መከላከል ማዕከል እና ከUSAID ጋር ባደርገው ውል መሰረት የተቀጠሩ ሰራተኞች ውል እንዲቋረጥ ማሳሰቡ ተጠቃሽ ነው።ምስል፦ Alemenew Mekonnen/DW

ሚኒስቴሩ ከእነዚህ ድርጅቶች በሚገኝ የበጀት ድጋፍ የሚከናወን ማንኛውም ሥራም ሆነ ክፍያ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ እንደደረሰውም በደብዳቤው ገልጿል። "እያንዳንዱ ሆስፒታል ላይ የምንጠቀምባቸው ዕቃዎች አብዛኞቹ በእርዳታ የምናገኛቸው ናቸው" 
ያሉን የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዮናታን ዳኘው በጤናው ዘርፍ ላይ የሚደርሰው "ጫና በቀላሉ ይህ ነው ተብሎ የሚገለጽ አይደለም" ብለዋል።

ዉይይት፣ የአሜሪካ ረቂቅ ሕግጋት ይዘት፣ጥቅምና ጉዳት ለኢትዮጵያ

ሁልጊዜ በእርዳታ መኖር ስለማይቻል ሁኔታው የማንቂያ ደዎል ነው ያሉት ባለሙያው፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያደርጉ፣ መንግሥትም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በማድረግ ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የአሜሪካ መንግሥት ውሳኔ የኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶችንም በጉልህ የሚነካ ይመስላል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሕብረት ዳይሬክተር አቶ መሱድ ገበየሁ ይህንኑ ነው የሚገልፁት።
"ይህ እርምጃ ምናልባት ለብዙ ድርጅቶች ሠራተኞችን ማሰናበት ጨምሮ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ማቋረጥ እና የመሳሰሉት ነገሮች ስለሚመጡ በሲቪል ማህበረሰቦች ላይ ብዙ ጫና የሚፈጥር እንደሆነ ነው የምረዳው"

የአሜሪካ መንግሥት ውሳኔ የኢትዮጵያ ሲቪክ ድርጅቶችንም በጉልህ የሚነካ ይመስላል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሕብረት ዳይሬክተር አቶ መሱድ ገበየሁ ይህንኑ ነው የሚገልፁት።ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

በውጭ እርዳታ የሚንቀሳቀሱት የሲቪክ ድርጅቶች ዕጣ

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ትናንት ማክሰኞ አስቸኳይ ሲል ባወጣው መግለጫ "በአሁኑ ወቅት ከዩ.ኤስ.ኤይድ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ሲቪክ ድርጅቶች ያለ ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ግልፅ ፍቃድ ንብረት የማስተላለፍ፣ የማስወገድ ወይም የመሸጥ ወይም ከመደበኛ ሥራዎች ጋር ተያያዥ ከሆኑ ጉዳዮች ውጭ በማናቸውም መልኩ ሀብትና ገንዘብን ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የተከለከለ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡" ብሏል። አቶ መሱድ እንደሚሉት ግን ይህ የነበረ አሰራር ነው። 

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ውሳኔዎች በኢትዮጵያ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራሉ?
በዚህ ውሳኔ የአሜሪካ መንግሥት ተወቃሽ ነውን?
ሁሉም ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሀብት ማፈላለግና ምንጫቸውን ማስፋት ላይ መበርታት እንዳለባቸው የገለፁት አቶ መሱድ ይህ በአለም አቀፍ ወንድማማችነት መርህ የሚመጣ የነበረ ድጋፍ እና እርዳታ እንጂ የአሜሪካ መንግሥት ለምን አቋረጠው ተብሎ የሚነቀፍበት ባለመሆኑ በራስ አቅም ለመቆም መንቀሳቀስ የግድ የሚልበት ጊዜ ለመምጣቱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW