ተፈናቃይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
ረቡዕ፣ ጥር 18 2014ማስታወቂያ
ትግራይ ዉስጥ በሚደረገዉ ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ሸሽተዉ ወደ መሐል ኢትዮጵያ የተመለሱ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እንደሚመደቡ የተገባላቸዉ ቃል እስካሁን ድረስ ገቢር አለመሆኑን አስታወቁ።ከ1500 የሚበልጡት ተማሪዎች እንደሚሉት አማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች መመደባቸዉን ትምሕርት ሚንስቴር ገልጦላቸዉ ነበር።ዩኒቨርስቲዎቹ ግን ተማሪ የመቀበል አቅም እንደሌላቸዉ ገልፀዉላቸዋል።የባሕርዳርና የጎንደር ዩኒቨርስቲዎች ባለስልጣናት ዛሬ በተለይ ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት ግን የተመደቡላቸዉን ተማሪዎች በቅርቡ እንደሚቀበሉ ቃል ገብተዋል።የትምህርት ሚንስቴር ባለስልጣናትም የተማሪዎቹ ችግር በቅርቡ እንደሚቃለል ተስፋ ሰጥተዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ