1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ቲክ ቶክ ለኢትዮጵያ ምን ይዞላት ፣ ምንስ ይዞባት መጣ ?

እሑድ፣ ታኅሣሥ 5 2018

የማህበራዊ መገናኛ መድረኩ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የፈጠራ አቅማቸውንና ተሰጥኦዋቸውን እንዲያሳዩ፣ ከእኩዮቻቸው ጋር ትስስር እንዲፈጥሩና አዳዲስ የገቢ ማግኛ ሥልቶችን እንዲቀይሱ የዕድል በር መክፈቱ አይታበልም፡፡ ጥቂት የማይባሉ እዚህ ግባ ከማይባል ቦታ ተነስተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝና አትርፎላቸዋል።

ቲክ ቶክ ለኢትዮጵያ ምን ይዞላት ፣ ምንስ ይዞባት መጣ ?
ቲክ ቶክ ለኢትዮጵያ ምን ይዞላት ፣ ምንስ ይዞባት መጣ ?ምስል፦ Dado Ruvic/REUTERS

ቲክ ቶክ ለኢትዮጵያ የበረከት ወይስ የመርገምት መንገድ?

This browser does not support the audio element.

ዘመኑ የዲጅታል ነው ። ኢትዮጵያም እንደተቀረው ዓለም በዚሁ ስረዓት ውስጥ መጓዟ የግድ ነው። በዚህ በፈጣን ቴክኖሎጂ ታግዞ በፍጥነት በሚለዋወጥ የዲጂታል ዓለም አብሮ መራመድን ይጠይቃል።

በዚህ ረገድ  በፈጣን የመረጃ መለዋወጫነታቸው የሚጠቀሱ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ገና በማደግ ላይ ላሉ ሃገራት ስረዓተ መንግስት እስከማስቀየር የደረሱ ብርቱ ተጽዕኖዎች ማሳደራቸው ታይቷል።

አሁን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ጥቅም ላይ የዋለው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎችን ማፍራት የቻለው ቲክ ቶክ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ በግልጽ የሚታይ ተጽዕኖ እያሳደረ መጥቷል።

የማህበራዊ መገናኛ መድረኩ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን  ወጣቶች የፈጠራ አቅማቸውንና ተሰጥኦዋቸውን እንዲያሳዩ፣ ከእኩዮቻቸው ጋር ትስስር እንዲፈጥሩና አዳዲስ የገቢ ማግኛ ሥልቶችን እንዲቀይሱ የዕድል በር መክፈቱ አይታበልም፡፡ ጥቂት የማይባሉ እዚህ ግባ ከማይባል ቦታ ተነስተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝና አትርፎላቸዋል።  ሃብት እስከማካበት ያደረሳቸውም ጥቂት አይደሉም።

መድረኩ  በተጨማሪም ለኢትዮጵያውያን የምግብ እና የአለባበስ ባህላቸውን ፣  ተፈጥሯዊ እና ባህላዊ ሃብታቸውን ፣ ታሪካቸው እና ማንነታቸውን  እርስ በርሳቸው ከመጋራት አልፈው ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ እንዲችሉ ዕድል ፈጥሮላቸዋል።

መድረኩ  በተጨማሪም ለኢትዮጵያውያን የምግብ እና የአለባበስ ባህላቸውን ፣  ተፈጥሯዊ እና ባህላዊ ሃብታቸውን ፣ ታሪካቸው እና ማንነታቸውን  እርስ በርሳቸው ከመጋራት አልፈው ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅ እንዲችሉ ዕድል ፈጥሮላቸዋል።ምስል፦ Privat

ይሁን እንጂ በዚያው ልክ መድረኩ በዚያው ልክ አሉታዊ ጎኖችና ተጽዕኖዎች እንዳለው በግልጽ ከማሳየቱ በላይ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሆን የሚያደርጉ በርካታ ችግሮች እያስከተለ መምጣቱ ስጋት አሳድሯል።

ኢትዮጵያዉያን ቲክቶክ በመጠቀም ከተቀሩ አፍሪቃዉያን ያን ያህል ስማቸው ጎልቶ ባይነሳም አሁን አሁን የተዛቡ መረጃዎችን በማሰራጨት የፖለቲካ ትርፍ ማግኛ እየሆኑ መምጣታቸው  ይነገራል። በተጨማሪም  ዕምነትን ከዕምነት ሊያጋጩ የሚችሉ የጥላቻ መልዕክቶችን ማሰራጨትን ጨምሮ በህብረተሰብ ጤናማ አኗኗር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ይዘቶችን ማጋራታቸው ከቀጠለ አሳሳቢ መሆኑም አይቀርም ፡፡

የማህበራዊ መገናኛ መድረኩ በዕድሜ የተገደበ አጠቃቀም እንዲኖረው  ፣ ማህበራዊ ኃላፊነት የማይወጡ ይዘቶችን ለመከላከል እና  ዜጎች በሃገራቸው ማህበረ ፖለቲካ ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮች ውስጥ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የመንግስት ግልጽ የክትትል እና ቁጥጥር ስረአት ምን ድረስ መሆን አለበት የሚለውም ማጠያየቁ አይቀርም።

ተወያዮች 

ዶ/ር መልሰው ደጀኔ የጋዜጠኝነት እና ስነ ተግባቦት መምህር  ፤ከሐዋሳ

ሃጂ መሱድ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ጠቅላይ ጸሐፊ  ፤ አዲስ አበባ

ጋዜጠኛ የሸዋ ማስረሻ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ ፤አዲስ አበባ

ወጣት መርዕድ ቱሉ ከወጣት ተጽዕኖ ፈጣሮች ፤ አዲስ አበባ

አዋያይ ጋዜጠኛ ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW