1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታጣቂዎች በማረቆ 7 ሰዎችን ገደሉ

ዓርብ፣ ነሐሴ 24 2016

ጥቃት በተፈጸመበት በማረቆ ልዩ ወረዳ የአሁኑ አይነት ጥቃት ሲደርስ የመጀመሪያው እንዳልሆነ የሟቾቹ የቅርብ ቤተሰብ አቶ ሁሴን ይናገራሉ፡፡ የአሁኑ ጥቃት ግን «ዘግናኝና ታቅዶ በሌሊት በተኙበት የተፈጸመ ነው»ብለዋል።የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠው የተፈጸመው ከምሥራቅ መስቃን ወረዳ በመጡ ሰዎች ነው ብለዋል ፡፡

በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል የምትገኘው የኮሼ ከተማ
በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል የምትገኘው የኮሼ ከተማምስል Mareko district Communication office

ታጣቂዎች በማረቆ 7 ሰዎችን ገደሉ

This browser does not support the audio element.


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ማረቆ ልዩ ወረዳ ዲዳ ሀሊቦ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች  በታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎችን ትናንት ሐሙስ ከቀበሩ ወዲህ በበረታ ሀዘን ውስጥ ይገኛሉ ፡፡ የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አቶ ሁሴን ለመንጎ ግን ሟቾችን አፈር ለማልበስ እንዳልታደሉ ይናገራሉ ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በጥቃቱ ቆስለው የተረፉ ቀሪ ሰዎችን ይዘው ስልጢ ዞን ወደ ሚገኘው የወራቤ ሆሰፒታል በመሄዳቸው ነው  ፡፡ የሟቾቹ የቅርብ ቤተሰብ መሆናቸውን ለዶቼ ቬለ የተናገሩት አቶ ሁሴን ታጣቂዎቹ ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት ተኩስ ከከፈቱባቸው አሥራ አንድ ሰዎች መካከል ሰባቱ መሞታቸውን ገልጸዋል ፡፡በመስቃን እና በማረቆ ማህበረሰብ መካከል የተቀሰቀሰ ግጭት

ጥቃት አድራሾቹ 

በነዋሪዎቹ ላይ ጥቃት የተፈጸመበት የማረቆ ልዩ ወረዳ የአሁኑ አይነት ጥቃት ሲደርስ የመጀመሪያው እንዳልሆነ የሟቾቹ የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ሁሴን ይናገራሉ ፡፡ ይሁንእንጂ በቀበሌው ነዋሪዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪው “ ጥቃቱ ዘግናኝና ታቅዶ በሌሊት በተኙበት የተፈጸመ ነው ፡፡ ሰው እንዴት ሕጻናትና ሴቶችን ተኩሶ ይገድላል “  ሲሉ ይጠይቃሉ ፡፡በጉራጌ ዞን በተቀሰቀሰ ግጭት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ
ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ በተባለው ቀበሌ ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠው ጥቃት አድራሾቹ ከምሥራቅ ጉራጌ ዞን ምሥራቅ መስቃን ወረዳ ተሻግረው የመጡ ናቸው ብለዋል ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ወልቂጤምስል Shewangzaw Wegayehu/DW

ከጥቃቱ በኋላ

መዓከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ታጣቂዎች ግድያ ፈጸሙ

ዶቼ ቬለ በጥቃቱ ዙሪያ የምሥራቅ መስቃን ወረዳንም ሆነ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል  የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎችን አግኝቶ ለማነጋገር ከትናንት ጀምሮ ያደረገው ጥረት አልተሳካም ፡፡ የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ ግን አሁን ላይ በቀበሌው ዳግም ሌላ ጥቃት እንዳይከሰት ከመከላከያ ሠራዊትና ከክልል የፀጥታ አባላት ጋር በመሆን የቅኝት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል ፡፡  በማረቆ ልዩ ወረዳ እና በአጎራባች ምሥራቅ መስቃን ወረዳ መካከል በዘጠኝ ቀበሌያት ላይ የይገባኛል ጥያቄ እንደሚነሳባቸው ይታወቃል ፡፡ ከዚሁ ውጥረት ጋራ በተያያዘ በቀበሌያቱ  አሁን ድረስ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ ፡፡ በሁለቱ ማህበረሰቦች መካከል ያለውን ቁርሾ ለመፍታት ባለፈው ዓመት ተካሂዷል የተባለው ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት አሁንም በነዋሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችን ማስቆም የቻለ አይመስልም ፡፡
ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ኂሩት መለሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ


ፎቶ ከማረቆ ልዩ ወረዳ መንግሥት ኮሚኒኬሽን


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW