ቱኒዚያ፤ በምርጫዉ በቂ ህዝብ አልተሳተፈም
ሰኞ፣ ጥር 22 2015
ማስታወቂያ
በቱኒዚያ የተካሄደው ሁለተኛው ዙር የፓርላማ ምርጫ በቂ ህዝብ ሳይሳተፍበት መቅረቱ ተነገረ። የመምረጥ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸዉ ዜጎች መካከል ድምፅ የሰጡት አሥራ አንድ ነጥብ ሦስት በመቶ የሚሆኑት ብቻ መሆናቸዉ ተዘግቧል። ፕሬዝዳንት ካይስ ሳይድ ከጀመሩት አወዛጋቢ ከተባለዉ ህገ-መንግስታዊ ተሃድሶ ወዲህ የህዝብ ተወካዩ ፓርላማ ምንም አይነት ስልጣን የለዉም። በምርጫዉ አነስተኛ የመራጭ ህዝብ ቁጥር መታየቱ የማያስገርም አይደለም የተጠበቀ ነዉ ተብሏልም። በቱኒዝያ የሚገኙት አብዛኞቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫዉ ላለመሳተፍ መወሰናቸዉም ተመልክቷል። ፓርቲዎቹ ፕሬዚዳንት ሳይድ እያካሄዱት ነው በተባለዉ ተሃድሶ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ፓርላማውን አዳክመዋል፤ በቱኒዝያ ዲሞክራሲን ቀብረዋል ሲሉ ይወነጅሏቸዋል። ይሁንና ጥቂት መራጮች ተገኙበት የተባለዉ የምርጫ ዉጤት እስካሁን ይፋ አልተደረገም።
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ