ታሪካዊዉ የኃይል ምንጭ፤ ከሰል
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 11 2003ማስታወቂያ
ከሰል ለማግኘት ደግሞ እንጨት ይፈለጋል፤ እንጨት ለማግኘት ዛፍ ይቆረጣል። ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ዉስጥ ይህን አስመልክቶ የተሰራ አንድ ጥናት እንደሚያመለክተዉ ወደ66 ሺ ገደማ ቶን ከሰል ለማምረት ወደአንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ዛፎች ይጨረጨፋሉ። ጥራቱን የጠበቀ ከሰል የሚገኘዉ ከአገር በቀል እና እድሜ ጠገብ ዛፎች በመሆኑ የብዝሃ ህይወት ስብጥር መጉዳቱ፤ አካባቢን ማራቆቱ ሳያንስ፤ ከሰል የሚከስልባቸዉ አካባቢዎች መሬት ለእርሻም ሆነ ለግጦሽ እሚበጅ አይሆንም ዉስጡ በሚጠራቀመዉ ካርቦን ሞኖክሳይድ ሰበብ! ወደከባቢ አየር የሚለቀቀዉ አደገኛ ጋዝም ተፅዕኖ ቀላል አይደለም። ግን ደግሞ ከሰል የብዙሃኑ ህዝብ የጓዳ ምሰሶ፤ የምድጃ አጋር ነዉ።
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ