1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ታሪካዊው የያዓ መሠራ መስጊድ

ሐሙስ፣ ሰኔ 5 2017

ሼህ አልፈኪ ከናይጀርያ ተነስተው በሱዳን በኩል ወደ ኢትጵያ መጥተው ያዓ መሰራ መስጂን ከመገንባታቸው በፊት በአሶሳ ለተወሰኑ ዓመታት መቆየቸውን፣ ከዚም ወደዳምቢ ዶሎ፣ጂማ፣ ትግራይና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሀይማኖት ትምህርት መስጠታቸውን ከ30 ዓመት በላይ በያዓ መሠራ መስጅድ በማገልገል ላይ የሚገኙ ሼህ መሐመድ ሳሲ ተናግረዋል፡፡

Äthiopien | Ya Masara-Moschee in der Benshangul-Gumuz-Region
ምስል፦ Negasa Desalegn/DW

ታሪካዊው የያዓ መሠራ መስጊድ

This browser does not support the audio element.

 

በምዕራብ ኢትዮጵያ ማኦኮሞ በተባለ ልዩ ወረዳ ውስጥ የሚገኘውን ያዓ መሠራን እንቃኛለን፡፡ በምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍል ከአዲስ አበባ በ680  ኪ.ሜ ርቀት ገደማ ላይ የሚገኘው ታሪካዊው ያዓ መሠራ መስጅዲ በአሁኑ ወቅት ከሀይማኖታዊ ይዘቱ በተጨማሪም የቱሪስት መዳረሻ እየሆነም ይገኛል፡፡ ቦታው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በየዓመቱ አረፋ በዓልን ለማክበር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ወደ ስፍራው ይጓዛሉ፡፡

የያዓ መሠራ ታሪክ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያዓ መሰራን ጨምሮ ታሪካዊ የሆኑ በርካታ የሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ የቱሪዝም መዳረሻዎች እንደሚገኙ የክልሉ ባህል እና ቱርዚም መረጃ ያስረዳል፡፡ ያዓ መሠራ የተባለው 73 ዓመት ገደማ ያሰቆጠረው መስገጅድ በአሁኑ ወቅት በዓመት  ወስጥ ከ30 እስከ 40 ሺ የሚደርሱ ሰዎች ወደ ቦታው በመሄድ በዓል ያከብሉ፡፡ መስጅዱ በ1944 ዓ.ም የናጀሪያዊ ዜግነት ባላቸው ሼህ አልፈኪ አህመድ ዑመር እንደተመሰረተ ታሪኩ ያስረዳል፡፡ ሼህ አልፈኪ ከናይጅሪያ በመነሳት በሱዳን በኩል የሐይማኖት ትምህርት  እያስተማሩ ወደዚህች ስፍራ በመምጣት መስጅዱን መገንባታቸውን ከሐይማኖቱ አባቶች አንዱ ከሆኑት ሼህ መሐመድ ሳኒ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ሼህ አልፈኪ ከናይጀርያ ተነስተው በሱዳን በኩል  ወደ ኢትጵያ መጥተው ያዓ መሰራ መስጂን ከመገንባታቸው በፊት በአሶሳ ለተወሰነ ዓመታት መቆየቸውን፣ ከዚያ ወደ ዳምቢ ዶሎ፣ጂማ፣ ትግራይ እና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሀይማኖት ትምህርት ማስተማራቸውን የገለጹ ሲሆን ከዚሁ በመነሳት ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሰዎች የአረፋ በዓልን ጨምሮ ሌሎች በእምነቱ የሚከበሩ በዓላትን ወደ ያዓ መሠራ በመምጣት እንደሚያከብሩ ከ30 ዓመት በላይ ለሚሆን ጊዜ በያዓ መሠራ መስጅድ በማገልገል ላይ የሚገኙ ሼህ መሐመድ ሳሲ ተናግረዋል፡፡

 ያዓ መሠራን የገነቡት ይሄው ናይጀሪያዊው ዜጋ ሼህ አልፈኪ አህመድ ከትውልድ ቀያቸው ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ ምድር  የመጡ የእስልምና ሐይማት ተከታይና የእምነት አስተማሪ ብቻ ሳይሆኑ በአካባቢውን ዘመናዊ ግብርና ስራን ያስፋፉ እንደነበር አመልክተዋል፡፡

 

ባሳለፈፍነው ሳምንት አርብ የተከበረውን  አረፋ በዓል ከተለያዩ ኢትዮጵያ ከፍሎች የመጡ የእምነቱ ተከታዮች በበስፍራው አክብረዋል፡፡ በእምነቱ ተከታዪች ዘንድ ይህን ያዓ መሰራ መስጂድ የሰሩት  ሼክ አልፊኪ በፈጣሪ የተላኩ ተብሎ ስለሚታመን ቦታው እንደ የድህነት  ወይም ልዩ በመሆነ መልኩ የተባረከ  ስፍራ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ስለዚህም በየዓመቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ያዓ መሰራ  በማቅናት በዓሉን እንደሚያከብሩ ሼክ መሐመድ ሳኒ አመልክተዋል፡፡

‹‹ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ሰዎች አረፋን ‹‹በያዓ መሠራ›› አክብረዋል››

ዘንድሮ የአረፋ በዓልን ከተለያዩ ኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ ሰዎች በብዛት ወደ ቦታው በመሄድ አክብረዋል፡፡ አቶ አኑዋር እንድሪስ በአማራ ክልል ዳንግላ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ የዘንድሮውን 1446ኛ የአረፋ በዓል በማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ያዓ መሰራ በመገኘት ካከበሩት መካከል ናቸው፡፡ አቶ አኑዋር ያዓ መሠራን ታሪክ በ1991 ዓ.ም ተማሪ እያሉ ታሪኩን መስማታቸውን  ገልጸው ታሪኩን ከሰሙ 27 ዓመት በኃላ በቦታ ላይ አረፋ በዓል ማክብራቸውን አመልክተዋል፡፡

የያ ማሳራ መስጊድ ምስል፦ Negasa Desalegn/DW

ከጅማ መጥተው በያዓ መሰራ አረፋን ያከበሩት ሌላው የእምነቱ ተከታይ ደግሞ  ሰይድ መሐመድ በኪር ናቸው፡፡ ከጅማ፣ኢሉ አባቦር፣ከደምቢ ዶላ እና የተለያዩ ቦታዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች በታሪካዊው ያዓ መሠራ አረፋን ማክበራቸውን ተናግረዋል፡፡ ለብዙ ዓመታትም በስፍራው በዓል ማክበራቸውን የተናገሩት አቶ ሰይድ መሐመድ ከኮሮና ወረርሽኝ ወዲህ ዘንድሮ ብዙ ቁጥር ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች በቦታው ላይ አረፋ በዓልን ማክበራውን አብራርተዋል፡፡

የአሶሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ሼክ ዩኑስ ኢሳም በአካባቢው ብዙ ዓመት የሰሩና ታሪኩን በቅርበት የሚያቁ ነዋሪ ናቸው፡፡ በወቅቱ መስጅዱ በተሰራበት ዓመት አካባቢ ብዙም መንደር ያልተስፋፋበት ስፍራ እንደነበር በመግለጽ በአሁነ ወቅት አካባቢው ወደ መለስተኛ መንደር አድጎ አረፋን በዓል እየጠበቁ የሚመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች ወደ ፈጣሪያቸው ጸሎች የሚያደርሱበት ስፍራ ሆኗል ብሏል፡፡

እንደ ሼክ ዩነስ ገለጻ በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ሀይማታዊ ጉዞ(ሀጂ) እምብዛም የተለመደ አይደለም፡፡ ወደ ያኣ መሠራ የተጀመረው ዓማኖታዊ ጉዞዎችም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ መጎልበትና ባህል መሆን እንዳበት መልዕክት አስላልፈዋል፡፡ በዚህ በያዓ መሰራ ቀደም ሲል መስጅድ ከመሰራ በፊት አካባቢውም የሚጠራት ስያሜ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡   

‹‹በዓመት እስከ 40ሺ ሰዎች ከተለያዩ ሀገሪቱ ክፍሎች ለበዓል ወደ ቦታው ይሄዳሉ››

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባህልና ቱሪዚም ቢሮም በክልሉ በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ታሪካዊ መስኮች እንዳሉ ገልጾ አሁን አሁን ወደ ታሪካዊው ያዓ መሠራ በመሄድ በዓላትን የሚያከብሩ የእምነቱ ተከታዮችም ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ በክልሉ ባህልና ቱሪዚም ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሽመልስ እንድሬ ይህ ያዓ መሰራ ከሀይማኖታዊ እሴቱ በተጨማሪ የውጭ እና የሀገር ወስጥ ቱሪስቶችን በመሳብ የኢኮኖሚ ምንጭም እየሆነ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

‹‹ ያዓ መሠራ የሚለው ስያሜ ያዓ እና መሠራ ከተባሉ ሁለት ቃላቶች የተገኘ ሲሆን ያዓ ማለት የሚፈስ ውሀ፣ መሠራ ደግሞ ቤተ መንግስት እንዴ ማለት ነው፡፡››

በዓመት አረፋን ጨምሮ የተለያዩ ባህላትን ለማክበር እስከ 40 ሺ የሚደርሱ ሰዎች ወደ ስፍራው በማቅናት በዓል እንደሚያከብሩ አክለዋል፡፡ በተጨማሪም ያዓ መሰራ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ብዙ ባልተስፋፋበት 19 40ዎቹ መስጅዱን የሰሩት ሼህ አልፈኪ በኩል በተሰራው ቀን ቀን ለወፍጮ አገልግሎት ማታ ደግሞ ለኤክትሪክ አገልግሎት የሚውል ሀድሮ ሐይል በውሀ የሚሰራ ኤሌክትሪክ  በያዓ መሰራ እንደነበር አቶ ሽመልስ እንድሬ አክለዋል፡፡

ያዓ መሰራ የሚገኝባት ማኦኮሞ የተባለችው ወረዳ የተለያዩ እምነቶች የሚስተናገዱባት እና የተለያየ እምነት ተከታዮች ተቻችለው የሚኖሩባት አካባቢ ናት ተብሏል፡፡ ወረዳዋ ከታሪካው ያዓ መሰራ በተጨማሪ የግዙፉ የማኦና ከሞ ዕጩ ብሔራዊ ፓርክና  ልዩ ልዩ ተፈጥሮአዊ የቱሪዝም መስህብ ሀብቶች  መገኛ እንደሆነች የተገለጸ ሲሆን ቦታው ከአሶሳ ከተማ በ90 ኪ.ሜ ገደማ ላይ እንደሚገኝ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተገኘ መረጀ ያመለክታል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW