ትምህርት
ትምህርት እና ሴቶች
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 2 2011ማስታወቂያ
በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት መረጃ መሠረት 132 ሚሊዮን ሴት ልጆች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው። መሰረታዊ የትምህርት ክህሎቶች ከሌላቸው 750 ሚሊዮን አዋቂዎች መካከል ሁለት ሶስተኛዎቹ ሴቶች ናቸው። ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ከሚገኙ ሴት ልጆች መካከል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን የሚያጠናቅቁት ከአንድ እጅ አይልቁም።
ይኸ አስከፊ ሐቅ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም የሚል አቋም ላይ የደረሰው በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት «የእሷ ትምህርት የእኛ ተስፋ» በተሰኘ አዲስ ውጥን ይፋ አድርጓል። ለመሆኑ እቅዱ ምን ይዟል? ሃይማኖት ጥሩነህ ዘገባ አላት
ሐይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ