1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ፈረንሳዊት ፖለቲከኛ ማሪን ለ ፔን በማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ

ሰኞ፣ መጋቢት 22 2017

ፈረንሳዊትዋ ስደተኛ የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ማሪን ለ ፔን «ራሊ ናሽናል» በተባለዉ ፓርቲያቸዉ በኩል የአውሮፓ ፓርላማ ገንዘብን አላግባብ በመጠቀም ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ። ዛሬ ሰኞ ፓሪስ ላይ በዋለዉ ችሎት፤ ማሪን ለ ፔን የአራት ዓመት ፅኑ እስራት ሁለቱን ዓመት እግራቸዉ ላይ የመቆጣጠርያ ቀበቶ ታስሮባቸዉ የቁም እስር ተፈርዶባቸዋል።

ፈረንሳዊትዋ የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ማሪን ለ ፔን
ፈረንሳዊትዋ የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ማሪን ለ ፔን ምስል፦ Gabrielle Cezard/SIPA/picture alliance

ታዋቂዋ ፈረንሳዊት ፖለቲከኛ በማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ

ፈረንሳዊትዋ ስደተኛ ጠል የሆነዉ የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ማሪን ለ ፔን «ራሊ ናሽናል» በተባለዉ ፓርቲያቸዉ በኩል የአውሮፓ ፓርላማ ገንዘብን አላግባብ በመጠቀም ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ። ዛሬ ሰኞ ፓሪስ ላይ በዋለዉ ችሎት፤  ማሪን ለ ፔን የአራት ዓመት ፅኑ እስራት ከተፈረደባቸዉ በኋላ ፤ ሁለቱን ዓመት እግራቸዉ ላይ የመቆጣጠርያ ኤሌክትሮኒክ ታስሮባቸዉ የቁም እስር ተፈርዶባቸዋል። ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታትም ከማንኛዉም የፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ታግደዋል። በዚህም የፈረንሳይቷ የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ የለ ፔን የፖለቲካ ጉዞ እዚህ ላይ ሳያከትም እንዳልቀረ እየተነገረ ነዉ። ለ ፔን ዛሬ ሰኞ  ፍርድ ቤት ከመቅረባቸዉ በፊት የፖለቲካ ጎዙዋቸዉ በዚህ ክስ ምክንያት ሳያበቃ እንዳልቀረ መናገራቸዉን ዶቼ ቬለ ዛሬ ቀደም ብሎ ዘግቧል። ፈረንሳይ ፓሪስ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለዉ ችሎት በ ለ ፔን እና ፓርቲያቸዉ ለፓርላማ ረዳቶች ከታሰበዉ የአውሮጳ ፓርላማ ገንዘብ ውስጥ 3 ሚሊዮን ዩሮ ማለትም (3.25 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) አላግባብ ፓርቲያቸዉን ለማደራጀት ተጠቅመዋል ሲል በማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል። ፈረንሳዊትዋ የቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ማሪን ለ ፔን  በሚቀጥለዉ የጎርጎረሳዉያን 2027 ለፕሬዚዳንትነት ምርጫ መወዳደር አይችሉም። ከዚህ ቀደም በፈረንሳይ ሦስት ጊዜ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ የተወዳደሩት ለ ፔን፤ 13 ሚሊዮን የሚሆን መራጮች እንደነበሯቸዉም ተመልክቷል። እንደ አቃቤ ሕጎች ገለፃ ከላይ የተጠቀሰዉ ገንዘብ ለፓርቲዉ የቀረበዉ ከጎርጎረሳዉያኑ 2004 እስከ 2016 ባሉት ጊዜ ውስጥ ሲሆን ፓርቲዉ የአዉሮጳ ኅብረትን ሕግጋቶችን በመጣስ በፈረንሳይ ለሚኖሩ ለፓርቲዉ ሠራተኞች ክፍያ ጥቅም ላይ አዉሏል ተብሏል። የ 56 ዓመትዋ ለ ፔን «ራሊ ናሽናል» የተባለዉ ቀኝ አክራሪዉ ፓርቲያቸዉ፤ የደረሰባቸዉን ክስና ፍርድ « ሥራቸውን እንዲያቆሙ ያቀደ ፖለቲካዊ ጥቃት» ሲሉ ጥፋተኛ የተባሉበትን ክስ ሁሉ ሃሰት ሲሉ ክደዋል። በአንድ ወቅት በ ማሪን ለ ፔን አባት የተመሰረተዉ እና ይመራ የነበረዉ የፈረንሳዩ «ራሊ ናሽናል»  ፓርቲ በአሁኑ ጊዜ በፈረንሳይ ፓርላማ ትልቁ ነጠላ ፓርቲ መሆኑም ተመልክቷል።

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW